የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፤ ከተቋማዊ ማሻሻያ ወይም reform በፊት ህገ መንግስቱን ያክብር!!
የሲዳማን
ዞን በክልል የማደራጀት ጥያቄን አስመልክቶ፤
ከዛሬ ስምንት ወራት በፊት በዞኑ ምክር ቤት
ጸድቆ፤ ብሎም በክልሉ ምክር ቤት ተቀባይነትን
አግኝቶ የአገሪቱ የምርጫ ቦርድ ሪፊሬንደም
እንዲያዘጋጅ የተጠየቀ ሲሆን፤ በዛሬ እለት
''የሪፌሬንዴም
ቀን ይነገረን '' በሚል
በሀዋሳ ከተካሄደው ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ ጋር
በተያያዘ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ
ሰብሳቢ ወ/ት
ብርቱካን ሚዴቅሳ በጉዳዩ ላይ ማብራሪያ
ሰጥተዋል፡፡
በማብራሪያውም፤
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፤ ህገመንግስቱን
በመቃረን የሲዳማ ክልል የመሆን ጥያቄ ሪፍሬንደም
በህገ መንግስቱ በተቀመጠው መሰረት በአንድ
አመት ውስጥ የሚካሄድ ሳይሆን፤ በመጪው
የአከባቢ እና አጠቃላይ ምርጫ ጋር ተያይዞ
የሚፈጸም መሆኑን የቦርዱ ሰብሳቢ አስታውቋል።
ወ/ት
ብርቱካን ሚዴቅሳ ከኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ጋር
በነበራቸው ቆይታ በሰጡት ማብራሪያ፤ በኢትዮጵያ
ህገመንግስት የተደነገጉትን መሰል የክልል
ጥያቄዎች ምላሽ እንዲያገኙ በአንድ አመት
ጊዜ ውስጥ ሪፍሬንደሞችን የማዘጋጀት ስራዎችን
ከመስራት ይልቅ ፤ በብሄራዊ የምርጫ ቦርድ
ተቋማዊ ማሻሻያ ወይም reform ላይ
ትኩረት ስጥቶ ይሰራል ብለዋል።
የኢትዮጵያ
ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ህገመንግስታዊ እና
ዲሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ ከህዝብ ለሚነሱ
ጥያቄዎች በአግባቡ ምላሽ ከመስጠት ይልት
በአቅም ማነስ እና ተቋማዊ ለውጥ ወዘተ ሰበብ
ኢ-ህገመንግስታዊ
አካሄድ መከተሉ፤ በአገሪቱ እየታየ ያለውን
የዲሞክራሲ ጭላንጭል ከማዳፈኑ በላይ የዶ/ር
አብይ አሃመድ አስተዳደር በህዝብ ዘንድ ያለውን
ተቀባይነት አደጋ ውስጥ ይጥላል።
በመሆኑም
የምርጫ ቦርዱ የግለሰቦችን እና የገዥውን
ፓርቲ ፊላጎት ከመወከል እና ከማስጠበቅ
ወጥተው፤ ለአገሪቱ ህገመንግስት ተገዥ በመሆን
ለተግባራዊነቱ ልሰሩ ይገባል። የሲዳማ ህዝብ
የኢትዮጵያ ህገመንግስት መከበር ብሎም ለክልላዊ
አስተዳደር ዳግሞኛ መመስረት የጀመረውን
ተጓድሎ ለአንድም ሰከንድ ልያቋርጥ አይገባም።
Comments
Post a Comment