መቀመጫውን በሀዋሳ ከተማ ያደረገው ኢፓርኬ የሁለንተናዊ ብቃት ማበልጸጊያና የስልጠና ማዕከል በራዕይና በእይታ ቅኝት ዙሪያ የማነቃቂያ ስልጠና ሰጠ፡፡
በ 3 ዋና ዋና አርዕስቶች ማለትም፤በራዕይና በራዕይ ተግዳሮቶች፡ በአላማ ጽናት እንዲሁም በዕይታ ቅኝት ዙሪያ በተሰጠው ስልጠና ላይ በከተማው በተለያዩ ተቋማት በመሪነት ላይ የሚገኙ ግለሰቦች፤ ወጣት ነጋዴዎች እንዲሁም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ተገኝተዋል፡፡
የኢፓርኬ ስልጠና ማዕከል መስራችና ስራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ አራርሶ ገረመው እንደገለጹት ስልጠናው አላማና ራዕይ ያለውን ዜጋ ከማብቃት ባለፈ ወጣቶች በነገሮች ሳይሰናከሉ አርቀውና አስፍተው ማየት እንዲችሉ፤ ብቃታቸውን ማሳደግ እንዲችሉ፤ ስለ ሀገርና ዜጋ ማሰብ እንዲችሉ፤ ውስጣዊ አቅማቸውን ተጠቅመው አላማቸውን ማሳካት እንዲችሉ እንዲሁም ህይወታቸውን በአግባቡ መምራት እንዲችሉ ከማገዝ አንጻር ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው አስረድተዋል፡፡
የዕለቱ የክብር እንግዳና የሀዋሳ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ከተማ ዶባ በበኩላቸው ወጣቱን ማዕከል ባደረገው የከተማው ሁለንተናዊ የልማት እንቅስቃሴ ላይ መሰል ስልጠናዎች የሚኖራቸው ፋይዳ የጎላ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ይህንንም መሰረት በማድረግ የከተማ አስተዳደሩ ከኢፓርኬና መሰል ተግባራት ላይ ከተሰማሩ ድርጅቶች ጎን በመቆም ማንኛውንም ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን አቶ ከተማ ጨምረው ገልጸዋል፡፡
የሀዋሳ ከተማ ህዝብ ግንኙነት ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ መልካሙ ተፈራ በበኩላቸው ወጣቱን መሰረት ያደረጉ የኢፓርኬን አጠቃላይ እንቅስቃሴዎች በማድነቅ በበኩላቸው ማንኛውንም ድጋፍ ለማድረግ ፈቃደኛ መሆናቸውን አሳውቀዋል፡፡ አክለውም ወጣቶችና ሌሎች የስልጠናው ተካፋዮች ከስልጠናው ያገኙትን ትምህርት ወደ ተግባር በመቀየር ከራስ አልፈው ሀገርንና ወገንን ለመጥቀም ቁርጠኛ መሆን እንደሚጠበቅባቸው አሳስበዋል፡፡
በዕለቱ ከቀረቡት የስልጠና ርዕሶች መሀል “የራዕይ ተግዳሮቶች” በሚል በደራሲ ስመጥሩ ታየ የቀረበው የሚገኝበት ሲሆን “በአላማ ጽናት” ዙሪያም ከሀገረ አሜሪካ የመጡት ምሁር አቶ ታደለ ነጋሽ ሰፊ ትንታኔ በመስጠት ጠቃሚ ዕውቀቶችን ለሰልጣኞች አስተላልፈዋል፡፡
የስልጠናው ዋነኛ አካል የሆነው አርዕስት በአቶ አራርሶ ገረመው የቀረበው “የእይታ ቅኝት” ሲሆን አላማን መኖር፤ እይታን ማስተካከል፤ ቦታን ማወቅ፤ ውስጣዊ አቅምን ማዳበርና በመሳሰሉት የስኬት ቁልፍ ሚስጥሮች ዙሪያ ሰፊ ትንተናን አካቷል፡፡
የስልጠናው ዋነኛ አካል የሆነው አርዕስት በአቶ አራርሶ ገረመው የቀረበው “የእይታ ቅኝት” ሲሆን አላማን መኖር፤ እይታን ማስተካከል፤ ቦታን ማወቅ፤ ውስጣዊ አቅምን ማዳበርና በመሳሰሉት የስኬት ቁልፍ ሚስጥሮች ዙሪያ ሰፊ ትንተናን አካቷል፡፡
በቀጣይም ኢፓርኬ መሰል ተግባራቶችን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ለማወቅ ተችሏል፡፡
Comments
Post a Comment