የሲዳማ ኤጄቶ አቋም መግለጫ
=====================
#ዛሬ በጥር 20 2011 ኣ/ም ታሪካዊው የሲዳማ ኤጄቶ ሁለተኛ ዙር ጋዶ በሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት መቀመጫ በሆነችው ሀዋሳ በወቅታዊ የህዝባዊን ጥያቄዎች እና ጥያቄው በደረሱበት ደረጃ ላይ ተመክሯል።
=====================
#ዛሬ በጥር 20 2011 ኣ/ም ታሪካዊው የሲዳማ ኤጄቶ ሁለተኛ ዙር ጋዶ በሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት መቀመጫ በሆነችው ሀዋሳ በወቅታዊ የህዝባዊን ጥያቄዎች እና ጥያቄው በደረሱበት ደረጃ ላይ ተመክሯል።
በመሆኑም ኤጄቶ ዛሬም ቢሆን ነገ የሰላም አማባሳደር ነው። የለውጡ መንግስታችንም በግልጽ እንደምያምነው ዘላቂ ሰላም የሚረጋገጠው ለሰላም መደፍረስ ቁልፍ ምክንያት የሚሆኑ ችግሮችን ቀድሞ በመከላከልና ያልተመለሱ ዘመን ዘለቅ የሆኑ ህዝባዊ ጥያቄዎችን ህግን እና ደሞክራሲያዊ መርሆችን ተከትሎ መመለስ ሲቻል መሆኑ ይታመናል፡፡
#በመሆኑም ከዚህ በላይ የሲዳማን ክልል ጥያቄ ህዝበ ውሳኔ ቀን ማራዘም ህዝብ ከመንግስት ጋር ያለውን መተማመን የሚሸረሽር ከመሆኑ ባሻገር የህዝብ ተቋማትን ገለልተኛነትና ህዝባዊ ውግንና ጥያቄ ውስጥ የሚያስገባ በመሆኑ መንግስት አከባቢያችንን ላልተፈለገ ውጥረት እና ስጋት ከሚያስገባ ጸር ህገመንግስታዊ አካሄድ በመቆጠብ አስቼኳይ ምላሽ ይሰጠን ዘንድ እንጠይቃለን።
በማጠቃለያም በዛሬው ጓባኤ ተወያይተን በሚከተሉት አቋሞች ላይ ተስማምተናል።
1 የሲዳማ ህዝብ ራሳችንን ችለን በክልል ልንደራጅ ጥያቄ በቀን 12/11/2010 ዓ.ም በተፃፈው ዳብዳቤ የዞኑ ምክር ቤት አጽድቆ ለደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መ/ ምክር ቤት ጥቅምት 23 ቀን 2011 ዓ.ም አቅርቦ ጥያቄያችን ህገ መንግስታዊ በመሆኑ በክልል ምክር ቤት ፀድቆ ሪፈረንደም እንድካሄድ አቅጣጫ አስቀምጦ ለኢፌዴሪ ምርጫ ቦርድ በቁጥር በቀን 12/3/2011 ዓ.ም በተፃፈው ደብዳቤ ህዝበ ዉሳኔ እንድናከናውን ጠይቀን የህዝበ ውሳኔውን ቀን በመጠባበቅ ላይ እንገኛለን ፡፡
ስለሆነም የሪፈረንደም ቀን በመዘገየቱ ህዝባችን ሌሎች ሰላማዊ የትግል አማራጮችን ለመጠቀም ስለሚገደድ ይህ ከመሆኑ በፍት በአፋጣኝ የረፈረንደም ቀን ይፋ እንድያደርጉልን በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡
2 ባሁን ግዜ የሲዳማ ህዝብ ከዳር እስከ ዳር እንደ ዋና አጀንዳ ይዞ ከሚገኝበት የሪፈረንደም ቀነ ቀጠሮ ውጪ ያለ የትኛውም አጀንዳ በምንም መስፈርት ተቀባይነት የለውም። በዚህም የጄቶን የትግል ወኔና ትኩረት የሚፈታተኑ አጀንዳዎችን ይዘው የሚቀርቡ ሀይሎች አደብ እንዲገዙ እንጠይቃለን።
3 በዚህ ሳምንታት የክልል ብሎም የሁለቱም መዋቅር አመራሮች የክልል ጥያቄያችን በደረሰበት ደረጃ ላይ አስቼኳይ መግለጫ ወይም ምላሽ እንዲሰጡን በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡
4 ለክልል ማቋቋሚያነት የተሰየምው ታስክ ፎርስ ሌሎች ቅድመ ዝግጅቶችም እስካሁን የደረሰበትን ደረጃ ለህዝብ ይፋ እንዲያደርግ እንጠይቃለን፡፡
#በመጨረሻም የተከበራችሁ የሀዋሳ ከተማ ነዋሪዎች የደቡብ ክልል ህዝቦች ብሎም መላው የኢትዮጵያ ህዝቦች የሲዳማን ህዝብ አቃፊነት እና እንግዳ አክባሪነት ከናንተ በላይ የሚመሰክር አለመኖሩ ለሁሉም ግልጽ ነው።
የናንተና የኛ ትስስር በደቡብ ክልል ህልውና ላይ የተመሰረት ባለመሆኑ ክልሉ ብፈርስ አንድነታችን የሚሸረሸርበት ምንም ምክንያት አይኖርም። #ከዚህ መነሻም ከሲዳማ ህዝብ ጥያቄ ጋር በመሰለፍ ኤጄቶ ከጸረ ህዝብ እና ጸረ ህገመንግስት ሀይሎች ጋር እያደረገ ያለውን ትግል እንድትቀላቀሉ ጥሪ እናቀርባለን።
#ኤጄቶ
#ሀዋሳ_ሲዳማ_ኢትዮጵያ🇪🇹
#ኤጄቶ
#ሀዋሳ_ሲዳማ_ኢትዮጵያ🇪🇹
Comments
Post a Comment