በሴካፋ ከ17 ዓመት በታች ዋንጫ ማጣሪያ የኢትዮጵያ ታዳጊ ብሄራዊ ቡድን የኬንያ አቻውን አሸነፈ።
በታንዛኒያ አዘጋጅነት እየተካሄደ በሚገኘው ከ17 አመት በታች የሴካፋ ሻምፒዮና እየተሳተፈ የሚገኘው ታዳጊ ቡድኑ የዛሬውን ጨዋታ 4 ለ 2 አሸንፏል።
ይህን ተከትሎም ምድቡን በ12 ነጥብ በበላይነት በማጠናቀቅ ግማሽ ፍጻሜውን መቀላቀሉን አረጋግጧል።
በሌላ የምድቡ ጨዋታ ኡጋንዳ ጂቡቲን 8 ለ 0 በማሸነፍ ቀይ ቀበሮዎችን ተከትላ ግማሽ ፍጻሜውን ተቀላቅላለች።
ታዳጊ ቡድኑ በመጭው ቅዳሜ ወደ ፍፃሜ ለማለፍ ከሩዋንዳ አቻው ጋር ጨዋታውን ያደርጋል።
ምንጭ፦ (ኤፍ ቢ ሲ)
Comments
Post a Comment