አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 20፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በሀዋሳ ከተማ በባለ ሁለት እግር ተሸከርካሪዎች (ሞተር ሳይክሎች) ላይ ላልተወሰነ ጊዜ እንዳይንቀሳቀሱ ተጥሎ የነበረው እገዳ መነሳቱን ፖሊስ አስታወቀ።
በጉዳዩ ዙሪያ የሀዋሳ ከተማ ፖሊስ መምሪያ እና የደቡብ ፖሊስ ከሚሽን በዛሬው ዕለት የጋራ መግለጫ ሰጥተዋል።
የሀዋሳ ከተማ ፓሊስ መምሪያ አዛዥ ኮማንደር መስፍን ዴቢሶ በከተማዋ በሞተር ሳይክሎች ላይ ተጥሎ የነበረው ገደብ መነሳቱን እና ህጋዊ አሽከርካሪዎች እንዲያሸከረክሩ መፈቀዱን ገልጸዋል።
በዚህም መሰረት ከጧቱ ከ12፡00 ሰዓት እስከ ምሽቱ 12፡00 ሰዓት ድረስ ማሽከርከር እንደሚቻል የተናገሩት ኮማንደር መስፍን፥ ልዩ ፈቃድ ያላቸው አሽከርካሪዎች ከምሽት 12፡00 ሰዓት በኋላም ማሽከርከር እንደሚችሉ አስረድተዋል።
ቀዚህ ቀደም በከተማዋ ተይዘው የነበሩ ሞተር ሳይክሎች ባለቤቶቹ ህጋዊ ሰነዶቻቸውን በማቅረብ እየወሰዱ እንደሆነም ገልፀዋል።
ቀሪዎቹም ህጋዊ ሰነዶቻቸውን አሟልተው በማቅረብ መውስድ መውሰድ እንደሚችሉም ነው ኮማንደር መስፍን ያስታወቁት።
የደቡብ ፖሊስ ኮሚሽን የወንጀል እና ትራፊክ አደጋ ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኮማንደር ታደለ ዋሪዮ በበኩላቸው በሃዋሳ ከተማ አሁን ላይ እየታየ ካለው አንፃራዊ ሰላም በመበነሳት ኮማንድ ፖስቱ ገምግሞ ውሳኔውን ማሳለፉን ተናግረዋል።
(ኤፍ.ቢ.ሲ)
Comments
Post a Comment