Skip to main content

የጊዳቦ ግድብ ምርቃት ለሁለተኛ ጊዜ ተራዝሟል

በዚህ ዓመት የሦስት መስኖ ግድቦች ግንባታ እንደሚጠናቀቅ ይጠበቃል

የመስኖ ውኃ ታሪፍ እየተዘጋጀለት ነው

ለበርካታ ዓመታት ሲጓተቱ ከቆዩት የመስኖ ግድብ ግንባታዎች ውስጥ በሰሜኑ ክፍል ግንባታቸው የሚገኙ ሦስት የመስኖ ግድቦች በዚህ ዓመት ሊጠናቀቁ እንደሚችሉ ተገለጸ፡፡
የውኃ መስኖና ኤሌክትሪክ ሚኒስቴር ለሪፖርተር እንዳስታወቀው፣ በዚህ ዓመት ግንባታቸው እንደሚጠናቀቁ የሚጠበቁት የርብ፣ የመገጭና የዛሬማ መስኖ ግድቦች ናቸው፡፡ የሚኒስቴሩ የሕዝብ ግንኙነትና የኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ብዙነህ ቶልቻ እንደጠቀሱት፣ በዚህ ዓመት እንዲጠናቀቁ ከሚጠበቁት መካከል የመገጭ ሳርባ፣ የርብ መስኖ አውታርና የዛሬማ ማዕዴን የመስኖ ልማት ፕሮጀክቶች በዚህ ዓመት እንደሚጠናቀቁ ተስፋ የሚደረጉት ናቸው፡፡ መገጭ ሳርባ 4,000 ሔክታር የአርሶ አደር ማሳ የሚያለማ ሲሆን፣ የርብ ግድብም 3,000 ሔክታር የአርሶ አደሮች መሬትን የማልማት አቅም ያለው የመስኖ አውታር ነው፡፡
በአማራ ክልል ደቡብ ጎንደር ዞን፣ ፋርጣ ወረዳ 2000 .የተጀመረው የርብ መስኖ ልማት ግድብ፣ ከአሥር ዓመታት በኋላ ግንባታው ተጠናቆ ጥቅምት 18 ቀን 2011 .በይፋ መመረቁ ይታወሳል፡፡ ይህ ፕሮጀክት 2000 .በአራት ዓመት ውስጥ ይጠናቀቃል ቢባልም፣ ግንባታው በተለያዩ ችግሮች ለስድስትዓመታት ዘግይቷል፡፡
ፕሮጀክቱ 1.6 ቢሊዮን ብር በጀት የተጀመረ ቢሆንም ግንባታው በተያዘለት ጊዜ ገደብ ባለመጠናቀቁ፣ በጀቱ እስካለፈው ዓመት ጥቅምት 2010 .ድረስ3.7 ቢሊዮን ብር መድረሱ ታውቋል፡፡ የግድቡን የዲዛይንና የቁጥጥር ሥራውን ያካሄደው የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ዲዛይንና ቁጥጥር ኮርፖሬሽን ሲሆን፣ግንባታውን ደግሞ የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን አከናውኖታል፡፡
የርብ መስኖ ልማት ግድብ የዘገየው በዲዛይን ለውጥ፣ በተቋራጩና በአማካሪ ድርጅቱ አቅም ውስንነትና ልምድ ማነስ፣ በውኃ መስኖና ኤሌክትሪክ ሚኒስቴርአስተዳደር ችግርና በግንባታ ዕቃዎች አቅርቦት እጥረት ምክንያት እንደነበር ሲገለጽ ቆይቷል፡፡ ይሁን እንጂ የግድቡ ሥራ ሙሉ ለሙሉ ተጠናቆና የውኃ ማስተላለፊያ ቦዮቹ ግንባታ አልቆ ተገቢውን አገልግሎት መስጠት የሚጀመረው በዚህ ዓመት መጨረሻ ሊሆን እንደሚችል ተገልጿል፡፡
በኢትዮጵያ በርካታ ግዙፍ ፕሮጀክቶች በየጊዜው ቢጀመሩም በተያዘላቸው የጊዜ ገደብና በጀት ስለማይጠናቀቁ ከፍተኛ ክስረት እያስከተሉ ይገኛሉ፡፡ ይህ በመሆኑም ብሔራዊ ፕላን ኮሚሽን ትልልቅ ፕሮጀክቶች ከመጀመራቸው በፊት ሰፊ ጥናትና ዝግጅት እንዲረግባቸው ኃላፊነት እንደተሰጠው የሚታወስ ነው፡፡
የጊዳቦ ግድብ በታኅሳስ ወር ሥራው ተጠናቆ እንደሚመረቅ መርሐ ግብር ቢያዝለትም ሳይካሄድ ቀርቷል፡፡ ለጥር 14 ቀን 2011 ዓ.ም. የተያዘው መርሐ ግብርም ጥር 11 ቀን 2011 ዓ.ም. በድንገት በተላለፈ መረጃ መሠረት እንዲራዘም ተደርጓል፡፡ ይሁን መቼ እንደሚካሄድ አልታወቀም፡፡ መገኘት ያለባቸው ኃላፊዎችና ወቅታዊ ሁኔታዎች ተደማምረው ለምርቃቱ መራዘም ሰበብ መሆናቸው ታውቋል፡፡
በሁለት ዓመታት ውስጥ ግንባታው እንደሚጠናቀቅ ታቅዶና 258 ሚሊዮን ብር በጀት የተጀመረው የጊዳቦ መስኖ ልማትና ግድብ ግንባታ ፕሮጀክት፣ ከስምንትዓመታት መጓተት በኋላ 1.66 ቢሊዮን ብር መጠናቀቁን መዘገባችን ይታወሳል፡፡ 2002 .ግንባታው የተጀመረው የጊዳቦ ግድብና መስኖ ልማትፕሮጀክት፣ እንዲጓተት ካስገደዱት ምክንያቶች መካከል መሠረታዊ የዲዛይን ለውጦች መደረጋቸው ሲሆን፣ የፕሮጀክቱ ግንባታ ከተፈረመ በኋላ ለሁለት ዓመታትግንባታው ሳይጀመር መጓተቱም ለዋጋ ንረት እንደፈጠረ የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን ይፋ አድርጓል፡፡
ኮርፖሬሽኑ ሦስት ተቋማትን በመጠቅለል ከተቋቋመ ከሦስት ዓመታት ወዲህ ከተረከባቸው ፕሮጀክቶች አንዱ የሆነው የጊዳቦ መስኖ ልማትና ግድብ ሥራፕሮጀክት፣ በግንባታ ጥሬ ዕቃዎች እጥረት፣ በተቋማት ቅንጅታዊ አሠራር መጓደል፣ በካሳ ክፍያዎችና በሌሎችም ምክንያቶች በሁለት ዓመታት እንዲጠናቀቅየተቀመጠለት ጊዜ ከመጓተቱም ባሻገር ወጪውም 645 በመቶ ገደማ ጨምሮ ሊጠናቀቅ ችሏል፡፡
ፕሮጀክቱ ከመነሻው ከታቀደው 16 ሜትር የግድብ ከፍታ ወደ 22.5 ሜትር ተሻሽሎ እንዲሠራ መደረጉን ኮርፖሬሽኑ አስታውቆ፣ ከሰባት ኪሎ ሜትር በላይየሚዘረጋ የውኃ መተኛ ቦታ 315 ሜትር ርዝማኔ ኖሮት እንዲገነባ መደረጉንም የኮርፖሬሽኑ መረጃ ይጠቁማል፡፡ በግድቡ 63 ሚሊዮን ኪዩቢክ ሜትር በላይውኃ የመያዝ አቅም እንዲኖረው ተደርጎ በመገንባቱ 13.5 ሺሕ ሔክታር መሬት በመስኖ ለማልማት እንደሚያስችል ታውቋል፡፡
መንግሥት ለመስኖ ልማት አውታሮቹ ግንባታ ያወጣውን ወጪ ለእርሻ ማሳያዎች ከሚያቀርበው ውኃ በታሪፍ በማስከፈል ገቢ የመሰብሰብ ዕቅድ አለው፡፡ በመሆኑም የመስኖ ውኃ ታሪፍ እንዴት እንደሚወሰንና በምን አግባብ እንደሚያስከፍል የሚደነግግ ዝርዝር ረቂቅ ሕግ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት መላኩን ከኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን የተገኘው መረጃ ይጠቁማል፡፡ ይሁንና የመስኖ ምሕንድስና ባለሙያዎች ግን እንዲህ ያለው መረጃ በአግባቡ እንዲደርሰው መደረግ እንዳለበትና ለሚቀርብለት የመስኖ ውኃ የሚከፍልበት አካሄድ ሊኖር እንደሚችል የሚገልጹ ዝግጅቶች ከወዲሁ ሊደረጉ እንደሚገባቸው ያሳስባሉ፡፡

Comments

Popular Posts

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የመንግሥት ስልጠና የምርጫ ቅስቀሳ አካል ነው ብሏል  የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ለምን ወጣ መባሉ ተገቢ አይደለም - ምርጫ ቦርድ ምርጫ ቦርድ ከኢህአዴግ ተፅዕኖ ሙሉ ለሙሉ ነፃ መሆኑ ሳይረጋገጥና የምርጫ አፈፃፀም ችግሮች ሳይወገዱ የምርጫ የጊዜ ሰሌዳ ለማወጅ መዘጋጀቱ ተገቢ አይደለም ሲል ፕ/ር በየነ ጴጥሮስ የሚመሩት ኢማዴ-ደህአፓ ተቃወመ፡፡ መንግስት፤ የዩኒቨርሲቲ መምህራንና ተማሪዎችን ጨምሮ ለተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች እየሰጠ ያለው ስልጠና የምርጫ ቅስቀሳ አካል ነው ሲልም ፓርቲው ኮንኗል፡፡  የኢትዮጵያ ማህበረ ዴሞክራሲ ደቡብ ህዝቦች አንድነት ፓርቲ ሰሞኑን ለብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ባስገባው ግልፅ ደብዳቤ፤ ያለፉት አገር አቀፍና የአካባቢ ምርጫዎች ከመካሄዳቸው በፊት በምርጫ ችግሮችና መፍትሄዎቻቸው ዙሪያ ኢህአዴግ ከተቃዋሚዎች ጋር የሚወያይበት መድረክ እንዲዘጋጅ በተደጋጋሚ ብንጠይቅም እስካሁን ከቦርዱ የተሰጠ ተግባራዊ ምላሽ የለም ብሏል፡፡  ሃገሪቱ “በአንድ አውራ ፓርቲ” ብቸኛ ቁጥጥር ስር መውደቋ አደገኛና አሳሳቢ ነው ያለው ፓርቲው፤ የመድብለ ፓርቲ ስርአት የመገንባት ተስፋችን ጨርሶ እንዳይከስም ቦርዱ ሃላፊነቱን መወጣት እንዳለበት አሳስቧል፡፡ ነፃና ፍትሃዊ ምርጫ የሚካሄድበትን ሁኔታ ለመፍጠር ገዥው ፓርቲና ሃቀኛ ተቃዋሚ ፓርቲዎች የሚወያዩበት መድረክ እንዲያመቻች በህግ ስልጣን የተሰጠው ምርጫ ቦርድ የገባውን ቃል በማጠፍ መድረኩን ሳያመቻች የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማዘጋጀቱ ፋይዳ የለውም ብሏል - ፓርቲው፡፡  ገዥው ፓርቲ ኢህአዴግ በተሻሻለው የምርጫ ህግ፣ ለቦርዱ የተሰጠውን የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ መድረክ የማስተባበር ስልጣን ለመቀማት ታማኝ ፓርቲዎችን በተቃዋሚ ስም አሰባስቦ “የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ መድረክ” በመፍጠር የምርጫ ውድድር አሯሯጭ አሰልፏል ሲ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

የለበሰው ያደፈ ቁምጣና ሹራብ ከቅዝቃዜው አላዳነውም፡፡ ካፊያው ልብሱን አርሶታል፡፡ ሽው እያለ ከሐይቁ የሚነሳው ነፋስ የሚፈጥረው ቅዝቃዜ ያንቀጠቅጠዋል፡፡ የተጫማው ያረጀ ሲሊፐር እግሩን ከምንም አላዳነውም፡፡ በባዶ እግሩ የሚራመድ ያህል ጨቅይቷል፡፡ ተደባዳቢ ይመስል ፊቱ የተሞነጫጨረ ነው፡፡ ገና 12 ዓመቱ ቢሆንም፣ ቁመናው እንደ ትልቅ ሰው ግዙፍ ነው፡፡ የሚለብሰውን እንደ ልቡ ባያገኝም፣ የሚያስፈልገውን ነገር ለማሟላት ቤሳቢስቲን የሌላቸው ወላጆቹን አያስቸግርም፡፡ ከቤተሰቦቹ ጋር ከሚኖሩበት ታቦር ተራራ ጀርባ ወዳለው ሐዋሳ ሐይቅ ከወረደ እንኳንስ የራሱን የቤተሰቦቹንም የዕለት ጉርስ የሚሸፍንበት ገንዘብ አያጣም፡፡ የአስጎብኚነት ዕውቀት፣ ከሐይቁም ውስጥ ዓሳ የሚያጠምድበት መረብም ሆነ ፈቃድ የለውም፡፡ ሙሉቀን (ስሙ ተቀይሯል) እና ጓደኞቹ ሐይቁን ለመጎብኘት የሚሄዱ ጎብኚዎች በካሜራቸው ጥሩ ፎቶ እንዲያስቀሩ ድባቡን የማሳመር ሥራ ይሠራሉ፡፡ ካሜራውን ይዞ ቁጭ ብድግ እያለ ጥሩ ፎቶ ለማንሳት ጥረት የሚያደርግ ሲያዩ፣ ቆርጠው የያዙትን የዓሳ ሥጋ ይዘው ጠጋ ጠጋ ይላሉ፡፡ ቁርጥራጩን የዓሳ ሥጋ ምግብ ለሚቀሙት አባኮዳዎች ሻሞ ይላሉ፡፡ የተወረወረላቸውን ቀድመው ለመቅለብ አባኮዳዎቹ ክንፋቸውን እየመቱ ወደ ላይ ብድግ ይላሉ፡፡ የናሽናል ጆግሪፊ የፎቶግራፍ ባለሙያዎች ያነሱት ዓይነት ፎቶዎች ሳያስቡት ያነሳሉ፡፡ በሁኔታው ተደስተው ደጋግመው ድንቅ ፎቶዎችን ለመውሰድ ሲዘጋጁ እነ ሙሉቀንም አጀንዳቸውን ይፋ ማድረግ ይጀምራሉ፡፡ አቶ ዳዊት አብርሃም ‹‹አንዱን ዓሳ በአሥር ብር ገዝቼ ነው እንዲህ የማዘጋጀው፤›› በማለት በቅድሚያ  መረጃ ይሰጣሉ፡፡ ለቀጣዩ ዜና በዚህ መልኩ እንዲዘጋጁ ካደረጉ በኋላ፣ ሌሎች ሰዎች መቶም ሁለት መቶም ብር እንደሚሰጧቸው ቀለል

Sidama: the Luwa and the Anga Culture and their Social Implications

By Wolassa Kumo 1. Introduction In my previous articles, I mentioned the Sidama grand social constitution Seera, and various sub constitutions which derive from this grand constitution. We have also seen that all social constitutions or Seera in Sidama were based on the Sidama moral code of halale, the true way of life. In this socio-cultural and socio-political system, the role of the elders was very important. Elders were bestowed with the power of enforcing the Seera and referring the recalcitrant to Magano or God if he/she refuses to abide by the Seera. The power of elders in the Sidama society was not based on a simple age count as is the case in most modern societies. The Sidama elder is more the product of various social processes through which he passes than the product of a simple aging. For a person to become a recognised elder with authority in Sidama, he has to become a Cimeessa (respected elder with authority) or Cimeeyye for many respected elders. There are three importa