የሐገር ሽማግሌዎች በበዓሉ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት የሲዳማ ዞን የክልል መስተዳድርነት ሥልጣን እንዲኖረዉ ከዚሕ ቀደም የተወሰነዉ ገቢር እንዲሆን ጠይቀዋል።ባለፈው ዓመት የፊቼ - ጫምባላላ በዓል ሲከበር በተቀሰቀሰ ግጭት የሰው ሕይወትና ንብረት ጠፍቶ ነበር:: ፊቼ ጫምበላላ በዓል በሐዋሳ የሲዳማ ብሔር የዘመን መለወጫ በዓል ፊቼ - ጫምባላላ ዛሬ ሐዋሳ ሐይቅ ዳርቻ በሚገኘው አደባባይ (ጉዱማሌ) እየተከበረ ነዉ።በበዓሉ ላይ በሲዳማ ዞን ከሚገኙ የተለያዩ ወረዳዎች የተዉጣጣ በሺሕ የሚቆጠር ሕዝብ፤የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፣ የፌደራልና የአጎራባች ክልሎች ባለሥልጣናት ተካፍለዋል።የሐገር ሽማግሌዎች በበዓሉ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት የሲዳማ ዞን የክልል መስተዳድርነት ሥልጣን እንዲኖረዉ ከዚሕ ቀደም የተወሰነዉ ገቢር እንዲሆን ጠይቀዋል።ባለፈው ዓመት የፊቼ - ጫምባላላ በዓል ሲከበር በተቀሰቀሰ ግጭት የሰው ሕይወትና ንብረት ጠፍቶ ነበር።የሐዋሳዉ ዘጋቢያችን ሸዋንግዛዉ ወጋየሁ እንዳለዉ የዘንድሮዉ በዓል ከዋዜማዉ ጀምሮ ሠላማዊ ነበር።የግጭት ሥጋት ግን አልተለየዉም።
It's about Sidaama!