አዲስ አበባ ፣ ነሃሴ 25 ፣ 2011 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ክልል ምክር ቤት አቶ ርስቱ ይርዳውን የክልሉ ምክትል ርእሰ መስተዳደር አድርጎ ሾመ። የክልሉ ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 5ኛ ዙር 4ኛ ዓመት 9ኛ ጉባኤው ነው አቶ ርስቱ ይርዳውን የክልሉ ምክትል ርእሰ መስተዳደር በማድረግ የሾመው። ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ አቶ ርስቱ ይርዳው ዛሬ ሹመታቸውን ተከትሎ ባደረጉት ንግግር፥ “ሀገራዊ ለውጡን ተከትሎ ያጋጠሙ ውስብስብ ችግሮች መፍትሔ በሚሹበት ሰዓት ቢሆንም፤ የሕዝቦችን ኃላፊነት በመቀበሌ ኩራት ይሰማኛል” ብለዋል። ብሔር፣ብሔረሰቦችና ሕዝቦች የጣሉባቸውን እምነት፣ ሁሉንም በእኩል ዓይን በማገልገል ለመወጣት ቅን ፍላጎት እንዳላቸው ገልፀዋል። በክልሉ የተነሱ የክልልነትና የአደረጃጀት ጥያቄዎች ለክልሉና ለደህኢዴን ከባድ ፈተና ስለመሆናቸው ያነሱት አቶ ርስቱ፥ የተፈጠሩትም ሁከቶች ከባድ ጉዳት ያደረሱና የአብሮነት ሕልውናን የተፈታተኑ ነበሩ ብለዋል። በክልሉ የሕግ የበላይነትን የማረጋገጥ፣ ሠላም የማስፈንና ጥፋተኞችን ለሕግ ማቅረብ ላይ ትኩረት የሚያደርጉ መሆናቸውንም አቶ ርስቱ ገልፀዋል። አቶ ርስቱ በሹመት ንግግራቸው “የብሔር ፅንፈኝነትን፣ የሀይማኖት አክራሪነትን እና ሕገ ወጥነት ለመከላከል ጠንካራ ስራ ይሰራል” ብለዋል። የአመራር ማስተካካያዎችም በጥብቅ ትኩረት እንደሚከናወንም ነው አቶ ርስቱ በንግግራቸው ያስገነዘቡት። የኑሮ ውድነትንና ሥራ አጥነትን ለማሻሻል ከባለድርሻ አካላት ጋር በትብብር እንደሚሠራ የተናገሩት አቶ ርስቱ፥ ከባ ሀብቶች ጋር ተቀራርቦ ለመሥራት ያላቸውን ፍላጎት በመግለፅ፣ የእንደጋገፍ ጥሪ ለባለ ሀብቶቹ አቅርበዋል። በተጨማሪም የደቡብ ክልል ምክር ቤት የክልሉ መንግስት የ2012 በጀት አፀድቋል። በዚሁ መሰረት የ
It's about Sidaama!