ለክልል ምስረታ ተገቢ ዝግጅት እየተደረገ ነው
ህዳር 10 ቀን መላው ህዝባችን በሰጠው ድምጽ መሰረት የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስን ለማቋቋም ይሁንታ ያስገኘ ተግባርን እውን ማድረግ ተችሏል፡፡
ይህን ተከትሎም አዲሱን ክልላችንን መመስረት የሚያስችል ቅደም ተከተላዊ አደረጃጀትን ከነባሩ ክልል ጋር በመቀናጀት አስፈላጊው ሁሉ በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡
ከዚህ ጎን ለጎን ነባሩ ክልል አዲሰ ለሚመሰረተው የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ህጋዊ ርክክብ ማድረግ የሚያስችለውን አሰራር ዘርግቶ ተግባራዊ በማደረግ ላይም ይገኛል፡፡
በዚህም ይፋ የሚደረገው ክልላችን መላው ህዝባችን፣ ታላላቅ እና ታዋቂ ግለሰቦች በተገኙበት በታላቅ ድምቀት እውን ማድረግ እንዲቻል እያንዳንዱ አካሄድ በተጠና እና ቅንጅታዊ አሰራርን ባማከለ መልኩ ከዳር የሚያደርሱ የተቋቋሙ ኮሚቴዎች የበኩላቸውን እስተዋጾኦ እያበረከቱም እንደሆነ መግለጽ ይቻላል፡፡
በመሆኑም መላው ህዝባችን ህጋዊ አሰራርን እና ቅደም ተከተልን ጠብቆ እየተከናወነ ያለውን የክልላችንን የምስረታ በአንዳንድ ማህበራዊ ሚዲያዎች በተቀመጠው ቀን መሰረት አለመሆኑን እየጠቆምን ጊዜውን አስመልክቶ እና ያለው ሂደት የሚጠቁሙ መረጃዎችን ከተማ አስተዳደሩ በየጊዜው በገጹ ላይ ይፋ እንደሚያደርግ ይገልጻል፡፡
ስለሆነም ህዝባችን ከዚህ ቀደም ያደርግ እንደነበረው ሁሉ ቀኑን በሰከነ ሁኔታ እና በትዕግስት እንዲጠብቅ አስተዳደሩ በዚህ አጋጣሚ ጥሪውን ያቀርባል፡፡
Comments
Post a Comment