ሀዋሳ የካቲት14/2011 የሲዳማ ህዝብ የክልል እንሁን ጥያቄውን ዛሬ በሃዋሳ ከተማ ባካሄደው ሰላማዊ ሰልፍ አቀረበ።
ከማለዳው ጀምሮ በተካሄደውና መነሻውን ከሃዋሳ ሪፈራል ሆስፒታል አድርጎ መድረሻውን በአዲሱ የከተማ ስታዲዮም ባደረገው ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ከሲዳማ ዞን 36 ወረዳዎች የተውጣጡ ቁጥራቸው በርካታ ህዝብ ተሳትፏል።
በሰልፉ ላይም ” የሲዳማ የክልል እንሁን ጥያቄ ህገመንግስታዊ ነው “፣ “ያለምልንም ደም ሪፍረንደም “፣ “ላቀረብነው የክልልነት ጥያቄ ሪፈረንደሙ በአስቸኳይ ይካሄድ ” እና ሌሎች መፈክሮችን ተሳታፊዎች ይዘው ወጥተዋል።
ከተሳታፊዎች መካከል የሲዳማ ወጣቶች ተወካይ ወጣት ታሪኩ ለማ “ባለፉት 27 ዓመታት አባቶቻችን የታገሉለት ራስን በራስ የማስተዳደር ዲሞክራሲያዊ ጥያቄ ሀገራዊ ልዕልና አግኝቶ ህዝቡን እኩል ተጠቃሚ ከማድረግ ይልቅ ባህልና ቋንቋችንን የማፈን ሥራ ሲሰራ ቆይቷል” ብሏል።
“ህገመንግስታዊ መብትን በመጠየቃቸውና የሲዳማን የክልል እንሁን ጥያቄ በማንገብ የወጡ በርካታ ወገኖቻችን ለእስራት፣ ለስደትና ለጉዳት ተዳርገዋል” ያለው ወጣት ታሪኩ የህዝቡ ኢኮኖሚያዊ፣ ባህላዊና ስነ ልቦናዊ መስተጋብር እንዲሁም ፖለቲካዊ ጥያቄው ግንዛቤ ውስጥ ሳይገባ መቆየቱን ተናግሯል።
የሀዋሳ ከተማ ምክትል ከንቲባ አቶ ስኳሬ ሹዳ በበኩላቸው እንዳሉት አንድ ዲሞክራሲያዊ ማህበረሰብ መገንባት የሚቻለው ሰጥቶ በመቀበል መርህ፣ በእኩልነትና እኩል በመጠቀም መብት ላይ በመመርኮዝ ነው።
የሲዳማ ህዝብ ላለፉት ዘመናት በተለያዩ ጊዜያት የክልልነትና ራስን በራስ የማስተዳደር መብቱን በህጋዊ መንገድ ለማስከበር ሲጠይቅ እንደነበርና ባለፉት ስርዓቶችም ጭምር ይህን መብቱን ለማስከበር ሲል እስከ ሕይወት መስዋዕትነት የከፈሉ በርካታ ጀግኖች እንዳሉት አስታውሰዋል።
ውጤቱ ቢዘገይም እንኳን ትግል የሚደረገው አንድ ውጤት ለማምጣት በመሆኑ አሁንም ጥያቄ ተጠናክሮ መቀጠሉንና ሰላማዊ ሰልፉ የእዚህ ማሳያ መሆኑን ተናግረዋል።
በሰላማዊ ሰልፍ ላይ የተነሱ የህዝብ ጥያቄና ቅሬታዎችን በየደረጃው ላለው የመንግስት አካል እንደሚያቀርቡ የገለጹት አቶ ስኳሬ፣ ጥያቄያቸው የመጨረሻ ውሳኔ እስኪያገኝ ድረስ አቅም በፈቀደ ሁሉ ከጎናቸው እንደሚቆሙ አረጋግጠዋል።
የሲዳማ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ቃሬ ጫዊቻ በበኩላቸው ” የሲዳማ ህዝብ ጥያቄ ወቅቱንና ህገመንግስቱን መሰረት አድርጎ በሰላማዊ መንገድ የቀረበ የመብት ጥያቄ ነው” ብለዋል።
የዞኑ አስተዳደር ህዝቡ ያነሳውን ጥያቄ ለሚመለከተው አካል እንደሚያቀርብ ገልጸው ጥያቄው ፈጣን ምላሽ እንዲያገኝ የዞኑ አስተዳደር አስፈላጊውን ሁሉ ድጋፍ እንደሚያደርግም አመልክተዋል።
በሰላማዊ ሰልፉ ላይ ከተሳተፉ የህብረተሰብ ክፍሎች መካከል ከሸበዲኖ ወረዳ የመጡት አቶ ብርሀኑ ቢጣላ እንዳሉት ከእዚህ በፊት የህዝቡን ጥያቄ ሲያስተጋቡ የነበሩ ልጆቻቸው ለጉዳት ሲዳረጉ እንደነበር አስታውሰዋል።
በኤጀቶ ሰላም አስከባሪ የሆነው ወጣት ካሳሁን ተረጨ በበኩሉ እንዳለው ሰላማዊ ሰልፉ በሰላም እንዲጠናቀቅ ለማድረግ ኤጀቶ ሰላም በማስከበርና በማስተባበር ስራውን በአግባቡ ሲሰራ ቆይቷል።
ዛሬ በሀዋሳ ከተማ የተካሄደው ሰላማዊ ሰልፍ ያለምንም ችግር በሰላም ተጀምሮ የተጠናቀቀ ሲሆን ቁጥራቸው ከአንድ ሺህ የሚበልጥ ኤጀቶዎች ሰልፉን በማስተባበር ለሰልፉ ሰላማዊነት የበኩላቸውን እገዛ ማድረጋቸውን የዘገበው ኢዜአ ነው።
“ሕገ መንግሰታዊ መብታችን ይከበር” በሚል መሪ ቃል በሀዋሳ ሰላማዊ ሰልፍ እየተካሄደ ነው
ህገ መንግሰታዊ መብታችን ይከበር በሚል መሪ ቃል በሀዋሳ ከተማ ሰላማዊ ሰልፍ እየተካሄደ መሆኑን ተገለፀ።
በሰለማዊ ሰልፉ ከሲዳማ ዞን 36 ወረዳዎች እና ከተማ መስተዳድሮች የተውጣጡ እንዲሁም የሀዋሳ ከተማ ነዋሪዎች የተሳተፉበት ነው።
የሰላማዊ ሰልፉ ተሳታፊዎች “ህገ መንግስታዊ መብታችን ይከበር! የሲዳማ የክልልነት ጥያቄ መልስ ይሰጠው! የሪፈረንደም ቀን ይወሰን !” የሚሉና ሌሎች መፈክሮችን ይዘው ወጥተዋል።
መነሻውን ከሀዋሳ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ ያደረገው ሰላማዊ ሰልፍ በሀዋሳ ዓለምአቀፍ ስታዲየም መዳረሻውን በማድረግ እንደሚጠናቀቅ ተገልጿል።
የደቡብ ክልል ምክር ቤት በጥቅምት ወር ባካሄደው በ10ኛ መደበኛ ጉባኤው የሲዳማ ብሔር በክልልነት የመደራጀት ጥያቄ ተቀብሎ ለህዝበ ውሳኔ ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ መምራቱ ይታወሳል።
walta
ህገመንግሰታዊ መብታችን ይከበር በሚል መሪ ቃል በሀዋሳ ሰለማዊ ሰልፍ እየተደረገ ነው
በሰለማዊ ሰልፉ ከሲዳማ 36 ወረዳዎች እና ከተማ መስተዳድሮች የተውጣጡ እንዲሁም የሀዋሳ ከተማ ነዋሪዎች የተሳተፉበት ነው።
ሰለማዊ ሰልፈኞቹ “ህገ መንግስቱ ይከበር ! የሲዳማ የክልልነት ጥያቄ መልስ ይሰጠው! የሪፈረንደም ቀን ይወሰን !” የሚሉና መሰል መፈክሮችን እያሰሙ ነው።
መነሻውን ከሀዋሳ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ ያደረገው ሰላማዊ ሰልፍ በሀዋሳ ዓለምአቀፍ ስታዲዮም መዳረሻውን በማድረግ እንደሚጠናቀቅ ተገልጿል።
የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ/ደኢህዴን/ ከወራት በፊት ባደረገው በ10ኛ መደበኛ ጉባኤው የሲዳማ ብሔር በክልልነት የመደራጀት ጥያቄ ተቀብሎ ለህዝበ ውሳኔ ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ መምራቱ ይታወሳል።
ebc
Comments
Post a Comment