የከተማዋን ደህንነት በማስጠበቅ ህብረተሰቡን በእኩል መልኩ ለማገልገል ከመቼውም ጊዜ በላይ መዘጋጀታቸውን የሀዋሳ ከተማ ፖሊስ አባላት ገለጹ፡፡
አባላቱ ይህንን የገለጹት ለሶስት ቀናት ባካሄዱት የስራ አፈጻጸም ግምገማ ማጠቃለያ መድረክ ላይ ነው፡፡
ሰራዊቱ ባሳለፈው የስራ ጊዜያት ውስጥ የነበረ ቡድንተኝነት የስራ ሞራላቸውን የነካ እንደሆነ ገልጸው አሁን እየተፈጠረ ባለው ግልጸኝነት እጅግ መደሰታቸውን ሲናገሩ ህብረተሰቡን በቁርጠኝነት ለማገልገል ምንም አይነት እንቅፋት እንደማኖር በመተማመን ነው፡፡
ሰራዊቱ ባሳለፈው የስራ ጊዜያት ውስጥ የነበረ ቡድንተኝነት የስራ ሞራላቸውን የነካ እንደሆነ ገልጸው አሁን እየተፈጠረ ባለው ግልጸኝነት እጅግ መደሰታቸውን ሲናገሩ ህብረተሰቡን በቁርጠኝነት ለማገልገል ምንም አይነት እንቅፋት እንደማኖር በመተማመን ነው፡፡
በአንዳንድ አባላት በሚስተዋሉ የስነ ምግባር ችግሮች በህብረተሰቡ ዘንድ አሜኔታ እንድናጣ ሆነናል ያሉት አባላቱ ውስጣዊ ችግሮቻችንን የሚፈታ አመራር በማግኘታችን የስራ ሞራላችን ከፍ ብሏልም ብለዋል፡፡
የሰራዊት አባላቱ አክለውም ህግን ከማክበርና ከማስከበር አንጻር ትኩረት ሰጥተው ለመስራትና ህብረተሰቡን ለመካስም ጭምር መዘጋጀታቸውን ነው የተናገሩት፡፡
ከጥቂት ወራት በፊት ባለፈው የሪፍረንደም ወቅት እና የገብርኤል መንፈሳዊ በዓል በሰላም መጠናቀቅ የሰራዊቱ ሚና ከፍተኛ እንደነበር የተናገሩት የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ጥራቱ በየነ ናቸው፡፡
አቶ ጥራቱ አክለውም አንዳንድ የሰራዊቱ አባላት ህብረተሰቡን በእኩል ከማገልገል አንጻር፣ በጥቅማ ጥቅም መደለል፣ቡድንተኛ መሆን፣ሙያዊ ስነምግባርን በመዘንጋት እና በሌሎች ምክንያቶች ኃላፊነታቸውን እንዳልተወጡ በግምገመው ወቅት የተለዩ ችግሮች እንደነበር አንስተዋል፡፡
በዘርፉ የሚስተዋሉ ችግሮችን በተቀመጠለት አሰራር እየገመገመ እርምጃ ከመውሰድ አኳያ የፖሊስ ማኔጅመንቱ ጉድለት እንዳለበትም ከንቲባው ተናግረዋል፡፡
የሰራዊቱ የረጅም ጊዜ ጥያቄ የነበረው የተለያዩ አልባሳትና ቁሳቁስ ውስንነት ችግርን ለመፍታት 14 ሚሊዮን ብር በመመደብ ግዥ መፈጸሙን የገለጹት ከንቲባው ከዚሁ የመብት ጥያቄ ጎን ለጎን የአመለካከት ለውጥ በማምጣት የስራ ድስፒሊንና ሞራልን በማጣመር ሙያዊ ግዴታን መወጣት እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡
የአዲሱ ክልል ምስረታ በቅርብ ጊዜ እንደሚከናወን የገለጹት አቶ ጥራቱ ወደ ከተማዋ የሚመጣውን የኢንቨስትመንት እና የቱሪስት ፍሰት በአግባቡ ለመጠቀም ሰራዊቱ ትልቅ ኃላፊነት አለበትም ብለዋል፡፡
ከሰራዊቱ ለቀረቡ የትምህርት እድል፣ የዘመናዊ ቴክኖሎጂ አቅርቦት፣ የመኖሪያ ቤት እና ሌሎች ጥያቄዎች ከመድረኩ ምላሽ ተሰጥቷል፡፡
በመድረኩም ባለፉት አራት ወራት የተሻለ የስራ አፈጻጸም ላስመዘገቡ የፖሊስ አባላት፣ የትራፊክ ፖሊሶች፣ክ/ከተሞች በየደረጃው ሰርተፍኬት የተሰጣቸው ሲሆን ልዩ የዋንጫ ተሸላሚዎች ዋንጫ ተቀብለው ለአባላቱ የተገዙ ቁሳቁሶችም ርክክብ ተደርጓል፡፡
ዜናው የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ህዝብ ግኙኝነት ነው
Comments
Post a Comment