Skip to main content

ምርጫ ቦርድ የሲዳማ ዞን የክልልነት ጥያቄ ህዝበ ውሳኔ የሚሰጥበት ቀን ይፋ አደረገ

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ዞን የክልልነት ጥያቄ ህዝበ ውሳኔ የሚሰጥበት ቀን ይፋ አደረገ።
በዚህም መሰረት የህዝበ ውሳኔው ድምጽ መስጫ ቀን ህዳር 03/2012 አ.ም እንደሚሆን ቦርዱ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በላከው መግለጫ አስታውቋል።
ቦርዱ ህዝበ ውሳኔ ያለበትን ሂደት አስመልክቶ ያወጣው ዝርዝር መግለጫ እንደሚከተለው ቀርቧል፦
የሲዳማ ዞን የክልልነት ጥያቄ ህዝበ ውሳኔ ያለበትን ሂደት አስመልክቶ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የተሰጠ መግለጫ
የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል ምክር ቤት በህዳር 12 ቀን 2011 ዓ.ም በተጻፈ ደብዳቤ የሲዳማ ዞን የክልልነት ጥያቄን ህዝበ ውሳኔ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እንዲያስፈጽምለት መጠየቁ ይታወሳል፡፡
በዚህም መሰረት ቦርዱ አመራሮች ከተሟሉለት በኋላ ባደረገው ውይይት የተለያዩ ውሳኔዎችን ያሳለፈ ሲሆን በሐምሌ 11 ቀን 2011 ዓ.ም በተጻፈ ደብዳቤ ቦርዱን ጨምሮ የክልሉ ምክር ቤት እና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት ማድረግ የሚገባቸውን ዝግጅቶች በዝርዝር አሳውቋል፡፡
በዚህም መሰረት ቦርዱ ለምክር ቤቱ በላከው ደብዳቤ የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል ምክር ቤት እስከ ሐምሌ 19 ቀን 2011 ዓ.ም ድረስ
1. በአሁኑ ወቅት የክልሉም የዞኑም አስተዳደር ዋና ከተማ ሆና የምታገለግለው የሃዋሳ ከተማን አስመልክቶ የህዝበ ውሳኔው ውጤት የሲዳማን ክልላዊ መንግስት መቋቋም የሚያረጋግጥ ቢሆን ከተማዋን አስመልክቶ ሁለቱ አካላት የሚኖራቸውን መብቶችና ግንኙነቶች ከዚህም ጋር በተያያዘ የሚነሱ የሃብት ክፍፍል ጥያቄዎች የሚያስተናግዱበትን አሰራር ዘርግቶ ለቦርዱ በጽሁፍ እንዲያሳውቅ
2. የህዝበ ውሳኔው ጸጥታና ደህንነት ማስጠበቅን አስመልክቶ የፌደራል የክልል እና የዞኑ ፓሊስ በትብብር የሚሰሩበትን ሁኔታ የሚያመቻች የስራ እቅድ አዘጋጅቶ ለቦርዱ እንዲያሳውቅ
3. የደቡብ ክልል ምክር ቤት በሲዳማ ዞን የሚኖሩ የተለያዩ የሌሎች ብሄር ብሔረሰብ አባላት ከህዝበ ውሳኔው በኋላ የሚኖራቸውን ህጋዊ የመብቶች ጥበቃን በተመለከተ ግልጽ አስተዳደራዊና ህጋዊ ማእቀፍ እንዲያዘጋጅና እንዲያሳቅ መጠየቁ ይታወሳል።
የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች የክልል ምክር ቤት በበኩሉ ሐምሌ 19 ቀን 2011 ዓ.ም በተጻፈ ደብዳቤ ምላሹን ለቦርዱ አቅርቧል፡፡
በምላሹም ክልሉ ካለበት ሁኔታና የስራ ጫና አንጻር የሲዳማ ዞን ክልላዊ መንግስት ሆኖ ቢቋቋም ከሃዋሳ ከተማ ጋር የተገናኙ ጉዳዮች የሚስተናገዱበት ህጋዊ ማእቀፍና እና በዞኑ የሚኖሩ ሌሎች የብሔር ብሔረሰብ አባላት ስለሚኖራቸው የመብት ጥበቃ ጊዜ ወስዶ መወያየት እንደሚገባው፣ ህግ ማውጣት ድረስ የሚደርስ ስራ መሆኑን ህግ ማውጣት ደግሞ፣ ማርቀቅ፣ ህዝብ አስተያየት መሰብሰብ እንዲሁም ማጽደቅን የሚጨምር ስራ በመሆኑ በተጨማሪም በአሁኑ ወቅት ክልሉ በኮማንድ ፓስት ስር የሚተዳደር በመሆኑ የተጠቀሱት የአሰራርና የህግ ማእቀፎችን የሚፈልጉ ጉዳዮችን ለማቅረብ ተለዋጭ ጊዜ እንዲሰጠው ጥያቄ አቅርቧል፡፡
በዚህም መሰረት ቦርዱ የተለያዩ ውይይቶችን ካደረገ በኋላ ምክር ቤቱ ምላሹን እስከ ነሃሴ 15 ቀን 2011 ዓ.ም ድረስ እንዲያሳውቅ በሐምሌ 30 ቀን 2011 ዓ.ም በተጻፈ ደብዳቤ ጠይቋል፡፡
የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል ምክር ቤት በነሃሴ 16 ቀን 2011 አ.ም በተጻፈ ደብዳቤ ህዝበ ውሳኔው የሲዳማን ክልል መሆን ቢያረጋግጥ የሃዋሳ ከተማን አስመልክቶ ሁለቱ አካላት ስለሚኖራቸው ግንኙነትና የሃብት ክፍፍል ህግ ለማውጣትና ህጋዊ ማእቀፍ ለማዘጋጀት እንዲሁም በዞኑ የሚኖሩ ሌሎች ብሔረሰብ አባላትን ስለሚኖራቸው መብትና ጥበቃ ከህገ መንግስቱ በተጨማሪ አስተዳደራዊና ህጋዊ ማእቀፎችን ለማዘጋጀት ጊዜ ስለሚያስፈልግ አሁን ማቅረብ እንደማይችል ገልጾ ነገር ግን ከህዝበውሳኔው አስቀድሞ የህግ እና አስተዳደራዊ ማእቀፎቹን በማጽደቅ እንደሚያቀርብ አረጋግጧል፡፡
በመሆኑም ቦርዱ ባደረገው ውይይት የሚከተሉትን ዋና ዋና ውሳኔዎች አስተላልፎ ለሚመለከታቸው አካላት አሳውቋል፡፡
1. ቦርዱ ከነሃሴ 20 ቀን 2011 አ.ም እስከ ህዳር 10 ቀን 2012 ድረስ የሚቆይ የህዝበ ውሳኔውን የድርጊት መርሃ ግብር እና በጀት አዘጋጅቶ ለደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል ምክር ቤት እና ለሚመለከታቸው አካላት የላከ ሲሆን በእቅዱ መሰረት የህዝበ ውሳኔው ድምጽ መስጫ ቀን ህዳር 03/2012 አ.ም ይሆናል፡፡
2. ቦርዱም በድርጊት መርሃ ግብሩ መሰረት፣ የባለድርሻ አካላትን ማስተባበር እና የአፈጻጸም ውይይት የማድረግ ስራውን ከነሃሴ 30 ቀን 2011 ዓ.ም ጀምሮ በተከታታይ ባሉት ሳምንታት የሚያከናውን ሲሆን ከዚህም ተጨማሪ የ 8,460 ( ስምንት ሺህ አራት መቶ ስልሳ) ምርጫ አስፈጻሚዎችን መመልመል 1,692 ( አንድ ሺህ ስድስት መቶ ዘጠና ሁለት) የድምጽ መስጫ ጣቢያዎችን ማደራጀት፣ የህዝበ ውሳኔ መመሪያዎች የማውጣትና የድምጽ መስጫ ወረቀቶች ህትመት የመሳሰሉትን ስራዎች ያከናውናል፡፡
3. ቦርዱ በተጨማሪም ከመስከረም 07 ቀን 2012 አ.ም ጀምሮ የህዝበ ውሳኔውን ጸጥታና ደህንነት ጥበቃ የእቅድ ዝግጅት ለማከናወን ከፌደራል፣ ከክልል እና ከዞን የጸጥታ አካላት ጋር የጋራ እቅድ የማውጣት ውይይቶችን ያደርጋል፡፡
4. የደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል ምክር ቤት የሀዋሳን ከተማ የወደፊት ሁኔታ ፤የሀብት ክፍፍል እና የሌሎች ብሄረሰብ አባላትን የመብቶች ጥበቃ አስመልክቶ ህጋዊ እና አስተዳደራዊ ማእቀፎችን ማውጣት ስራ እስከ መስከረም 22 ድረስ ያጠናቀቃል፡፡
5. የደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል ምክር ቤት ቦርዱ ባቀረበው ዝርዝር የበጀት እቅድ መሰረት ህዝበ ውሳኔን ለማፈጸም የሚያስፈልገውን 75,615,015.00 (ሰባ አምስት ሚልዮን ስድስት መቶ አስራ አምስት ሺህ አስራ አምስት) ብር በጀት እስከ መስከረም 12 ቀን 2012 አ.ም ድረስ ወደ ቦርዱ የባንክ አካውንት ያስተላልፋል፡፡
በመሆኑም ቦርዱ የቴክኒክ ጉዳዮች በቀሪው ጊዜ ሲያጠናቅቅ ባለድርሻ አካላትም በተሰናዳው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት የሚጠበቅባቸውን ሃላፊነት በመወጣት ሕዝበ ውሳኔው በታቀደለት ጊዜ መሰረት እንዲከናወን የበኩላቸውን ሃላፊነት እንዲወጡ ያስታውቃል፡፡

Comments

Popular Posts

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የመንግሥት ስልጠና የምርጫ ቅስቀሳ አካል ነው ብሏል  የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ለምን ወጣ መባሉ ተገቢ አይደለም - ምርጫ ቦርድ ምርጫ ቦርድ ከኢህአዴግ ተፅዕኖ ሙሉ ለሙሉ ነፃ መሆኑ ሳይረጋገጥና የምርጫ አፈፃፀም ችግሮች ሳይወገዱ የምርጫ የጊዜ ሰሌዳ ለማወጅ መዘጋጀቱ ተገቢ አይደለም ሲል ፕ/ር በየነ ጴጥሮስ የሚመሩት ኢማዴ-ደህአፓ ተቃወመ፡፡ መንግስት፤ የዩኒቨርሲቲ መምህራንና ተማሪዎችን ጨምሮ ለተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች እየሰጠ ያለው ስልጠና የምርጫ ቅስቀሳ አካል ነው ሲልም ፓርቲው ኮንኗል፡፡  የኢትዮጵያ ማህበረ ዴሞክራሲ ደቡብ ህዝቦች አንድነት ፓርቲ ሰሞኑን ለብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ባስገባው ግልፅ ደብዳቤ፤ ያለፉት አገር አቀፍና የአካባቢ ምርጫዎች ከመካሄዳቸው በፊት በምርጫ ችግሮችና መፍትሄዎቻቸው ዙሪያ ኢህአዴግ ከተቃዋሚዎች ጋር የሚወያይበት መድረክ እንዲዘጋጅ በተደጋጋሚ ብንጠይቅም እስካሁን ከቦርዱ የተሰጠ ተግባራዊ ምላሽ የለም ብሏል፡፡  ሃገሪቱ “በአንድ አውራ ፓርቲ” ብቸኛ ቁጥጥር ስር መውደቋ አደገኛና አሳሳቢ ነው ያለው ፓርቲው፤ የመድብለ ፓርቲ ስርአት የመገንባት ተስፋችን ጨርሶ እንዳይከስም ቦርዱ ሃላፊነቱን መወጣት እንዳለበት አሳስቧል፡፡ ነፃና ፍትሃዊ ምርጫ የሚካሄድበትን ሁኔታ ለመፍጠር ገዥው ፓርቲና ሃቀኛ ተቃዋሚ ፓርቲዎች የሚወያዩበት መድረክ እንዲያመቻች በህግ ስልጣን የተሰጠው ምርጫ ቦርድ የገባውን ቃል በማጠፍ መድረኩን ሳያመቻች የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማዘጋጀቱ ፋይዳ የለውም ብሏል - ፓርቲው፡፡  ገዥው ፓርቲ ኢህአዴግ በተሻሻለው የምርጫ ህግ፣ ለቦርዱ የተሰጠውን የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ መድረክ የማስተባበር ስልጣን ለመቀማት ታማኝ ፓርቲዎችን በተቃዋሚ ስም አሰባስቦ “የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ መድረክ” በመፍጠር የምርጫ ውድድር አሯሯጭ አሰልፏል ሲ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

የለበሰው ያደፈ ቁምጣና ሹራብ ከቅዝቃዜው አላዳነውም፡፡ ካፊያው ልብሱን አርሶታል፡፡ ሽው እያለ ከሐይቁ የሚነሳው ነፋስ የሚፈጥረው ቅዝቃዜ ያንቀጠቅጠዋል፡፡ የተጫማው ያረጀ ሲሊፐር እግሩን ከምንም አላዳነውም፡፡ በባዶ እግሩ የሚራመድ ያህል ጨቅይቷል፡፡ ተደባዳቢ ይመስል ፊቱ የተሞነጫጨረ ነው፡፡ ገና 12 ዓመቱ ቢሆንም፣ ቁመናው እንደ ትልቅ ሰው ግዙፍ ነው፡፡ የሚለብሰውን እንደ ልቡ ባያገኝም፣ የሚያስፈልገውን ነገር ለማሟላት ቤሳቢስቲን የሌላቸው ወላጆቹን አያስቸግርም፡፡ ከቤተሰቦቹ ጋር ከሚኖሩበት ታቦር ተራራ ጀርባ ወዳለው ሐዋሳ ሐይቅ ከወረደ እንኳንስ የራሱን የቤተሰቦቹንም የዕለት ጉርስ የሚሸፍንበት ገንዘብ አያጣም፡፡ የአስጎብኚነት ዕውቀት፣ ከሐይቁም ውስጥ ዓሳ የሚያጠምድበት መረብም ሆነ ፈቃድ የለውም፡፡ ሙሉቀን (ስሙ ተቀይሯል) እና ጓደኞቹ ሐይቁን ለመጎብኘት የሚሄዱ ጎብኚዎች በካሜራቸው ጥሩ ፎቶ እንዲያስቀሩ ድባቡን የማሳመር ሥራ ይሠራሉ፡፡ ካሜራውን ይዞ ቁጭ ብድግ እያለ ጥሩ ፎቶ ለማንሳት ጥረት የሚያደርግ ሲያዩ፣ ቆርጠው የያዙትን የዓሳ ሥጋ ይዘው ጠጋ ጠጋ ይላሉ፡፡ ቁርጥራጩን የዓሳ ሥጋ ምግብ ለሚቀሙት አባኮዳዎች ሻሞ ይላሉ፡፡ የተወረወረላቸውን ቀድመው ለመቅለብ አባኮዳዎቹ ክንፋቸውን እየመቱ ወደ ላይ ብድግ ይላሉ፡፡ የናሽናል ጆግሪፊ የፎቶግራፍ ባለሙያዎች ያነሱት ዓይነት ፎቶዎች ሳያስቡት ያነሳሉ፡፡ በሁኔታው ተደስተው ደጋግመው ድንቅ ፎቶዎችን ለመውሰድ ሲዘጋጁ እነ ሙሉቀንም አጀንዳቸውን ይፋ ማድረግ ይጀምራሉ፡፡ አቶ ዳዊት አብርሃም ‹‹አንዱን ዓሳ በአሥር ብር ገዝቼ ነው እንዲህ የማዘጋጀው፤›› በማለት በቅድሚያ  መረጃ ይሰጣሉ፡፡ ለቀጣዩ ዜና በዚህ መልኩ እንዲዘጋጁ ካደረጉ በኋላ፣ ሌሎች ሰዎች መቶም ሁለት መቶም ብር እንደሚሰጧቸው ቀለል

Sidama: the Luwa and the Anga Culture and their Social Implications

By Wolassa Kumo 1. Introduction In my previous articles, I mentioned the Sidama grand social constitution Seera, and various sub constitutions which derive from this grand constitution. We have also seen that all social constitutions or Seera in Sidama were based on the Sidama moral code of halale, the true way of life. In this socio-cultural and socio-political system, the role of the elders was very important. Elders were bestowed with the power of enforcing the Seera and referring the recalcitrant to Magano or God if he/she refuses to abide by the Seera. The power of elders in the Sidama society was not based on a simple age count as is the case in most modern societies. The Sidama elder is more the product of various social processes through which he passes than the product of a simple aging. For a person to become a recognised elder with authority in Sidama, he has to become a Cimeessa (respected elder with authority) or Cimeeyye for many respected elders. There are three importa