ኢዜማ አሃዳውያንነትን ከውጭ፤ በውስጡ ግን አማራነትን እያቀነቀነ፤ በአማራ ህዝብ የማወደድ እና ባህር ዳር ከተማ ልያደርግ የነበረው ጉባኤ በቁጡ ፋኖዎች በጦር መሳሪያ በታገዘ ተቃውሞ የተባረረ ነው። ህዝቡና አመራሮቹ አንናበብም ባሉት የሀዋሳ ከተማ ግን፤ የብልጽግና ፓርቲ አጎባዳጅ የሲዳማ አመራሮች፤ ዶክተር አብይን ለማስደመም እና ወዳጆቹን ለማስደሰት ሲባል፤ የሲዳማ አባቶች በታላቁ ጉዱማሌ እንዳይሰበሰቡ በተከለከሉበት ሁኔታ ኢዜማ እንደፈለገ በሲዳማ እንዲፈነጭ እና የሲዳማን ህዝብ ከዚህ በፊት በኢሳት እና በሌሎች የሚዲያ አውታሮች እንዳልሰደበ እና እንዳላሳቀቀ ሁሉ፤ በአካል መጥተው ሲዳማን በግዛ ከተማው እንድሳደብ አድርገዋል።
ኢዜማ በሲዳማ ምድር ባለመብት ሆኖ መቅረቡ ሳያንስ በሁሉም የሲዳማ ወረዳዎች እንደሚሰራ እና እንዳለ ተነግሯል፤ መናገር ብቻ ሳይሆን በሀዋሳው ጉባኤ ላይ ከ36ቱም የሲዳማ ወረዳዎች የተወከሉ አባላቱ ተገኝተዋል።
እኛ ግን ሽማግሌውን የሲዳማ አርነት ንቅናቄ- ሲአንን ማጠናከር ወይም ሌላ አንድ አዲስ የፖለቲካ ፓርቲ ማቋቋም አቅቶን፤ ልሙጥ ባንድራ ባየን ቁጥር አይናችን ይቀላል እንላለን። ጠላቶቻችንን በከተማችን ጋብዘን በጎሮበቶቻችን ፊት እንሰደባለን፤ በገዛ ከተማችን እንዋረዳለን። ኢዜማ በየትኛውም ክልል ጉባኤ ማድረግ ያልቻለው እና በአከባቢው ነዋሪዎች የተከለከለው በምክኒያት መሆኑን የተረዳን አይመስልኝም። በተለይ የእኛ አመራሮች የተረዱ አይመስልም። ለሲዳማ እንደ ህዝብ መቀጠል ከመሰል አሃዳውያን ጋር መሻረክ አያዋጣውም።
ክልል ለመሆን የሰጠነው ድምጽ ቀለም ሳይደርቅ፤ በአሃዳውያን መዋጣችንን ልያረዱን ተዘጋጅተዋል። የሲዳማ ክልል ምስረታ ጊዜ የሚንሰጠው ጉዳይ አይደለም። ለሲዳማ ክልል የስልጣን ሽግግር ሁላችንም መነሳት አለብን!!
Comments
Post a Comment