የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በአጭር ጊዜ ውስጥ በአዲስ ክልል መመስረት የሚያስችለውን ዝግጅት አጠናቀቀ፡፡
የሲዳማ ብሔር ለመብቱ እና ለነጻነቱ ሲታገል የህይወት እና አካላዊ መስእዋትነትን በመክፈል ጭምር ትግል ማድረጉ ለምዕተ ዓመት እና ከዚያም በላይ መታገሉ የሚታወቅ ነው፡፡
ይህ ብሄሩ ያለማቋረጥ ያደረገው ትግል ዛሬ ላይ የታየውን ድል ለመጎናጸፍ ታጋሽ በመሆን ጭምር ዋጋ የከፈለበትም ሆኖ ይገኛል፡፡
በዚህም ህዳር 10 ቀን 2012 ዓ/ም ህዝበ ውሳኔ ምርጫ ሲያካሂድ ወጣቶች፣ እናቶች፣አባቶችና አዛውንቶች ሳይቀሩ በነቂስ ወጥተው ነጻ፣ ፍትሀዊና ሰላማዊ ምርጫ ሲያካሂዱ ሂደቱ ለዓለም ትልቅ ትምህርት የሚሰጥና ድንቅ የሚባል ነበር፡፡
ይህንኑን ምስረታ እውን ለማድረግም ትግሉን የሚመጥን ዝግጅት እንዲያደርጉ ትልቅ ተልዕኮ የተሰጣቸው ኮሚቴዎች የተቋቋሙ ሲሆን እያንዳንዱ ኮሚቴም ስራውን በተገቢው መልኩ ያጠናቀቀ መሆኑን ስንገልጽ ህዝባችን ለምስረታው ዕለት ሲዳማ ብሄር መገለጫ የሆኑ ዝግጅቶችን በማድረግ እንድጠብቁን በመጠቆም ነው።
Comments
Post a Comment