በአለማችን ላይ የሚገኙትን ጎሳዎች በተመለክተ የወጣው አንድ ጽሁፍ የሲዳማ ህዝብ ቁጥር ከ8 ነጥብ 5 ሚሊዮን በላይ መሆኑን አመለከተ


በዛሬው እለት በአለማችን ላይ በወቅቱ በጎሳነት ስለሚታወቁ ህዝቦች በተመለከተ የወጣው አንድ ጽሁፍ እንዳመለከተው፤ በኢትዮጵያ ካሉ ጎሳዎች መካከል አንዱ የሆነው ሲዳማ፤ በቁጥር ከ 8 ነጥብ 5 ሚሊዮን በላይ መሆንን አመልክቷል።

እንደጽሁፉ ከሆነ በኢትዮጵያን እና በኤሪትራ የሚገኘው የትግራይ ህዝብ አንድ ላይ ተደምሮ የሲዳማን ህዝብ በቁጥር አይበልጥም። በሁሉቱም አገራት የሚኖረው የትግሬ ህዝብ ቁጥር ብበዛ 9 ሚሊዮን ነው ተብሏል።  

የኢትዮጵያ መንግስት በተለያዩ ጊዚያት የሲዳማን ህዝብ ቁጥር በተመለከተ የሚያወጣቸው መረጃዎች፤ የህዝቡን ቁጥር ከአራት ሚሊዮን በማሳነስ እንደሚያቀርቡት ይታወቃል። የአገሪቱ መንግስት የህዝቡን ቁጥር በእጅጉ አሳንሶ በማቅረቡ የተነሳ፤ የሲዳማ ህዝብ፤ የህዝብን ቁጥር ከግንዛቤ ውስጥ በማስገባት በሚመደበው ባጄት ተጠቅሚ እንዳይሆን እንዳደረገው መረዳት ይቻላል።

አዲሱ አመራር ትክክለኛውን የሲዳማ ህዝብ ቁጥር በውሉ በመገንዘብ፤ የሚገባውን የልማት እና የመልካም አስተዳደር ስራዎች በአግባቡ ብፈጽም መልካም ነው።


No comments