Skip to main content

በ11 ወራት ከታቀደው የቡና ወጪ ንግድ ከ287 ሚሊዮን ዶላር ቅናሽ ያሳየ ገቢ ተገኘ

ሻይና ቅመማ ቅመምን ጨምሮ ከ679 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ተመዝግቧል
በተያዘው በጀት ዓመት እስከ ግንቦት ወር መጨረሻ ድረስ 264 ሺሕ ቶን ቡና ለውጭ ገበያ በማቅረብ ይገኛል ተብሎ የሚጠበቀው የገቢ መጠን ከ955 ሚሊዮን ዶላር በላይ ቢሆንም፣ በአፈጻጸሙ ግን ከ287 ሚሊዮን ዶላር በላይ ቅናሽ የተመዘገበበትን ገቢ ማስገኘቱ ታውቋል፡፡
የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለሥልጣን ባወጣው ወርኃዊ ሪፖርት መሠረት፣ እስከ ግንቦት 2011 ዓ.ም. ባሉት 11 ወራት ውስጥ ከቡና ይጠበቅ ከነበረው ገቢ 70 በመቶ ገደማ ወይም 668.58 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ተገኝቷል፡፡ በአጠቃላይ የዘርፉ ገቢና አፈጻጸም አምና በተመሳሳይ ወቅት ከቡና ብቻ ከተገኘው የ740 ሚሊዮን ዶላር የቡና ገቢ አኳያም፣ 72 ሚሊዮን ዶላር ገደማ ቅናሽ ተመዝግቧል፡፡
በዚህ ዓመት ለታየው የቡና አፈጻጸም መዳከም ውጫዊና ውስጣዊ ምክንያቶች ቀርበዋል፡፡ ባለሥልጣኑ የዓለም የቡና ዋጋ በ20 በመቶ ቅናሽ ማሳየቱን በውጫዊ ምክንያትነት ያጣቀሰ ሲሆን፣ ቡና አምራች አገሮች በርካታ የቡና ምርት ማቅረባቸው፣ የኢትዮጵያን ቡና የሚገዙ ደንበኞች ግዥ ከመፈጸም መዘግየታቸውና አምና ከነበራቸው ክምችት አኳያ የግዥ ፍላጎታቸው መቀነሱ ከቀረቡት ምክንያቶች ውስጥ ተካተዋል፡፡
በአንፃሩ ከውስጣዊ ችግሮች መካከል የአገር ውስጥ የቡና ዋጋ ከዓለም ዋጋ ጋር ባለው ልዩነት ሳቢያ ላኪዎች የውል ስምምነታቸውን ማክበር አለመቻላቸው አንዱ ሲሆን፣ የኤሌክትሪክ ኃይል በየጊዜው መቆራረጡ ቡናውን በወቅቱ አዘጋጅቶ ለመላክ እንዳላስቻለና የኮንቴይነር ዕጥረት መታየት በምክንያትነት ቀርበዋል፡፡
የቡና የወጪ ንግድ አፈጻጸም ከሻይና ከቅመማ ቅመም ምርቶች ጋር ተዳምሮ 209,407.76 ቶን ያስመዘገበ ሲሆን፣ ይህም ከዕቅዱ አኳያ የ74.84 በመቶ መጠን በመላክ በጠቅላላው የ679 ሚሊዮን ዶላር ገቢ በማስገኘት ሊጠናቀቅ ከሁለት ሳምንት ያነሰ ዕድሜ የቀረው የበጀት ዓመት አገባዷል፡፡
እስካለፈው ግንቦት ወር በነበረው የዚህ ዓመት የቡና ወጪ ንግድ አፈጻጸም ከመዳረሻ አገሮች አኳያ ሲታይ፣ ሳዑዲ ዓረቢያ በ40,432 ቶን ወይም በ20 በመቶ ድርሻ ቀዳሚዋ የኢትዮጵያ ቡና ገዥ ተብላለች፡፡ በገቢም የ107.76 ሚሊዮን ዶላር ወይም የ16 በመቶ ድርሻ ነበራት፡፡ አሜሪካ በ20,222 ቶን ወይም በ10 በመቶ ድርሻ፣ በ106.32 ሚሊዮን ዶላር ወይም በ16 በመቶ የገቢ ድርሻ ሁለተኛውን ደረጃ ይዛለች፡፡ ጀርመን የ29,049.53 ቶን ወይም የ14 በመቶ የመጠን ድርሻ ያለውን ቡና በ83.89 ሚሊዮን ዶላር በመግዛት ሦስተኛዋ የኢትዮጵያ ቡና መዳረሻ ሆናለች፡፡
የተቀሩት አገሮች በገቢ ቅደም ተከተል ሲቀመጡ ጃፓን አራተኛ፣ ቤልጅየም አምስተኛ፣  ደቡብ ኮሪያ ስድስተኛ፣ ጣሊያን ሰባተኛ፣ ሱዳን ስምንተኛ፣ አውስትራሊያ ዘጠነኛ፣ እንዲሁም እንግሊዝ የአሥረኛ ደረጃን ይዘዋል፡፡  በጠቅላላው አሥሩ አገሮች 84 በመቶ የቡና መጠን እንደሚገዙና 82 በመቶ ገቢም ከእነዚህ አገሮች እንደሚመነጭ የቡናና ሻይ ባለሥልጣን ሪፖርት ያብራራል፡

Comments

Popular Posts

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የመንግሥት ስልጠና የምርጫ ቅስቀሳ አካል ነው ብሏል  የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ለምን ወጣ መባሉ ተገቢ አይደለም - ምርጫ ቦርድ ምርጫ ቦርድ ከኢህአዴግ ተፅዕኖ ሙሉ ለሙሉ ነፃ መሆኑ ሳይረጋገጥና የምርጫ አፈፃፀም ችግሮች ሳይወገዱ የምርጫ የጊዜ ሰሌዳ ለማወጅ መዘጋጀቱ ተገቢ አይደለም ሲል ፕ/ር በየነ ጴጥሮስ የሚመሩት ኢማዴ-ደህአፓ ተቃወመ፡፡ መንግስት፤ የዩኒቨርሲቲ መምህራንና ተማሪዎችን ጨምሮ ለተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች እየሰጠ ያለው ስልጠና የምርጫ ቅስቀሳ አካል ነው ሲልም ፓርቲው ኮንኗል፡፡  የኢትዮጵያ ማህበረ ዴሞክራሲ ደቡብ ህዝቦች አንድነት ፓርቲ ሰሞኑን ለብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ባስገባው ግልፅ ደብዳቤ፤ ያለፉት አገር አቀፍና የአካባቢ ምርጫዎች ከመካሄዳቸው በፊት በምርጫ ችግሮችና መፍትሄዎቻቸው ዙሪያ ኢህአዴግ ከተቃዋሚዎች ጋር የሚወያይበት መድረክ እንዲዘጋጅ በተደጋጋሚ ብንጠይቅም እስካሁን ከቦርዱ የተሰጠ ተግባራዊ ምላሽ የለም ብሏል፡፡  ሃገሪቱ “በአንድ አውራ ፓርቲ” ብቸኛ ቁጥጥር ስር መውደቋ አደገኛና አሳሳቢ ነው ያለው ፓርቲው፤ የመድብለ ፓርቲ ስርአት የመገንባት ተስፋችን ጨርሶ እንዳይከስም ቦርዱ ሃላፊነቱን መወጣት እንዳለበት አሳስቧል፡፡ ነፃና ፍትሃዊ ምርጫ የሚካሄድበትን ሁኔታ ለመፍጠር ገዥው ፓርቲና ሃቀኛ ተቃዋሚ ፓርቲዎች የሚወያዩበት መድረክ እንዲያመቻች በህግ ስልጣን የተሰጠው ምርጫ ቦርድ የገባውን ቃል በማጠፍ መድረኩን ሳያመቻች የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማዘጋጀቱ ፋይዳ የለውም ብሏል - ፓርቲው፡፡  ገዥው ፓርቲ ኢህአዴግ በተሻሻለው የምርጫ ህግ፣ ለቦርዱ የተሰጠውን የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ መድረክ የማስተባበር ስልጣን ለመቀማት ታማኝ ፓርቲዎችን በተቃዋሚ ስም አሰባስቦ “የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ መድረክ” በመፍጠር የምርጫ ውድድር አሯሯጭ አሰልፏል ሲ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

የለበሰው ያደፈ ቁምጣና ሹራብ ከቅዝቃዜው አላዳነውም፡፡ ካፊያው ልብሱን አርሶታል፡፡ ሽው እያለ ከሐይቁ የሚነሳው ነፋስ የሚፈጥረው ቅዝቃዜ ያንቀጠቅጠዋል፡፡ የተጫማው ያረጀ ሲሊፐር እግሩን ከምንም አላዳነውም፡፡ በባዶ እግሩ የሚራመድ ያህል ጨቅይቷል፡፡ ተደባዳቢ ይመስል ፊቱ የተሞነጫጨረ ነው፡፡ ገና 12 ዓመቱ ቢሆንም፣ ቁመናው እንደ ትልቅ ሰው ግዙፍ ነው፡፡ የሚለብሰውን እንደ ልቡ ባያገኝም፣ የሚያስፈልገውን ነገር ለማሟላት ቤሳቢስቲን የሌላቸው ወላጆቹን አያስቸግርም፡፡ ከቤተሰቦቹ ጋር ከሚኖሩበት ታቦር ተራራ ጀርባ ወዳለው ሐዋሳ ሐይቅ ከወረደ እንኳንስ የራሱን የቤተሰቦቹንም የዕለት ጉርስ የሚሸፍንበት ገንዘብ አያጣም፡፡ የአስጎብኚነት ዕውቀት፣ ከሐይቁም ውስጥ ዓሳ የሚያጠምድበት መረብም ሆነ ፈቃድ የለውም፡፡ ሙሉቀን (ስሙ ተቀይሯል) እና ጓደኞቹ ሐይቁን ለመጎብኘት የሚሄዱ ጎብኚዎች በካሜራቸው ጥሩ ፎቶ እንዲያስቀሩ ድባቡን የማሳመር ሥራ ይሠራሉ፡፡ ካሜራውን ይዞ ቁጭ ብድግ እያለ ጥሩ ፎቶ ለማንሳት ጥረት የሚያደርግ ሲያዩ፣ ቆርጠው የያዙትን የዓሳ ሥጋ ይዘው ጠጋ ጠጋ ይላሉ፡፡ ቁርጥራጩን የዓሳ ሥጋ ምግብ ለሚቀሙት አባኮዳዎች ሻሞ ይላሉ፡፡ የተወረወረላቸውን ቀድመው ለመቅለብ አባኮዳዎቹ ክንፋቸውን እየመቱ ወደ ላይ ብድግ ይላሉ፡፡ የናሽናል ጆግሪፊ የፎቶግራፍ ባለሙያዎች ያነሱት ዓይነት ፎቶዎች ሳያስቡት ያነሳሉ፡፡ በሁኔታው ተደስተው ደጋግመው ድንቅ ፎቶዎችን ለመውሰድ ሲዘጋጁ እነ ሙሉቀንም አጀንዳቸውን ይፋ ማድረግ ይጀምራሉ፡፡ አቶ ዳዊት አብርሃም ‹‹አንዱን ዓሳ በአሥር ብር ገዝቼ ነው እንዲህ የማዘጋጀው፤›› በማለት በቅድሚያ  መረጃ ይሰጣሉ፡፡ ለቀጣዩ ዜና በዚህ መልኩ እንዲዘጋጁ ካደረጉ በኋላ፣ ሌሎች ሰዎች መቶም ሁለት መቶም ብር እንደሚሰጧቸው ቀለል

Sidama: the Luwa and the Anga Culture and their Social Implications

By Wolassa Kumo 1. Introduction In my previous articles, I mentioned the Sidama grand social constitution Seera, and various sub constitutions which derive from this grand constitution. We have also seen that all social constitutions or Seera in Sidama were based on the Sidama moral code of halale, the true way of life. In this socio-cultural and socio-political system, the role of the elders was very important. Elders were bestowed with the power of enforcing the Seera and referring the recalcitrant to Magano or God if he/she refuses to abide by the Seera. The power of elders in the Sidama society was not based on a simple age count as is the case in most modern societies. The Sidama elder is more the product of various social processes through which he passes than the product of a simple aging. For a person to become a recognised elder with authority in Sidama, he has to become a Cimeessa (respected elder with authority) or Cimeeyye for many respected elders. There are three importa