(ኤፍ.ቢ.ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ከሀዋሳ ከተማ ወጣቶች ጋር ተወያዩ። ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ በውይይታቸው ለሀዋሳ ከተማ ወጣቶች እንደተናገሩት ኢትዮጵያዊነት ከፍታ ነው ብለዋል። የከፍታችን ዋና ምሰሶው ፍቅር ሲሆን፥ ሀዋሳ ከተማ የተለያዩ ብሄር ብሄረሰቦች በመተሳሰብ እና በመፈቃቀድ ከፍታቸውን ጠብቀው በጋራ የሚኖሩባትና በምሳሌነትም የምትጠቀስ ከተማ ነች ብለዋል። የሀዋሳ ከተማ ወጣቶች ይህን አረዓያነት የማስቀጠል ኃላፊነት እንደለባቸውም አሳስበዋል። ወጣቱ ትውልድ ተራራ ለመውጣት ብሎም አስፈለጊ ሆኖ ሲገኝ መናድ የሚችለው ኢትዮጵያዊ ከፍታውን ሲጠብቅ ብቻ ነውም ብለዋል። አልፎ አልፎ ከዚህ ከፍታችን የሚያወርዱ ትርክቶች ተከትሎ የሚፈጠሩ ችግሮች ለችግር የሚዳርጉ መሆናቸውን አስገንዝበዋል። እነዚህን ችግሮች ለማስወገድ ደግሞ አብሮነት፣ ፍቅር መተሳሰብ፣ መፈቃቀድ መሆኑን ነው ያመላከቱት። አባቶቻችን የኢትዮጵያ ዳር ድንበር በማስከበር የተዋደቁት የኢትዮጵያን ከፍታ ለዚህ ትውልድ ለማስተላለፍ ነው ብለዋል። ምንጭ
It's about Sidaama!