የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በመሉ እንኳን ለብርሀነ ትንሳኤው በዓል በሰላም አደረሰን፤ አደረሳችሁ በማለት መልካም ምኞቱን ይገልጻል
የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በመሉ እንኳን ለብርሀነ ትንሳኤው በዓል በሰላም አደረሰን፤ አደረሳችሁ በማለት መልካም ምኞቱን ይገልጻል፡፡ የዘንድሮውን የትንሳኤ በዓል የከተማዋ ነዋሪ በድምቀት ሲያከብረው የተለመደ አብሮነቱን በፍቅር ብሎም አርዓያ የሆነ ምግባሩን ለብዙዎች የሚገለጥበት ሆኖ እንደሚያልፍ የአስተዳደሩ እምነት ነው፡፡ በኢትዮጵያ የከተሞች መድረክ የምንጊዜም የአሸናፊነት ተምሳሌት፣ ምቹ የቱሪዝም እና የኢንቨስትመንት መዳረሻ የሆነችው ከተማችን ሀዋሳ ለእኚህ ተጨባጭ ስኬታማ የለውጥ ጉዞዎቿ አመራሩ፣ ፐብሊክ ሰርቫንቱ፣ ልማታዊ ባለሀብቱ እና ከምንም በላይ ሰላም ወዳዱ የከተማዋ ነዋሪ ድምር ውጤት እንደሆነ አስተዳደሩ ያምናል፡፡ እኚህን አቅሞች ቀጣይ በከተማዋ የልማት ግስጋሴዎች ውስጥ የተሳለጠ ከማድረግ አንጻርም በየበጀት አመቱ ግዙፍ እና በተሻለ ልህቀት ሁለንተናዊ አቅሟን ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሻግሩ የልማት ግቦችን አስተዳደሩ በመንደፍ ጭምር ተግባራዊ እያደረገ ይገኛል፡፡ በዚህም የከተማዋ ነዋሪ በየትኛውም የልማት ስራ ቀጥተኛ ተሳታፊ እና ተጠቃሚ ብሎም እንደ ፍላጎቱ ተግባራዊ በሚደረጉ የልማት ውጥኖች ላይ አስተያየት ከመስጠት የዘለለ በጎደሉትም ላይ ጠያቂ እስከመሆን የደረሰ ዘመናዊ የከተማ ነዋሪነቱን እያስመሰከረ እንደሆነ ያሉ ነባራዊ እውነታዎች ያስረዱናል፡፡ ይህ ሀቅ ሆኖ ሳለ ግን አንዳንድ የከተማችንን ሰላማዊ የሆነ ገጽታን የሚያጠለሹ አብሮነትን በመሸርሸር ያልተገባ ጥላቻን ለመዝራት ጥረት የሚያደርጉ ሀይሎች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተበራከቱ ማየታችን የተለመደ እየሆነ ይገኛል፡፡ በመሆኑም የከተማችን ነዋሪ የዚህን እኩይ ስነምግባር ባለቤት የሆኑ ግለሰቦችን ስውር ሴራ ከወዲሁ በመለየት እና የማይነጥፍ ፍቅሩን ለዘመናት