የኢህአዴግ ሊቀ መንበር ዶ/ር አብይ አህመድ ለድርጅታዊ ጉባዔው ሀዋሳ ከተማ ገቡ

(ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢህአዴግ ሊቀ መንበርና የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በ11ኛው የኢህአዴግ ድርጅታዊ ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ ሀዋሳ ከተማ ገብተዋል።
11ኛው የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢህአዴግ) ድርጅታዊ ጉባዔ “ሀገራዊ አንድነት ለሁለንተናዊ ብልፅግና” በሚል መሪ ቃል ከነገ ጀምሮ በሀዋሳ ከተማ ይካሄዳል።
በድርጅታዊ ጉባዔው ላይ ለመሳተፍም የኢህአዴግ ሊቀ መንበርና የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በዛሬው እለት ሀዋሳ ከተማ ገብተዋል።
በተጨማሪም የኢህአዴግ ምክትል ሊቀ መንበርና የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር አቶ ደመቀ መኮንን ድርጅታዊ ጉባዔው ላይ ለመሳተፍ ሀዋሳ ደርሰዋል።
እንዲሁም የኢህአዴግ ድርጅታዊ ጉባኤ ተሳታፊዎችም ሃዋሳ ከተማ መድረሳቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ልዩ ሀላፊ አቶ ፍፁም አረጋ አስታውቀዋል።
11ኛው የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢህአዴግ) 11ኛ ድርጅታዊ ጉባዔ ነገ ጠዋት ላይ በሀዋሳ ከተማ እንደሚጀምር ይጠበቃል::

No comments