የሲዳማ ዞን ለሲዳማ ክልል ምስረታ ስነ-ስርዕት (የክልል ምረቃ ድግስ) ዝግጅት እያካሄደ ነው
*************
(ጥር 20 ፣ 2012
ማለዳ ሚዲያ)
*************
(ጥር 20 ፣ 2012
ማለዳ ሚዲያ)
የሲዳማ ህዝብ አስተዳደር በክልል ለመደራጀት የሚያስችለውን ቅድመ ዝግጅት እያጠናቀቀ መሆኑን በተደጋጋሚ ሲገልጽ ከርሟል።
ከስልጣን ርክክቡ መዘግየት ጋር ተያይዞ በህዝቡ ዘንድ የተለያዩ ጥርጣሬዎች እየተነሱ ቢሆንም ዞኑ እያደረኩ ያለሁትን ዝግጅት የሚያስቆም አንዳች ነገር አልገጠመኝም በማለት በያዝነው ወር ማገባደጃ ርክክቡ ፍጻሜ አግኝቶ አዲሱ ክልል በይፋ እንደሚመረቅ በተደጋጋሚ ለህዝቡ ቃል እየገባ ነው።
ክልል ሆኖ ለመደራጀት የሚያስፈልጉ የህግ የመዋቅርና መሰል ቅድመ ሁኔታዎች በመጠናቀቅ ላይ መሆናቸው ሲገለጽ የነበረ ሲሆን ከርክክቡ ጋር በተያያዘ የደቡብ ክልል ም/ቤት ስልጣኑን በደብዳቤ እንደሚያስረክብ በመርህ ደረጃ ከዞኑ ጋር መግባባት ላይ ተደርሶ የነበረ ቢሆንም እስካሁን ደብዳቤው ከደቡብ ክልል እንዳልወጣ ሚድያችን ባደረገው ማጣራት ማረጋገጥ ተችሏል።
በያዝነው ወር መጨረሻ ይኖራል ተብሎ እየተጠበቀ ያለው የክልል ምረቃ ድግስ በብልጽግና ስብሰባ አማካኝነት ሊራዘም ይችላል የሚሉ ስጋቶች ቢበራከቱም ዞኑ ስለጉዳዩ የሰጠው ተለዋጭ ፍንጭ የለም።
ማለዳ ሚድያ በዚህና መሰል ጉዳዮች ላይ ከሰሞኑ ጠለቅ ያሉ መረጃዎችን በማሰባሰብ ሰፊ ትንታኔ ይሰጥበታል።
ዜናው የማለዳ ሚዲያ ነው
Comments
Post a Comment