የሲዳማ ዞን አስተዳደር የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ትላንት ወዲያ ባስነበበው ጋዜጣና በተለያዩ መጽሔቶች የሲዳማ አስተዳደር ዋና አስተዳዳሪ ከአቶ ደስታ ሌዳሞ ጋር የተደረገው ቃለ-ምልልስ ከአንድ ወር በፊት የተደረገ መሆኑንና በዚህ ሣምንት ውስጥ የተደረገ አለመሆኑን የሲዳማ አስተዳደር ህ/ግ/ ጽ/ቤት ገልጿል፡፡
አያይዞም፤ በተለይ የሲዳማ አዲሱ ክልል ምስረታ በተመለከተ መጽሔቱ የዞ የወጣው ከወር በፊት የተደረገውን ቃለ-ምልልስ መሆኑን በድጋሚ በመግለፅ በአንዳንድ ሶሻል ሚዲያዎች ሁለት አይነት ሀሳብ በአንድ ጊዜ እንደተላለፈ ተደርጎ በመውሰድ ግሪታ ውስጥ የመግባት አይነት አዝማሚያዎች በመኖራቸው ውድ የሲዳማ ህዝብና የህዝባችን ወዳጆች በሙሉ ምስረታው በአንድ ወር ውስጥ ለመጨረስ በቂ ዝግጅት በማድረግ ላይ መሆናችንን ስንገልፅላችሁ በታላቅ ደስታ ነው ብሏል፡፡
ዛሬ ላይ የወጡ አንዳንድ የሲዳማ ክልል ምስረታን የሚያመለክቱ ዜናዎች እንደሚያሳዩት፤ የሲዳማ ክልል ምስረታ በሚቀጥሉት ሁለት ሳምንታት ውስጥ ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል።
Comments
Post a Comment