Skip to main content

Posts

Showing posts from January, 2020

ኤጄቲማ ፌደራሊስት ፓርቲ- EFP ጊዜያዊ አስተባባሪዎች የተሰጠ መግለጫ

ከጊዜያዊ አስተባባሪዎች የተሰጠ መግለጫ የሲዳማ ህዝብ ላለፉት 130 ዓመታት ለብሄር ብሄረሰቦች እራስን በራስ የማስተዳደር መብትና ለሉኣላዊ የስልጣን ባለቤትነት እውን መሆን መራራ ትግል ሲያደርግ እንደቆየ ይታወቃል። አሁን ላይ ለረጅም ግዜ ሲደረግ የነበ ረው ትግል ወደ ወሳኝ የድል ምዕራፍ ተሸጋግሯል። የተገኘውን ድል ጠብቆና አድምቆ ለመሄድ የተደራጀና ህዝባዊ መሰረት ያለው ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ እንደሚያስፈልግ ግልጽ ነው። ሆኖም አሁን ያለው አከባቢያዊና ሀገራዊ የፖለቲካ እውነታ ህዝባችን እና ያገኘውን ድል የሚመጥን ከመሆን በተቃራኒ ህዝባችን በጠየቀው ጥያቄ እንዲሸማቀቅና ጥፋተኝነት እንዲሰማው በማድረግ ከፍተኛ የሆነ የብቀላ ወጥመድ እየተዘረጋ ያለበትን ሁኔታ አስተውለናል። ህዝባችንን ዳግም በጨለማ ለመወርወር እየተደረጉ ያሉ እንቅስቃሴዎች ከግዜ ወደ ግዜ መልካቸውንና መጠናቸውን እየቀየሩ በህዝባችን ላይ ከፍተኛ የሆነ የሞራል እና የስነ ልቦና ጫናዎችን እየፈጠሩ ቆይተዋል። ለአብነትም የሲዳማ ህዝብ ብዙ ዋጋ ከፍሎ ያገኘው በክልል የመደራጀት መብት የስልጣን ርክክብ እንዳይደረግና እንዲዘገይ ከዛም ባሻገር ከህዝባችን ፍላጎትና ውሳኔ ውጪ የሆነ ፖለቲካዊ መዋቅር ለመፍጠር እየተደረገ ያለው ሙከራ የዚህ ሴራ ማሳያ ነው። ከዚህም ባለፈ ህዝባችን ድል ሊያስጠብቅ የሚችለውን ህብረ ብሄራዊ ፌደራላዊና ህገ መንግስታዊ ስርዓትን አጠልሽቶ ለማሰናከል እየተደረገ ያለው ጥረት ይህ ነው የሚባል አይደለም። ለዚህ ሴራ ትግበራ ይሆን ዘንድ የሲዳማ ፖለቲካ ሊህቃኖችን፥አክቲቪስቶችን እና ጋዜጠኞች ላለፉት 7 ወራት ያለ ፍርድ በእስር እንዲሰቃዩ ተደርጎ የሚመሰረተውን የሲዳማ ክልል አቅም አልባና ደካማ አድርጎ ለማቅረብ የተኬደው ርቀት ከፍተኛ ነው። በህዝባችን ላይ እየተካሄደ

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 11ኛ ሳምንት ዛሬ በተደረገ ጨዋታ ሲዳማ ቡና ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲን አሸነፈ

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 11ኛ ሳምንት ዛሬ በተደረገ ጨዋታ ሲዳማ ቡና ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲን አሸነፈ። በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 11ኛ ሳምንት በሃዋሳ ከተማ ስታዲየም ዛሬ በተደረገ ጨዋታ ሲዳማ ቡና ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲን 5 ለ 0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል። የመጀመሪያዋን ጎል በ21ኛው ደቂቃ ላይ ሀብታሙ ገዛኸኝ ሲያስቆጥር፥ በ59 እና በ70ኛው ደቂቃ አዲስ ግደይ ኳሷን ከመረብ አገናኝቷል። በ66ኛው ደቂቃ ደግሞ ይገዙ ቦጋለ አራተኛውን ጎል ያስቆጠረ ሲሆን፥ በ69 ደቂቃ አበባየሁ ዮሐንስ የመጨረሻውን ጎል ማስቆጠር ችሏል። እስከ ጨዋታው ፍፃሜ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ግብ ሳያስቆጠር ቀርቷል። በዚህም ሲዳማ ቡና በ12 ነጥብ እና በ6 ጎል ሰባተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። ምንጭ 

የሲዳማ ዞን ለሲዳማ ክልል ምስረታ ስነ-ስርዕት (የክልል ምረቃ ድግስ) ዝግጅት እያካሄደ ነው

የሲዳማ ዞን ለሲዳማ ክልል ምስረታ ስነ-ስርዕት (የክልል ምረቃ ድግስ) ዝግጅት እያካሄደ ነው ************* (ጥር 20 ፣ 2012 ማለዳ ሚዲያ) የሲዳማ ህዝብ አስተዳደር በክልል ለመደራጀት የሚያስችለውን ቅድመ ዝግጅት እያጠናቀቀ መሆኑን በተደጋጋሚ ሲገልጽ ከርሟል። ከስልጣን ርክክቡ መዘግየት ጋር ተያይዞ በህዝቡ ዘንድ የተለያዩ ጥርጣሬዎች እየተነሱ ቢሆንም ዞኑ እያደረኩ ያለሁትን ዝግጅት የሚያስቆም አንዳች ነገር አልገጠመኝም በማለት በያዝነው ወር ማገባደጃ ርክክቡ ፍጻሜ አግኝቶ አዲሱ ክልል በይፋ እንደሚመረቅ በተደጋጋሚ ለህዝቡ ቃል እየገባ ነው። ክልል ሆኖ ለመደራጀት የሚያስፈልጉ የህግ የመዋቅርና መሰል ቅድመ ሁኔታዎች በመጠናቀቅ ላይ መሆናቸው ሲገለጽ የነበረ ሲሆን ከርክክቡ ጋር በተያያዘ የደቡብ ክልል ም/ቤት ስልጣኑን በደብዳቤ እንደሚያስረክብ በመርህ ደረጃ ከዞኑ ጋር መግባባት ላይ ተደርሶ የነበረ ቢሆንም እስካሁን ደብዳቤው ከደቡብ ክልል እንዳልወጣ ሚድያችን ባደረገው ማጣራት ማረጋገጥ ተችሏል። በያዝነው ወር መጨረሻ ይኖራል ተብሎ እየተጠበቀ ያለው የክልል ምረቃ ድግስ በብልጽግና ስብሰባ አማካኝነት ሊራዘም ይችላል የሚሉ ስጋቶች ቢበራከቱም ዞኑ ስለጉዳዩ የሰጠው ተለዋጭ ፍንጭ የለም። ማለዳ ሚድያ በዚህና መሰል ጉዳዮች ላይ ከሰሞኑ ጠለቅ ያሉ መረጃዎችን በማሰባሰብ ሰፊ ትንታኔ ይሰጥበታል። ዜናው የማለዳ ሚዲያ ነው 

ለክልል ምስረታ ተገቢ ዝግጅት እየተደረገ ነው

ለክልል ምስረታ ተገቢ ዝግጅት እየተደረገ ነው ህዳር 10 ቀን መላው ህዝባችን በሰጠው ድምጽ መሰረት የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስን ለማቋቋም ይሁንታ ያስገኘ ተግባርን እውን ማድረግ ተችሏል፡፡ ይህን ተከትሎም አዲሱን ክልላችንን መመስረት የሚያስችል ቅደም ተከተላዊ አደረጃጀትን ከነባሩ ክልል ጋር በመቀናጀት አስፈላጊው ሁሉ በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡ ከዚህ ጎን ለጎን ነባሩ ክልል አዲሰ ለሚመሰረተው የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ህጋዊ ርክክብ ማድረግ የሚያስችለውን አሰራር ዘርግቶ ተግባራዊ በማደረግ ላይም ይገኛል፡፡ በዚህም ይፋ የሚደረገው ክልላችን መላው ህዝባችን፣ ታላላቅ እና ታዋቂ ግለሰቦች በተገኙበት በታላቅ ድምቀት እውን ማድረግ እንዲቻል እያንዳንዱ አካሄድ በተጠና እና ቅንጅታዊ አሰራርን ባማከለ መልኩ ከዳር የሚያደርሱ የተቋቋሙ ኮሚቴዎች የበኩላቸውን እስተዋጾኦ እያበረከቱም እንደሆነ መግለጽ ይቻላል፡፡ በመሆኑም መላው ህዝባችን ህጋዊ አሰራርን እና ቅደም ተከተልን ጠብቆ እየተከናወነ ያለውን የክልላችንን የምስረታ በአንዳንድ ማህበራዊ ሚዲያዎች በተቀመጠው ቀን መሰረት አለመሆኑን እየጠቆምን ጊዜውን አስመልክቶ እና ያለው ሂደት የሚጠቁሙ መረጃዎችን ከተማ አስተዳደሩ በየጊዜው በገጹ ላይ ይፋ እንደሚያደርግ ይገልጻል፡፡ ስለሆነም ህዝባችን ከዚህ ቀደም ያደርግ እንደነበረው ሁሉ ቀኑን በሰከነ ሁኔታ እና በትዕግስት እንዲጠብቅ አስተዳደሩ በዚህ አጋጣሚ ጥሪውን ያቀርባል፡፡ Source

የአንበጣ መንጋ ክስተት ከተስተዋለ ብኋላ ህብረተሰቡ እየወሰደ ያለው የጥንቃቄ እርምጃ የሚደነቅ መሆኑን የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ገለፀ

የአንበጣ መንጋ ክስተት ከተስተዋለ ብኋላ ህብረተሰቡ እየወሰደ ያለው የጥንቃቄ እርምጃ የሚደነቅ መሆኑን የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ገለፀ፡፡ እንደከተማ የአንበጣ መንጋው ተበታትኖ በሶስት አቅጣጫ የታየ መሆኑ የከፋ ጉዳት እንዳያስከትል ያግዛል ያሉት አቶ ፍቅረየሱስ አሸናፊ የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ግብርና መምሪያ ኃላፊ ናቸው፡፡ ይሁንና መንጋውን ለማባረር ነዋሪው በሚያደርገው ያላሰለሰ እንቅስቃሴ ከከተማ እንዲወጣ ካልተደረገ የከፋ ጉዳት የሚያስከትል መሆኑን አቶ ፍቅረየሱስ ጨምረው ገልፀዋል፡፡ ንፋስ የሌለ መሆኑ መንጋው የንፋሱን አቅጣጫ ተከትሎ እንዲወጣ ንፋሱን ተከትሎ ጭስ ማጨስ እና ድምፅ ማሰማት አለመቻሉ በዚህም በዚያም ጭስ ማጨሱ እና ድምፅ የማውጣት ስራ መሰራቱ አስቸጋሪ ያደረገው መሆኑን ጨምረው ገልፀዋል፡፡ ለሰው እና ለእንስሳት እንዲሁም ለከተማ ግብርና ስራ የሚመከር ባለመሆኑ የኬሚካል ርጭት ማድረግ ቀላል አለመሆኑን የገለፁት አቶ ፍቅረየሱስ ህብረተሰቡ በሚያደርገው ጥረት መንጋውን ማባረር ካልተቻለ በተኩስ የሚሞከር መሆኑን ነው አቶ ፍቅረየሱስ ጨምረው የገልፁት፡፡ በተለይ በከተማ አካባቢ ከፍተኛ የሆነ የሰው እንቅስቃሴ ያለ በመሆኑ የአንበጣ መንጋውን በጪስ እና በተለያየ መንገድ ለማባራር ሙከራ እየተደረገ መሆኑ የሚበረታታ መሆኑን አቶ መልካሙ ተፈራ የከተማ አስተዳደሩ ህዝብ ግንኙነት ጽ/ቤት ኃላፊ ገልፀዋል፡፡ የሰዎች እንቅስቃሴ የሌለባቸው አካባቢዎች በተለይ እንደ ጉዱማሌ ፓርክ፣ ሚሊኒየም ፓርክ እና ሌሎች ስፋት ያላቸው እና የሰዎች እንቅስቃሴ የማይታይባቸው አካባቢዎች ላይም ትኩረት መስጠት እንደሚገባ ነው አቶ መልካሙ ጨምረው የገለፁት፡፡ በሌላ በኩል አንበጣውን ለማባረር በሚደረገው ጥረት ጭስ ለማጨስ የሚለኮስ እሳት ሌላ አደጋ

በሀዋሳ ከተማ እንዳንድ አካባቢዎች የአንበጣ መንጋ ክስተት ማምሻውን ተስተዋለ

በሀዋሳ ከተማ እንዳንድ አካባቢዎች የአንበጣ መንጋ ክስተት ማምሻውን ተስተዋለ፡፡ የአንበጣ መንጋ ክስተቱን ለመከላከል መንጋው በተስተዋለባቸው አካባቢዎች የከተማዋ ነዋሪዎቸች ጭስ ማጬስን እና ድምፅ ማሰማትን በአማራጭነት እየተጠቀሙ ይገኛል። በአሁን ሰዓት በከተማዋ ሰማይ ላይ ጭስ እየተስተዋለ ሲሆን ለአንበጣ ተብሎ የተለኮሰ እሳት ሌላ ጥፋት እንዳያስከትል ትልቅ ጥንቃቄ ማድረግ ተገቢ ነው። ህብረተሰቡ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲያደርግ ከተማ አስተዳደሩ ጥሪውን ያቀርባል። Source

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በአጭር ጊዜ ውስጥ በአዲስ ክልል መመስረት የሚያስችለውን ዝግጅት አጠናቀቀ

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በአጭር ጊዜ ውስጥ በአዲስ ክልል መመስረት የሚያስችለውን ዝግጅት አጠናቀቀ፡፡ የሲዳማ ብሔር ለመብቱ እና ለነጻነቱ ሲታገል የህይወት እና አካላዊ መስእዋትነትን በመክፈል ጭምር ትግል ማድረጉ ለምዕተ ዓመት እና ከዚያም በላይ መታገሉ የሚታወቅ ነው፡፡ ይህ ብሄሩ ያለማቋረጥ ያደረገው ትግል ዛሬ ላይ የታየውን ድል ለመጎናጸፍ ታጋሽ በመሆን ጭምር ዋጋ የከፈለበትም ሆኖ ይገኛል፡፡ በዚህም ህዳር 10 ቀን 2012 ዓ/ም ህዝበ ውሳኔ ምርጫ ሲያካሂድ ወጣቶች፣ እናቶች፣አባቶችና አዛውንቶች ሳይቀሩ በነቂስ ወጥተው ነጻ፣ ፍትሀዊና ሰላማዊ ምርጫ ሲያካሂዱ ሂደቱ ለዓለም ትልቅ ትምህርት የሚሰጥና ድንቅ የሚባል ነበር፡፡ ይህንኑን ምስረታ እውን ለማድረግም ትግሉን የሚመጥን ዝግጅት እንዲያደርጉ ትልቅ ተልዕኮ የተሰጣቸው ኮሚቴዎች የተቋቋሙ ሲሆን እያንዳንዱ ኮሚቴም ስራውን በተገቢው መልኩ ያጠናቀቀ መሆኑን ስንገልጽ ህዝባችን ለምስረታው ዕለት ሲዳማ ብሄር መገለጫ የሆኑ ዝግጅቶችን በማድረግ እንድጠብቁን በመጠቆም ነው። Source

Urgent!

Report: A highflying desert locust swarm is being sighted in Alatta Chuko, AlattaWondo, Yirgalem by now. Destination could be the highlands of Wonsho, Gorche, Arbegona, Malaga or even Wondo Genet. Share this message, alert the people on the ground.  Thank you !

ለሶስተኛ ዙር የልማት ተነሺዎች ምትክ ቦታ በእጣ የማስተላለፍ ስራ ተከናወነ

በሀዋሳ ከተማ አስተዳደር በአካባቢ የልማት ጥናት መሰረት በዩኤልዲፒ የልማት ስራ ለሁለት ዙር ተነሺዎች ምትክ ቦታ በእጣ የማስተላለፍ ስራ እንደተሰራ ይታወቃል፡፡ በዛሬው እለትም ለሶስተኛ ዙር በታቦር ክ/ከተማ ፋራ ቀበሌ በመንገድ ልማት ተነሺ ለሆኑ 122 ነባር ባለይዞታዎች በዶሮ እርባታ አካባቢ በተዘጋጀ መሬት እንደየ መሬት ይዞታቸው በዕጣ በመለየት ምትክ ቦታ የማስተላፉ ስራ ተከናወኗል፡፡ እስከ አሁን ለ240 ነባር ባለይዞታ አርሶ አደሮች ምትክ ቦታ የተሰጣቸው ሲሆን በአጠቃላይ 1136 ተነሺዎችን ከሁለት ወር ባነሰ ጊዜ ውስጥ በተዘጋጀላቸው ቦታ በማሳረፍ ሙሉ በሙሉ የመንገድ ከፈታ ስራዎችን በመስራት የህብረተቡን የልማት ጥያቄ ለመመለስ ከተማ አስተዳደሩ እየሰራ መሆኑን የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ጥራቱ በየነ ተናግረዋል፡፡ አቶ ጥራቱ ከዚህ ቀደም በተላለፉ ቦታዎች አካባቢ የተከናወኑ ተግባራትን በስፍራው ተዘዋውረው የጎበኙ ሲሆን ልማቱን ሊያፋጥኑ የሚችሉ አሰራሮች እንደሚተገበሩም ተናግረዋል፡፡ በከተማዋ በጎርፍ ምክንያት የሚስተዋለውን ችግር ለመቅረፍ በዋርካ ሆቴል እና በሳውዝ ስታር አካባቢ የተጀመሩ የጎርፍ ውሃ መውረጃ ቦዮች በተፈለገው ፍጥነት ያልተጓዘ መሆኑን የተናገሩት ከንቲባ አቶ ጥራቱ ችግሩን በዘላቂነት ለመቅረፍ ህብረተሰቡ መታገስ እንደሚገባም ተናግረዋል፡፡ በከተማዋ የሀዌላ ቱላ ክ/ከተማን ጨምሮ የመንገድ፣ የመብራት፣የውሃ፣ሙያ ማሰልጠኛ ተቋም፣ የጎዳና ልጆችን በማሰልጠን እና ሌሎች መልካም አስተዳደር እና የልማት ስራዎች ላይ ከተማ አስተዳደሩ በየደረጃው ለማከናወን በበጀት ተደግፎ ተግባራት መጀመሩን ተናግረዋል፡፡ በመንግስት ተቋማት ውስጥ ያሉ ብልሹ አሰራሮችን ለማስወገድም የተለያዩ ማስተካከያዎች መደረጉን የተናገሩት አቶ

ከሲዳማ ኤጄቶ የተሰጠ አስቸኳይ መግለጫ

የሲዳማ ህዝብ ለዘመናት ባደረገው እልህ አስጨራሽ ትግል እና በከፈለው ውድ መስዋትነት ፍሬ እራስን በእራስ የማስተዳደር መብቱን በህዳር 10/2012 ዓ.ም በተካሄደው እና ከ2.3 ሚልዮን በላይ መራጮች ተሳትፈውበት ከ98/100 በላይ ይሁንታን በሰጡበት ህዝበ-ውሳኔ አማካኝነት በድል ማጠናቀቁ ይታወቃል። ምንም እንኳን ለዚህ ጣፋጭ ድል ለመብቃት ያሳለፈነው ጉዞ እጅግ መራራ ቢሆንም ክብር እና ምስጋና በትግሉ ወቅት ለተሰዉ ታጋይ ሰማዕታት ይሁንና ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲተላለፍ የመጣውን የአደራ እዳ ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ እንዲቋጭ አድርገናል። በህዝቡ ህገመንግስታዊ ጥያቄ እና ህገመንግስቱን ተከትሎ ጥያቄውን ለማስመለስ ሲያካሂድ በነበረው ሰላማዊ የትግል አካሄድ ላይ በመንግስት በኩል በተፈጸመ ኢ-ህገመንግ ስታዊ የፖለቲካዊ ደባ ምክንያት ከ140 የሚልቁ ንጽሀን የሲዳማ ተወላጆች ህይወት መቀጠፉ የቅርብ ጊዜ ትዝታችን ነው። "ለህገመንግስታዊ ጥያቄያችን ህገመንግስታዊ ምላሽ ብቻ እናሻለን" በሚል መርህ ሲካሄድ በነበረው ሰላማዊ ትግል ወቅት ላይ ከህገመንግስቱ ድንጋጌ እና አካሄድ ውጪ በሆነ መልኩ ከመንግስት በኩል የቀረቡ አማራጭ የፖለቲካ ውሳኔዎችን አምርረን መቃወማችን ይታወሳል። ይሁንና ህዝቡ ባደረገው ተቃውሞ እና በከፈለው መስዋትነት የብሄሩ እራስን በእራስ የማስተዳደር ጥያቄ ህገመንግስቱ በምያዘው መልኩ ከሁለት ወራት በፊት በተካሄደው ህዝበ-ውሳኔ ክልል ለመሆን የሚያስችለንን ድምጽ በማግኘት ያጠናቀቅን ቢሆንም የህዝበ-ውሳኔው ውጤት ከተገለጸበት ጊዜ ጀምሮ በደቡብ ክልል መንግስት እና በሲዳማ ክልል መካከል መደረግ የነበረበት የስልጣን ርክክብ ሳይካሄድ ቆይቷል።ህዝቡ ይህን የመንግስት ዝግመታዊ የሴራ አካሄድ በጥርጣሬ በመመልከት ባስቸኳይ የ

ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ ከደቡብ ክልል ከተውጣጡ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ጥር 14 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከደቡብ ክልል ከተውጣጡ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር ተወያይተዋል። በጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት እየተካሄደ ባለው ውይይት ከ2 ሺህ የሚበልጡ ተወካዮች ተሳታፊዎች ናቸው። ከሁሉም የክልሉ ዞኖች የተውጣጡ ምሁራን፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሀይማኖት አባቶች እና የወጣት ተወካዮች በውይይት መድረኩ ላይ ተሳትፈዋል። በውይይቱ ላይ ተሳታፊዎቹ በክልል መደራጀት ጋር የተያያዙ ጥያቄዎችን ለጠቅላይ ሚኒስትሩ አቅርበዋል። እንዲሁም ከመሰረተ ልማት ጋር ተያይዞ የመንገድ ችግር እንዳለ፤ የጤና ተቋማት በበቂ ሁኔታ አለመኖር፣ የጤና ባለሙያዎች እና የመድሃኒት እጥረት እንዲሁም ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ባልተዳረሰባቸው ዞኖችም ተቋማቱ እንዲገነቡ ጥያቄዎች ቀርበዋል። በተጨማሪም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እስካሁን ወዳልሄዱባቸው ዞኖች ሄደው ከህዝብ ጋር ለምን አልተወያዩም የሚል ጥያቄም ቀርቧል። በሀገሪቱ አልፎ አልፎ የሚፈጠሩ ችግሮችን በመቅረፍ ዘላቂ ሰላም ለማምጣት መሰራት አለበት ባሉት ጉዳይ ላይም ሃሳብ አንስተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሰጡት ምላሽ፥ ከሰላም እጦት ጋር ተያይዞ ለሚነሱ ጥያቄዎች ተነጋግሮ መፍትሄ የማበጀት ስራ ይሰራል ብለዋል። ከመሰረተ ልማት ጋር እና ከመልካም አስተዳደር እጦት ጋር ተያይዘው ለቀረቡ ጥያቄዎችም አንድ የጋራ ኮሚቴ በማዋቀር ታች ድረስ ዘልቆ ችግሮችን በመለየት ዘላቂ መፍትሄ ለማምጣት እንደሚሰራም ነው የገለፁት። በክልል ከመደራጀት ጋር ተያይዞ ለተነሱ ጥያቄዎችም፥ በክልል ከመደራጀት ጋር ተያይዘው ለሚነሱ ጥያቄዎች በአንድ መድረክ ላይ መልስ መስጠት እንደማይቻል አስረድተዋል። ነገር ግን የሀገርን አንድነት እና የዜጎ

የሚኒስትሮች ም/ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 78ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ

ምክር ቤቱ ውሳኔ ያሳለፈባቸው ጉዳዮችም እንደሚከተለው ቀርበዋል፦ 1. ምክር ቤቱ በቅድሚያ የተወያየው የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤትን ህጋዊ ሰውነት ለመስጠት በተዘጋጀው ረቂቅ አዋጅ ላይ ነው፡፡የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት ህጋዊ ሰውነት እንዲኖረው በቀረበው ረቂቅ አዋጅ ላይ ተወያይቶ ህጋዊ ሰውነት እንዲሰጠው በሙሉ ድምጽ በመወሰን ረቂቅ አዋጁ ይጸድቅ ዘንድ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ ወስኗል፡፡ 2. በመቀጠል ምክር ቤቱ የተወያየው የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ምርምርና ልማት ማዕከል ማቋቋሚያ ረቂቅ ደንብ ላይ ነው፡፡ በዚህም ሀገራዊ ጥቅምን ለማስጠበቅ የሚያስችሉ በምርምር፣ ልማት እና ትግበራ የተመሰረቱ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ አገልግሎቶች፣ ምርቶች እና መፍትሄዎችን መስጠትና የልህቀት ማዕከል ማቋቋም በማስፈለጉ እና በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ዙሪያ ላይ ለሚሰሩ ጀማሪ አልሚዎች ምቹ ምህዳር መፍጠር የሚያስችል ረቂቅ ደንብ ለሚኒስትሮች ም/ቤት ውሳኔ አቅርቧል፡፡ ምክር ቤቱም በቀረበው ረቂቅ ደንብ ላይ ከተወያየ በኋላ ተቀባይነት ስላገኘ ደንቡ በነጋሪት ጋዜጣ እንዲወጣና በስራ ላይ እንዲውል ወስኗል፡፡ 3. የሲቪል አቪዬሽን አዋጅን ለማሻሻል የተዘጋጀ ረቂቅ አዋጅ ሌላው በምክር ቤቱ የታዬ ጉዳይ ነው፡፡ነባሩ የማስፈጸሚያ አዋጅ በቆየባቸው የትግበራ ዓመታት ውስጥ በህግ ያልተሸፈኑ አዳዲስ አስተሳሰቦች እና የቁጥጥር ስርአቶች በመኖራቸው የሰው ሀብት ስምሪትና የተፈላጊ ብቃት ተለዋዋጭነት መኖሩ በተለይም ከዘርፉ ልዩ የስራ ባህሪ አንጻር የአቬዬሽን ዘርፉን ለመምራት እና ለመቆጣጠር፣ የበረራ ደህንነትን ለማረጋገጥ እና የአደጋ ስጋትን ለመቀነስ አለማቀፍ ድርጅቱ በየጊዜው የሚያወጣቸው ምክረ ሀሳቦች፣ ደረጃዎችና የተመረጡ አሰ

መቀመጫውን በሀዋሳ ከተማ ያደረገው ኢፓርኬ የሁለንተናዊ ብቃት ማበልጸጊያና የስልጠና ማዕከል በራዕይና በእይታ ቅኝት ዙሪያ የማነቃቂያ ስልጠና ሰጠ

መቀመጫውን በሀዋሳ ከተማ ያደረገው ኢፓርኬ የሁለንተናዊ ብቃት ማበልጸጊያና የስልጠና ማዕከል በራዕይና በእይታ ቅኝት ዙሪያ የማነቃቂያ ስልጠና ሰጠ፡፡ በ 3 ዋና ዋና አርዕስቶች ማለትም፤በራዕይና በራዕይ ተግዳሮቶች፡ በአላማ ጽናት እንዲሁም በዕይታ ቅኝት ዙሪያ በተሰጠው ስልጠና ላይ በከተማው በተለያዩ ተቋማት በመሪነት ላይ የሚገኙ ግለሰቦች፤ ወጣት ነጋዴዎች እንዲሁም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ተገኝተዋል፡፡ የኢፓርኬ ስልጠና ማዕከል መስራችና ስራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ አራርሶ ገረመው እንደገለጹት ስልጠናው አላማና ራዕይ ያለውን ዜጋ ከማብቃት ባለፈ ወጣቶች በነገሮች ሳይሰናከሉ አርቀውና አስፍተው ማየት እንዲችሉ፤ ብቃታቸውን ማሳደግ እንዲችሉ፤ ስለ ሀገርና ዜጋ ማሰብ እንዲችሉ፤ ውስጣዊ አቅማቸውን ተጠቅመው አላማቸውን ማሳካት እንዲችሉ እንዲሁም ህይወ ታቸውን በአግባቡ መምራት እንዲችሉ ከማገዝ አንጻር ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው አስረድተዋል፡፡ የዕለቱ የክብር እንግዳና የሀዋሳ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ከተማ ዶባ በበኩላቸው ወጣቱን ማዕከል ባደረገው የከተማው ሁለንተናዊ የልማት እንቅስቃሴ ላይ መሰል ስልጠናዎች የሚኖራቸው ፋይዳ የጎላ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ይህንንም መሰረት በማድረግ የከተማ አስተዳደሩ ከኢፓርኬና መሰል ተግባራት ላይ ከተሰማሩ ድርጅቶች ጎን በመቆም ማንኛውንም ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን አቶ ከተማ ጨምረው ገልጸዋል፡፡ የሀዋሳ ከተማ ህዝብ ግንኙነት ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ መልካሙ ተፈራ በበኩላቸው ወጣቱን መሰረት ያደረጉ የኢፓርኬን አጠቃላይ እንቅስቃሴዎች በማድነቅ በበኩላቸው ማንኛውንም ድጋፍ ለማድረግ ፈቃደኛ መሆናቸውን አሳውቀዋል፡፡ አክለውም ወጣቶችና ሌሎች የስልጠናው ተካፋዮች ከስልጠናው ያገኙትን ትምህርት

እንደ አዲስ ዘመን ያሉ ጋዜጦች እየገረቡ እንደሚያወጡት ዜና ሳይሆን፤ የሲዳማን ክልል ምስረታ ለማብረስ ጥቂት ሳምንታት ብቻ መቅረታቸው ተገለጸ

የሲዳማ ዞን አስተዳደር የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ትላንት ወዲያ ባስነበበው ጋዜጣና በተለያዩ መጽሔቶች የሲዳማ አስተዳደር ዋና አስተዳዳሪ ከአቶ ደስታ ሌዳሞ ጋር የተደረገው ቃለ-ምልልስ ከአንድ ወር በፊት የተደረገ መሆኑንና በዚህ ሣምንት ውስጥ የተደረገ አለመሆኑን የሲዳማ አስተዳደር ህ/ግ/ ጽ/ቤት ገልጿል፡፡ አያይዞም፤ በተለይ የሲዳማ አዲሱ ክልል ምስረታ በተመለከተ መጽሔቱ የዞ የወጣው ከወር በፊት የተደረገውን ቃለ-ምልልስ መሆኑን በድጋሚ በመግለፅ በአንዳንድ ሶሻል ሚዲያዎች ሁለት አይነት ሀሳብ በአንድ ጊዜ እንደተላለፈ ተደርጎ በመውሰድ ግሪታ ውስጥ የመግባት አይነት አዝማሚያዎች በመኖራቸው ውድ የሲዳማ ህዝብና የህዝባችን ወዳጆች በሙሉ ምስረታው በአንድ ወር ውስጥ ለመጨረስ በቂ ዝግጅት በማድረግ ላይ መሆናችንን ስንገልፅላችሁ በታላቅ ደስታ ነው ብሏል፡፡ ዛሬ ላይ የወጡ አንዳንድ የሲዳማ ክልል ምስረታን የሚያመለክቱ ዜናዎች እንደሚያሳዩት፤ የሲዳማ ክልል ምስረታ በሚቀጥሉት ሁለት ሳምንታት ውስጥ ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል።

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ምስረታ በአጭር ጊዜ ውስጥ አውን ማድረግ የሚያስችል ስራ እየተከናወነ ይገኛል

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ምስረታ በአጭር ጊዜ ውስጥ አውን ማድረግ የሚያስችል ስራ እየተከናወነ ይገኛል፡፡ ለምዕተ አመትና ከዚያ በላይ የሲዳማ ብሔር ለመብቱ እና ነጻነቱ የህይወት እና አካላዊ መስዋዕትነትን በመክፈል ትግል ማድረጉ የሚታወቅ ነው፡፡ በዚህም ጥቂት የማይባሉ የብሔሩ ተወላጆች ከአጼው ዘመን ጀምሮ እስከ ኢህአዲግ አገዛዝ ድረስ በተደራጀ እና ባልተደራጀ መልኩ ኢፍትሀዊነትን እና አንባገነንነትን በመታገል ጭምር የበኩላቸውን ድርሻ መወጣት ችለዋል፡፡ ይህ ከሀገር አልፎ በጎረቤት ሀገር ሞቃዲሾ ሳይቀር ወታደራዊ ትግልን በተደራጀ መልኩ በማድረግ ጭምር አስፈላጊውን የነጻነት ታጋዮችን በማጠናከር ትግሉን ያለማቋርጥ ያደረገው የሲዳማ ብሔር ዛሬ ላይ የታየውን ድል ለመጎናጸፍ ያላሰለሰ ጥረቱ ሆኖም ይገኛል፡፡ ከዚህ ጎን ለጎንም የብሔሩ ምሁራን እና አክቲቪስቶች በተመሳሳይ መልኩ በሀገር ውስጥም ሆነ ከሀገር ውጭ የፖለቲካዊ የዲፕሎማሲ አማራጮችንም ሆነ ነጻ የሆኑ ትግሎችን በማቀጣጠል የበኩላቸውን መወጣት ችለዋል፡፡ በዚህ አይነት መልኩ ከዳር ይደርስ ዘንድ ዋጋ የተከፈለበት ይህ የብሔራችን ትግል በርካቶች መስዋዕት የሆኑበት እና በርካቶች ደግሞ አካላዊም ሆነ ስነ ልቦናዊ ማቅ እስከመልበስ ያላሰለሰ ጥረት ያደረጉበት እንደሆነ ሊታወቅ ይገባል፡፡ ለሀገራችን ጭምር አዲስ የትግል እሳቤን በማከል እንዲሁም ለህብረ ብሔራዊ ፌድራላዊ ስርዓታችን መጎልበት አዲስ ምዕራፍ እስከመሆን በደረሰ መልኩ ህዳር 10 ቀን 2012 ዓ.ም ነጻ፣ ፍትሀዊ እና ሁሉን አቀፍ የሆነ ህዝበ ውሳኔን ማረጋገጥ ያስቻለ ምርጫ ማካሄዳችን ይታወቃል፡፡ በዚህም መላው የሀገራችን ህዝቦች፣ ታላላቅ የሀገር ውስጥ እና የውጭ ሀገራት ሚዲያዎች ሳይቀሩ በግልጽ እውቅና የቸሩ

Odoo kanchafare!

Odoo kanchafare! Daganke halante assitinno jawa sharronni sidaami gashshoote e'no kanchafari wo'muni wo'ma wo'ma sidaamu gashshoote agure ba'nota halaalanya bu'ewini macciishinoommo. Wole widoonino agure fulasi de'ne xaate didaano yine dese'e yinanitano dikkitinno. Korkaatuno bubbisi widira hige buuwate akati noosihuraati. Wole hige bubbisiro gantummo,ninke hige bubbisiro hige daara dandaannohura. Qorophote geeshshira Geediote widoo noohuno daara dandaano yitanno huluulono dibainno. Techcho kayi Tuula Hawaasiha jawa sinu quchchuma eino yine manna hembeelisinitino kapho ikkase buuxate dandiinoommo. Xaate kanchafaru sidaamira horo higoonke. Higeno ta'moonke! Odoonke buichcho Sidaamu gashshooti latishshu biddiishshi sooreesi kalaa Kaasu Arusihuwinniiti. ዜናው የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ህዝብ ግኙኝነት ነው

የከተማዋን ደህንነት በማስጠበቅ ህብረተሰቡን በእኩል መልኩ ለማገልገል ከመቼውም ጊዜ በላይ መዘጋጀታቸውን የሀዋሳ ከተማ ፖሊስ አባላት ገለጹ

የከተማዋን ደህንነት በማስጠበቅ ህብረተሰቡን በእኩል መልኩ ለማገልገል ከመቼውም ጊዜ በላይ መዘጋጀታቸውን የሀዋሳ ከተማ ፖሊስ አባላት ገለጹ፡፡ አባላቱ ይህንን የገለጹት ለሶስት ቀናት ባካሄዱት የስራ አፈጻጸም ግምገማ ማጠቃለያ መድረክ ላይ ነው፡፡ ሰራዊቱ ባሳለፈው የስራ ጊዜያት ውስጥ የነበረ ቡድንተኝነት የስራ ሞራላቸውን የነካ እንደሆነ ገልጸው አሁን እየተፈጠረ ባለው ግልጸኝነት እጅግ መደሰታቸውን ሲናገሩ ህብረተሰቡን በቁርጠኝነት ለማገልገል ምንም አይነት እንቅፋት እንደማኖር በመተማመን ነው፡፡ በአንዳንድ አባላት በሚስተዋሉ የስነ ምግባር ችግሮች በህብረተሰቡ ዘንድ አሜኔታ እንድናጣ ሆነናል ያሉት አባላቱ ውስጣዊ ችግሮቻችንን የሚፈታ አመራር በማግኘታችን የስራ ሞራላችን ከፍ ብሏልም ብለዋል፡፡ የሰራዊት አባላቱ አክለውም ህግን ከማክበርና ከማስከበር አንጻር ትኩረት ሰጥተው ለመስራትና ህብረተሰቡን ለመካስም ጭምር መዘጋጀታቸውን ነው የተናገሩት፡፡ ከጥቂት ወራት በፊት ባለፈው የሪፍረንደም ወቅት እና የገብርኤል መንፈሳዊ በዓል በሰላም መጠናቀቅ የሰራዊቱ ሚና ከፍተኛ እንደነበር የተናገሩት የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ጥራቱ በየነ ናቸው፡፡ አቶ ጥራቱ አክለውም አንዳንድ የሰራዊቱ አባላት ህብረተሰቡን በእኩል ከማገልገል አንጻር፣ በጥቅማ ጥቅም መደለል፣ቡድንተኛ መሆን፣ሙያዊ ስነምግባርን በመዘንጋት እና በሌሎች ምክንያቶች ኃላፊነታቸውን እንዳልተወጡ በግምገመው ወቅት የተለዩ ችግሮች እንደነበር አንስተዋል፡፡ በዘርፉ የሚስተዋሉ ችግሮችን በተቀመጠለት አሰራር እየገመገመ እርምጃ ከመውሰድ አኳያ የፖሊስ ማኔጅመንቱ ጉድለት እንዳለበትም ከንቲባው ተናግረዋል፡፡ የሰራዊቱ የረጅም ጊዜ ጥያቄ የነበረው የተለያዩ አልባሳትና ቁሳቁስ ውስንነት ችግርን ለመፍታ

ጊዜው አዲስ የሲዳማ ፓርቲ ማቋቋሚያ ነው

ኢዜማ አሃዳውያንነትን ከውጭ፤ በውስጡ ግን አማራነትን እያቀነቀነ፤ በአማራ ህዝብ የማወደድ እና ባህር ዳር ከተማ ልያደርግ የነበረው ጉባኤ በቁጡ ፋኖዎች በጦር መሳሪያ በታገዘ ተቃውሞ የተባረረ ነው። ህዝቡና አመራሮቹ አንናበብም ባሉት የሀዋሳ ከተማ ግን፤ የብልጽግና ፓርቲ አጎባዳጅ የሲዳማ አመራሮች፤ ዶክተር አብይን ለማስደመም እና ወዳጆቹን ለማስደሰት ሲባል፤ የሲዳማ አባቶች በታላቁ ጉዱማሌ እንዳይሰበሰቡ በተከለከሉበት ሁኔታ ኢዜማ እንደፈለገ በሲዳማ እንዲፈነጭ እና የሲዳማን ህዝብ ከዚህ በፊት በኢሳት እና በሌሎች የሚዲያ አውታሮች እንዳልሰደበ እና እንዳላሳቀቀ ሁሉ፤ በአካል መጥተው ሲዳማን በግዛ ከተማው እንድሳደብ አድርገዋል። ኢዜማ በሲዳማ ምድር ባለመብት ሆኖ መቅረቡ ሳያንስ በሁሉም የሲዳማ ወረዳዎች እንደሚሰራ እና እንዳለ ተነግሯል፤ መናገር ብቻ ሳይሆን በሀዋሳው ጉባኤ ላይ ከ36ቱም የሲዳማ ወረዳዎች የተወከሉ አባላቱ ተገኝተዋል። እኛ ግን ሽማግሌውን የሲዳማ አርነት ንቅናቄ- ሲአንን ማጠናከር ወይም ሌላ አንድ አዲስ የፖለቲካ ፓርቲ ማቋቋም አቅቶን፤ ልሙጥ ባንድራ ባየን ቁጥር አይናችን ይቀላል እንላለን። ጠላቶቻችንን በከተማችን ጋብዘን በጎሮበቶቻችን ፊት እንሰደባለን፤ በገዛ ከተማችን እንዋረዳለን። ኢዜማ በየትኛውም ክልል ጉባኤ ማድረግ ያልቻለው እና በአከባቢው ነዋሪዎች የተከለከለው በምክኒያት መሆኑን የተረዳን አይመስልኝም። በተለይ የእኛ አመራሮች የተረዱ አይመስልም። ለሲዳማ እንደ ህዝብ መቀጠል ከመሰል አሃዳውያን ጋር መሻረክ አያዋጣውም። ክልል ለመሆን የሰጠነው ድምጽ ቀለም ሳይደርቅ፤ በአሃዳውያን መዋጣችንን ልያረዱን ተዘጋጅተዋል። የሲዳማ ክልል ምስረታ ጊዜ የሚንሰጠው ጉዳይ አይደለም። ለሲዳማ ክልል የስልጣን ሽግግር ሁ

#WaltaTV:የዘመናት ትግል የሲዳማ ሕዝብ ክፍል አንድ

ጫፍ የረገጠ ዘ አይርሽ ታይም ዘጋባ በሲዳማ ላይ

ከዚህ በፊት የThe Irish Times የሚያወጣቸውን ዘገባዎች በፍቅር ነበር የማነበው። ዛሬ ግን ይዞ የወጣው ዘገባ አንጄቴን ነው የቆረጠው። ይህንን የሚያክል ጋዜጣ ግራ ቀኙን ሳያገናዝብ ፤ ይህንን መሰል ወደ አንድ ጎን ያደላ፤ እንዳውም ወደ አሃዳውያን ያደላ መረጃ እና ዘጋባ ይዞ ይወጣል የሚል እምነት መቼም አልነበረኝም። በሃዋሳ ከተማ ነዋሪ ጸረ ሲዳማ የሆኑ አንድ ግለሰብን አናግሮ፤ ስለ ሲዳማ ደግሞ ማንንም ሳያናግር ወደ አንድ ጎን ያጋደለ የጅምላ ፍረጃ ዘገባ ለአለም ህዝብ አቅርቧል። የሲዳም ህዝብ ለ131 አመታት የታገለለትን ራስን በራስ የማስተዳደሩን ጉዳይ አገርን ከማፍረስ ጋር አያይዞ አቅርቧል። የሲዳማ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ መብት ይጠበቅ ማለቱን እንደስህተት፤ የሲዳማን ህዝብ ህገ መንግስታዊ እና ዴሞክራሲያዊ መብቶችን በፍጹም ዴምክራሲአያዊ መንገድ ለመፍታት የተከወነውን ህዝበ ውሳኔ ኣሄድን በማንሸሽ አቅርቧል። ለመሆኑ በፎቶው ላይ ያሉት ህንጻዎች ከህዝበ ውሳኔ ጋር ተያይዘው ነው ከጅምር የቀሩት? እንግዲህ እግዚዬር ያሳያችሁ ጋዜጣው ይህንን ነው የሚለው። እኔ የተሰማኝን ጥቃት የሚገልጽበት ቃላት የሉኝም፤ ነገር ግን ዜናውን አንብባችሁ ለጻፊው ተገቢውን ምላሽ እንደምትስጡ እተማመናለሁ። ዜናውን ከሊንኩ ላይ ያንቡ፡

‹‹የሲዳማ ክልል የሚመራበት ህገ መንግስት በረቂቅ ደረጃ ተጠናቋል››አቶ ደስታ ሌዳሞ የሲዳማ ዞን ዋና አስተዳዳሪ

ሐዋሳ፡- ‹‹የሲዳማ ክልል የሚመራበት ህገ መንግስት በረቂቅ ደረጃ ተጠናቋል›› ሲሉ የሲዳማ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ደስታ ሌዳሞ ገለፁ።ተቋማትን የመገንባት ስራ ከዚሁ ጎን ለጎን እንደሚካሄድ አስታውቀዋል። ዋና አስተዳዳሪው አቶ ደስታ ሌዳሞ ሰሞኑን ከአዲስ ዘመን ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንዳስታወቁት፤ በአሁኑ ወቅት አዲሱ የሲዳማ ክልል የሚመራበት የራሱ ህገ መንግስት በረቂቅ ደረጃ ተጠናቋል። ህገ መንግስቱን የማርቀቅ ስራ ቀደም ሲል የተጀመረ ሲሆን፣ ከተረቀቀም አንድ ዓመት ያህል ሆኖታል። ረቂቅ ህገ መንግስቱ ላይ የሲዳማ ህዝብ አንድ ጊዜ እንዲወያይበት መደረጉን የተናገሩት አቶ ደስታ፤ በህዝቡ መተቸቱና ማስተቸቱ እንደሚቀጥልም አስታውቀዋል። ለተጨማሪ ንባብ ሊንኩን ይጫኑ https://www.press.et/Ama/?p=25582

በሁለት ተማሪዎች መካከል በተፈጠረ ግጭት የአንድ ተማሪ ህይወት መጥፋቱን ተከትሎ በሀዋሳ ዩኒቨርስቲ የሰዓት ገደብ መጣሉን የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ ገለፀ

በሁለት ተማሪዎች መካከል በተፈጠረ ግጭት የአንድ ተማሪ ህይወት መጥፋቱን ተከትሎ በሀዋሳ ዩኒቨርስቲ የሰዓት ገደብ መጣሉን የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ ገለፀ በትላንትናው ዕለት በሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ሁለት ተማሪዎች በመካከላቸው በነበረ የቆየ ግጭት ምክንያት በተፈጠረ ፀብ የአንድ ተማሪ ህይወት መጥፋቱን የገለፁት የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ ኮማንደር እዮብ አቤቶ ናቸው፡፡ በግጭቱ ሟች በስለት መወጋቱን እንደሰማ ወዲያውኑ በቦታው የደረሰው የከተማው ፖሊስ ተጎጂው የህክምና እርዳታ እንዲያገኝ ቢያደርግም በሪፈራል ሆስፒታል ህክምና እያገኘ ባለበት ወቅት ህይወቱ ማለፉን ጨምረው ገልፀዋል፡፡ ድርጊቱን የፈፀመው ተማሪ እና ድርጊቱ እንዲፈፀም የተባበሩ አካላት ፖሊስ በስውር እና በግልፅ ባደረገው ክትትል በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የገለፁት ኮማንደር እዮብ አስፈላጊው ምርመራ እየተከናወነ መሆኑንም ጨምረው ገልፀዋል፡፡ ከተማሪዎችና ከዩኒቨርስቲ ማህበረሰብ አባላት ጋር በጉዳዩ ዙሪያ ፖሊስ ሰፊ ውይይት ማድረጉን የገለፁት ኃላፊው በአሁን ሰዓት በሁሉም ካምፓሶች የሚገኙ ተማሪዎችና የዩኒቨርስቲ ማህበረሰብ አባላት ድርጊቱን አውግዘው ወደሰላማዊ የመማር ማስተማር ስራው መመለሳቸውን ገልፀዋል፡፡ ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደቱን አስጠብቆ ለመቀጠል ከዩኒቨርስቲ ተማረዎችና የዩኒቨርስቲ ማህበረሰብ ጋር በተደረገ ውይይት ላልተወሰነ ጊዜ የተማሪዎች መውጫ እና መግቢያ ሰዓት ላይ ገደብ መቀመጡን ኮማንደር እዮብ ጨምረው ገልፀዋል፡፡ በዚህም ከምሽት አንድ ሰዓት ብኅላ ወደ ዩኒቨርስቲ መግባትም ሆነ ከዩኒቨርስቲ መውጣት ላልተወሰነ ጊዜ የተከለከለ መሆኑን የገለፁት ኮማንደር እዮብ ከምሽት ሁለት ሰዓት ብኋላ በዩኒቨርስቲ ቅጥር ገቢ ውስጥ ከፀጥታ አካላ

በግል ቂም ተነሳስቶ በሀዋሳ ዩኒቨርስቲ የዶርም አባሉን ህይወት ያጠፋው ተማሪ በቁጥጥር ስር መዋሉ ተገለፀ

በግል ቂም ተነሳስቶ በሀዋሳ ዩኒቨርስቲ የዶርም አባሉን ህይወት ያጠፋው ተማሪ በቁጥጥር ስር መዋሉ ተገለፀ ድርጊቱ በቀን 30/4/2012 ዓ.ም ትላንት ምሽት 4 ሰዓት አካባቢ የተፈፀመ መሆኑን የገለፁት ኮለኔል ሮዳሞ ኪአ በሀዋሳ ከተማ አስተዳደር የሰላምና ፀጥታ አስተዳደር መምሪያ ኃላፊ ናቸው፡፡ በሀዋሳ ዩኒቭርስቲ ተማሪ በሆኑ ሁለት ግለሰቦች መካከል በግል ፀብ በተፈጠረው በዚህ ግጭት የአንደኛ ዓመት የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪ የሆነው ግለሰብ ህይወት በስለት ተወግቶ ማለፉን ኃላፊው ገልፀዋል፡፡ ግጭቱ በተፈጠረ ሰዓት በአካባቢው የነበሩ የህብረተሰብ ክፍሎች ለፖሊስ ባደረጉት ጥሪ መሰረት የከተማው ፖሊስ በፍጥነት ደርሶ ጉዳት የደረሰበት ተማሪ በዩኒቨርስቲው ባለ ክሊኒክ የህክምና እርዳታ እንዲያገኝ ያደረገ ቢሆንም ተጎጂው ሪፈር ተፅፎለት ወደ ሪፈራል ሆስፒታል ተልኮ የህክምና እርዳታ እያገኘ ባለበት ህይወቱ ማለፉን ጨምረው ገልፀዋል፡፡ ድርጊቱን የፈፀመው ግለሰብ እና በድርጊቱ የተሳተፉ አካላት በፖሊስ በቁጥጥር ስር ውለው በተደረገው ምርመራ እና ማጣራት ወንጀሉ የተፈፀመው በሟች እና በገዳዩ መካከል በነበረ የቆየ ግጭት ምክንያት በተያዘ ቂም መሆኑን የገለፁት ኮለኔል ሮዳሞ ናቸው፡፡ በዚህ ድርጊት ባልተጠበቀ ሁኔታ የተማሪው ህይወት ከጠፋ ብኋላ በሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ዋናው ግቢ ጥዋት ላይ ብቻ የመማር ማስተማር ሂደቱ መጠነኛ መስተጓጎል እንደገጠመው የገለፁት ኮለኔል ሮዳሞ በአሁን ሰዓት በሀዋሳ ዩኒቨርስቲ በሁሉም ካፓስ የመማር ማስተማር ስራው በሰላማዊ መንገድ የቀጠለ መሆኑን ነው የገለፁት፡፡ በአሁን ሰዓት ከሁሉም የፀጥታ ሀይል የተውጣጣ ኮማንድ ፖስት በሁሉም ካምፓሶች የተቋቋመ መሆኑን የገለፁት ኮለኔል ሮዳሞ አስተማማኝ የፀጥታ ሁኔታ መኖሩን ጨምረው ገ