በሁለት ተማሪዎች መካከል በተፈጠረ ግጭት የአንድ ተማሪ ህይወት መጥፋቱን ተከትሎ በሀዋሳ ዩኒቨርስቲ የሰዓት ገደብ መጣሉን የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ ገለፀ
በሁለት ተማሪዎች መካከል በተፈጠረ ግጭት የአንድ ተማሪ ህይወት መጥፋቱን ተከትሎ በሀዋሳ ዩኒቨርስቲ የሰዓት ገደብ መጣሉን የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ ገለፀ
በትላንትናው ዕለት በሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ሁለት ተማሪዎች በመካከላቸው በነበረ የቆየ ግጭት ምክንያት በተፈጠረ ፀብ የአንድ ተማሪ ህይወት መጥፋቱን የገለፁት የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ ኮማንደር እዮብ አቤቶ ናቸው፡፡
በግጭቱ ሟች በስለት መወጋቱን እንደሰማ ወዲያውኑ በቦታው የደረሰው የከተማው ፖሊስ ተጎጂው የህክምና እርዳታ እንዲያገኝ ቢያደርግም በሪፈራል ሆስፒታል ህክምና እያገኘ ባለበት ወቅት ህይወቱ ማለፉን ጨምረው ገልፀዋል፡፡
ድርጊቱን የፈፀመው ተማሪ እና ድርጊቱ እንዲፈፀም የተባበሩ አካላት ፖሊስ በስውር እና በግልፅ ባደረገው ክትትል በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የገለፁት ኮማንደር እዮብ አስፈላጊው ምርመራ እየተከናወነ መሆኑንም ጨምረው ገልፀዋል፡፡
ከተማሪዎችና ከዩኒቨርስቲ ማህበረሰብ አባላት ጋር በጉዳዩ ዙሪያ ፖሊስ ሰፊ ውይይት ማድረጉን የገለፁት ኃላፊው በአሁን ሰዓት በሁሉም ካምፓሶች የሚገኙ ተማሪዎችና የዩኒቨርስቲ ማህበረሰብ አባላት ድርጊቱን አውግዘው ወደሰላማዊ የመማር ማስተማር ስራው መመለሳቸውን ገልፀዋል፡፡
ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደቱን አስጠብቆ ለመቀጠል ከዩኒቨርስቲ ተማረዎችና የዩኒቨርስቲ ማህበረሰብ ጋር በተደረገ ውይይት ላልተወሰነ ጊዜ የተማሪዎች መውጫ እና መግቢያ ሰዓት ላይ ገደብ መቀመጡን ኮማንደር እዮብ ጨምረው ገልፀዋል፡፡
በዚህም ከምሽት አንድ ሰዓት ብኅላ ወደ ዩኒቨርስቲ መግባትም ሆነ ከዩኒቨርስቲ መውጣት ላልተወሰነ ጊዜ የተከለከለ መሆኑን የገለፁት ኮማንደር እዮብ ከምሽት ሁለት ሰዓት ብኋላ በዩኒቨርስቲ ቅጥር ገቢ ውስጥ ከፀጥታ አካላት ውጭ መንቀሳቀስ ላልተወሰነ ጊዜ መከልከሉንም ጨምረው ገልፀዋል፡፡
Comments
Post a Comment