ይህ የተገለጸው የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ አቶ ጥራቱ በየነ ከጸጥታው ዘርፍ ጋር ባደረጉት የውይይት መድረክ ላይ ነው፡፡
መድረኩ የጸጥታ ኃይሉ ባለፈው ዓመት የተመራበትን የአግባብ በጠንካራና ደካማ ጎን የገመገመ ሲሆን ለአዲሱ የስራ አመትም አቅጣጫን ያመላከተ ነው ፡፡

የከተማዋን ሰላምና ጸጥታ የማስከበር ኃላፊነት የተጣለበት ፖሊስ በተግባር አፈጻጸም በርካታ ውስንነቶች እንዳሉበት ሲገለጽ ጉዳዩ ከቁርጠኝነት ማነስ የመነጨ እንደሆነም አባላቱ አረጋግጠዋል፡፡
ለዚህም እንደ ምክንያት ከተጠቀሱት መካከል ለፖሊስ አባላት የተሰጠ ትኩረት አናሳ መሆን፣ ሰብዓዊ መብት አለመከበር፣ በስራ ውጤታማነት ሳይሆን በጎሰኝነት መጠቃቀም፣ ሆን ተብሎ ፖሊስ በህብረተሰቡ ዘንድ እንዲጠላ ማድረግ፣ የፖሊሱ መብት በወንጀለኞች ሲደፈር ምላሽ ያለመስጠት እና የስራ ሞራል ማጣት እንደሆኑ ነው አባላቱ በመድረኩ የገለጹት፡፡
ይሁን እንጂ በጸጥታው ዘርፍ በፖሊስ በኩል የሚስተዋሉ ችግሮች ካሏቸው መካከል አንዳንድ የፖሊስ አባላት ከተመደቡበት ቀጠና ውጪ መሆን፣ችግሮች ተከስተው እያዩ በቸልተኝነት ማለፍ፣ የአቅም ውስንነት፣ የመረጃ አያያዝ ችግር፣ የውስጥ አንድነት ያለመኖር እና የመሳሰሉት እንዳሉባቸውም አባላቱ ተናግረዋል፡፡
ከዚሁ ጎን ለጎንም አባሉ በሚፈለገው ልክ ተንቀሳቅሶ ለመስራት የተሸከርካሪ ችግር መኖር፣ የትጥቅ አለመሟላት፣ በጣም በቆየና በአጭር ኮርስ ስልጠና ብቻ የተገደቡ መሆናቸውን ገልጸው እውቀታቸውን ለማዳበር ከስራ ውጭ ሆነው የትምህርት እድል ለማግኘት ምቹ ሁኔታ አለመኖር እንደ ችግር የገለጿቸው ናቸው።
የሀዋሳ ከተማ ፖሊስ መምሪያ አዛዥ ምክትል ኮማንደር ኢዮብ አቤቶ ከኮማንድ ፖስት መምጣት በኋላ ፖሊስ ያሉበትን ችግሮች ማየት በመቻሉና ለለውጥ በመነሳቱ አበረታች ለውጥ ሊመዘገብ ችሏል ብለዋል።
በዚህም በከተማዋ ህገ-ወጥ ሞተሮችን በመያዝ፣ ሌቦችን ወደ ህግ በማቅረብ፣ ንብረትን ከነጣቂዎች ማስጣል፣ ህገ-ወጥ የመሬት ወረራን መከላከል፣ በጎዳና ንግድ፣ እና በመሳሰሉት የጸጥታ ችግር ዙሪያ ለውጦች እንዲጠናከሩ መከናወኑንም ኮማንደሩ አክለዋል።
የሀዋሳ ከተማ የሰላምና ጸጥታ አስተዳደር መምሪያ ኃላፊ ኮሎኔል ሮዳሞ ኪአ በበኩላቸው ከተማዋን ጸጥታን የማረጋገጥ እንዲሁም የከተማዋን ገቢ እያዳከመና የንግዱን ማህበረሰብ እየጎዳ ያለውን የኮንትሮ ባንድ ንግድ ለመታደግ የህግ የበላይነትን ለማስከበር ትኩረት ተሰጥቶ ይሰራል ብለዋል፡፡
የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ጥራቱ በየነ በሀገር ደረጃ የመጣው ለውጥ ሰዎች ሀሳባቸውን በነጻነት እንዲገልጹ ያስቻለና ነጻነት የሰጠ መሆኑን ገልጸው አመራሩም ይሁን የጸጥታ ሀይሉ የራሱን ፍላጎት ወደ ጎን በመተው ለህዝብ ደህንነት ሊሰራ ይገባል ብለዋል፡፡
በልቶና ጠጥቶ ማደር ያልቻለ ህዝብ በማያውቀው ምክንያት ሲሞት ከማየት በላይ የሚያሳምም ነገር አይኖርም ያሉት አቶ ጥራቱ መሪውም ሆነ ተመሪው በጎሰኝነት ጫፍ የወጣበት፣ ለወጣቱ በመጣ የስራ እድል እራሱ የሚዘፈቅበት፣ አሰራር ሊታረም ይገባል ብለዋል።
በመልካም ስነምግባር የሚገለጹ የጸጥታው ዘርፍ አካላት እንዳሉ ሁሉ ችግር ያለባቸውን በሚፈልገው ፍጥነት በመራመድ እራሳቸውን ሊያርሙ ይገባልም ብለዋል፡፡
ከዚህ ቀደም በማወቅም ይሁን ባለማወቅ በአባላቱ ላይ የተከሰቱ ክስተቶችን ሌሎች ህዝቦች ላይ እንደተከሰተው በማሰብ ምንም አይነት የሞራል ውድቀት ሳያግዳችሁ የህዝቡን እፎይታ ማረጋገጥ ይገባልም ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ከንቲው በመድረኩ በርካታ ግብዓቶችን እንዳገኙና ይህንንም በአዲስ ዓመት እቅድ በማካተት የሚመሩ መሆኑንም ነው አቶ ጥራቱ የተናገሩት፡፡
የተቋሙ አባላት በበርካት ችግሮችና ባልተመቻቹ ሁኔታዎች ውስጥ ሆነው ውጤት እንዲያመጡ ስለማይጠበቅ ከንቲባው ከአባላቱ ለቀረቡ የስልጠና፣ የቁሳቁስ፣ የአልባሳት፣ትጥቅና መሰል ችግሮች ዙሪያ ደረጃ በደረጃ ለማገዝ ቃል ገብተዋል፡፡
መድረኩ ከዘርፉ አመራርና አባላት ጋር ትውውቅ ያደረጉበት እንዲሁም የአዲስ አመት ዋዜማ በመሆኑ ለጸጥታው ዘርፍ የእንኳን አደረሳችሁ መልእክትን በማስተላለፍ አዲሱ ዓመት የፍቅር፣ የአንድነትና የሰላም እንዲሆን በመመኝት ነው ያጠናቀቁት፡፡
HAPRC

Comments
Post a Comment