ከዚህ በፊት የThe Irish Times የሚያወጣቸውን ዘገባዎች በፍቅር ነበር የማነበው። ዛሬ ግን ይዞ የወጣው ዘገባ አንጄቴን ነው የቆረጠው። ይህንን የሚያክል ጋዜጣ ግራ ቀኙን ሳያገናዝብ ፤ ይህንን መሰል ወደ አንድ ጎን ያደላ፤ እንዳውም ወደ አሃዳውያን ያደላ መረጃ እና ዘጋባ ይዞ ይወጣል የሚል እምነት መቼም አልነበረኝም። በሃዋሳ ከተማ ነዋሪ ጸረ ሲዳማ የሆኑ አንድ ግለሰብን አናግሮ፤ ስለ ሲዳማ ደግሞ ማንንም ሳያናግር ወደ አንድ ጎን ያጋደለ የጅምላ ፍረጃ ዘገባ ለአለም ህዝብ አቅርቧል።
የሲዳም ህዝብ ለ131 አመታት የታገለለትን ራስን በራስ የማስተዳደሩን ጉዳይ አገርን ከማፍረስ ጋር አያይዞ አቅርቧል። የሲዳማ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ መብት ይጠበቅ ማለቱን እንደስህተት፤ የሲዳማን ህዝብ ህገ መንግስታዊ እና ዴሞክራሲያዊ መብቶችን በፍጹም ዴምክራሲአያዊ መንገድ ለመፍታት የተከወነውን ህዝበ ውሳኔ ኣሄድን በማንሸሽ አቅርቧል። ለመሆኑ በፎቶው ላይ ያሉት ህንጻዎች ከህዝበ ውሳኔ ጋር ተያይዘው ነው ከጅምር የቀሩት? እንግዲህ እግዚዬር ያሳያችሁ ጋዜጣው ይህንን ነው የሚለው።
እኔ የተሰማኝን ጥቃት የሚገልጽበት ቃላት የሉኝም፤ ነገር ግን ዜናውን አንብባችሁ ለጻፊው ተገቢውን ምላሽ እንደምትስጡ እተማመናለሁ።
Comments
Post a Comment