ስርዓቱ በህገ-መንግስታዊ መብት ጥያቄዎች ውስጥ ጣልቃ መግባቱ የለውጡን አካሄድ ጥያቄ ውስጥ የማስገባት ማሳያ ነው! በሀገራችን ላለፉት 28 አመታት ከልክ ያለፈ አፈናና ጭቆና የዜጎችን ክቡር ህይወትና አካል ካጠፋና ካጎደለ በኋላ በተከፈለው መስዋዕትነት በሀገራችን የመጣዉ አንፃራዊ ለዉጥ ፤የዜጎች ድምጽ የመሰማት ምልክት እየታየ እንደሆነ የማይካድ ሀቅ ነው፡፡ የለውጥ ትሩፋትን ተከትሎ ለዘመናት እየተነሱ በፖለቲካ ጡጫ ሲታፈኑና አይነከ የነበሩ፤ነገር ግን ህገመንግስታዊ የሆኑ ጥያቄዎች መነሳት ተጀምሯል፤ አዳድስ ጥያቄዎችም እነደዚሁ፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ የሲዳማ ህዝብ ላለፉት በርካታ አመታት የታገለለትን፣ የህይወትና የአካል መስዋዕትነት የከፈለበት እራሱን በራሱ የማስተዳደር ጥያቄ እንደገና ተነስቶ አስፈላጊውን ኢፌዴሪ ህገ-መንግስት ቅድመ ሁኔታዎችን ከሟላ በኋላ በደቡብ ክልል ምክር ቤት ወሳኔና ጠያቂነት በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አመቻችነት ህዝበ-ውሳኔ እንዲደረግ ብቻ እየተጠበቀ ይገኛል፡፡ ይሁንና ይህ ታሪካዊ ጥያቄ በኢፌዴሪ ህገ-መንግስት በተመለከተው ጊዜ ገደብ መሰረት ህዝበ ውሳኔ ተደርጎ ሊጠናቀቅ ከሚጠበቀው ጊዜ የቀረው በጣት የሚቆጠሩ ወራት ብቻ ሆኖ ሳለ በደቡብ ክልል ምክር በት በኩል የቁርጠኝነት ማነስና የፖለቲካ ጣልቃ ገብነት በሰፊው እየታየ እንደሆነ ድርጅታችን ገምግሟል፡፡ ይህ ተግባር ህገ-ወጥ ብቻ ሳይሆን እንደቀደሙት ጨለማ ጊዜያት ሁሉ አሁንም የገዢ ፓርቲ ጫና በመንግስት ተቋማት ላይ እያረፈ አንደሆነ የሚያረጋግጥ ነው፡፡ ለአብነትም፡- 1ኛ. በየካቲት 14 ቀን 2011ዓ.ም የህዝቤ-ውሳኔ መዘግየትን ምክንያት ተደርጎ በመላ ሲዳማ የተጠራው ሰላማዊ ሰልፍ እጅግ ፉጹም ሰላማዊ በሆነ አከኋን መደረጉን ምክንያት በማድረግ ከጋዜጠኞች ለብሔራዊ ምርጫ
It's about Sidaama!