ለደቡብ ክልል አፈ-ጉባዔ ጽ/ቤት ሀዋሳ፤ ጉዳዩ፡- በህገ-መንግስቱ መሠረት የሥልጣን ርክክብ እንዲደረግ ስለማሳሰብ፤ ========= አንደሚታወቀው ሁሉ የሲዳማ ህዝብ ለዚህች አገር ሰላም፣መረጋጋትና አንድነት የራሱን የታሪክ አሻራ ያኖረና በአንፃሩም ደግሞ በየዘመኑ የሚፈራረቁ አምባገነን የኢትየጵያ ገዢዎች የሚያደርሱበትን በደልና አፈና በጽናት ስታገል የቆየ ህዝብ እንደሆነ ታሪካዊ ሀቅ ነው፡፡ በተለያዩ ጊዜያት የሀገሪቷን ሥልጣን ኮርቻ የሚቆናጠጡ ገዢዎች ሲዳማን ሳይሆን የሲዳማን ሀብት ለመቀራመት ካላቸው ከፍተኛ ፍላጎት የህዝቡን ቋንቋ፣ታሪክ፣ ባህልና ማኅበራዊ አሻራና ማንነት ለመናድ ሲሰሩ ቆይተዋል፡፡የሀገር ግንባታ ሂደት የማንነት ፈተና በማይሆንበት መልኩ መስራት ይቻላል የሚል ጠንካራ አቋም ማራመድ የጀመሩት የሲዳማ ቀደምት ታጋዮችና ሌሎች የትግል አርበኞች በከፈሉት የህይወት ዋጋ ላለፉት 28 አመታት ስራ ላይ የዋለው ህገ-መንግስታዊ ሥርዓት እውን ሆኗል፡፡ ምንም እንኳን የሲዳማ ህዝብ የጭቁን ብሔሮችን ድምጽ አስተጋብቶና ታግሎ ለ1987 ዓ.ም ህገ-መንግስት ታሪክ የማይረሳ አሻራውን ለማሳረፍ ቢበቃም የሲዳማ ምድር እንጅ የሲዳማ ህዝብን አምርረው በሚጠሉ ገዢ መደቦች በተጠነሰሰ ሴራዎች ህዝባችን የህገ-መንግስቱ ትሩፋት ተቋዳሽ እንዳይሆን በመታገዱ ምክንያት ለቀጣይ ሰላማዊ የትግል ምዕራፍ ለመቀጠል ተገዶአል፡፡ በገዛ ሀገሩ ወደ ዳር የተገፋና በይ ተመልካች ሆኖ ለዘመናት የቆየው ሰፊው የሲዳማ ህዝብ በደሙና ባጥንቱ የተጻፈው ህገ-መንግስት ሊታደገው ባለመቻሉ ለሞት፣ ለስደትና ለእስራት ቢዳረግም ቅሉ ህዝብን ግን ከትግል ወደ ኋላ ሊያስቀረው አልቻለም ፡፡ በመሆኑም ከአባቶች የተወረሰ መብትን የማስከበር የትግል ወኔ ለዚህ ዘመን ትውልድ በመድረሱ አዲሱ ትውልድም የትግል
It's about Sidaama!