Skip to main content

Posts

Showing posts from July, 2018

የሀይማኖትን ካባ ለብሶ በሀዋሳ ነዋሪዎች ላይም ሆነ በሲዳማ ብሔር ላይ የተሳሳተ መልዕክት ለማስተላለፍ የሚደረግ ማንኛውም ሙከራ ይቁም! ፖስተር ዮናታን ምን ነካው?

ፖስተር  ዮናታን ምን ነካው? ፖስተር  ዮናታን ምን ነካው? :::::::::::::::::::::::::::::::::::::: የማር-ሲል ቴለቭዥን ፖስተር ዮናታን መልካም ወጣት 2010 በምል በ5 ዙር 25,000 ወጣቶችን እያሰለጠነ ነው፡፡ ብያንስ አስተያየት ሳልሰጥ አይቼ እንዳላየ ማለፍ አልቻልኩም ፡፡ ነገሩ ወዲህ ነው ዛሬ ፍተ ልውጥ የሆኑ ወጣቶች "ዘረኝነትን እፀየፋለሁ!" በሚል በኦሬንጅ ቲ-ሸርት ሀዋሳን አጥለቀለቀዋታል፡፡ ታዲያ ምን ችግር አለው? ችግሩ ግልፅ ነው፡፡ ከወር በፊት በተቀነባበረ ሴራ በሀዋሳ ከተማ በሲዳማና ወላይታ መሀል ግጭት ተቀስቅሶ የሰው ህይወት ጠፍቷል ፡፡ የሲዳማ ልጆች ወላይታወቹን ስያጠቁ የሚያሳይ የተቀነባበረና በጥንቃቄ የተሰራ ቭድዮ በመላው አለም ተሰራጭቷል ፡፡ በሁለቱም ወገኖች የሰው ህይወት ብጠፋም ፣ በአንድ ወገን ብቻ ግድያ እንደተፈፀመ ተደርጎ ለማሳየት ተሞክሯል ፡፡ ከሶዶ ዩኒቬርስቲ ሴት እህቶቻችን ከፎቅ ላይ ስወረወሩና በሳንጃ ተወግተው ስገደሉ ፣ ከቤት ተጠርተው በወላይታ ተወላጅ ፖሊሶች ተደብድበው ስገደሉ የሚያሳይ ቭድዮ አልተቀረፀም፡፡ ሌላም የሲዳማ ብሔር ዘረኛ እንደሆነና በውስጡ ያሉትን ብሔሮች እንደምያጠቃና እንደምያባርር ተደርጎ ተቀነባብሯል፡፡ በጣም ያሳዝናል የሲዳማ ብሔር በፍፁም ዘረኛ የሚባል አይደለም ፡፡ በኢትዮጵያ ውስጥ ከየትኛውም የተሻለ ሁሉንም አቅፎ በሰላም የሚኖር ብሔር ነው እንጂ፡፡ ስበደል እራሱ "ዲአፍኒ" ሳይል ለውሳኔ አይቸኩልም፡፡የሀዋሳ ከተማ ከ70 ብሔረሰብ በላይ በውስጣ ይዛ የፍቅር ከተማ የተባለችው ለምን ሆነና ነው ? ለምሊኔም የኖረበትን ምድር የእኛ ነው እስክባል ታግሷል፡፡ ዛሬ ላይ ሀዋሳና ሲዳማ ውስጥ ዘረኝነት እንዳለ ለማስመ

ሃዌላ: የሲዳማ አርሶ አደሮች ተገቢውን የገበያ ትስስር በማጣታቸው የተነሳ ለእንግልት ተዳርገዋል

ከሃዌላ ሙራንቾ ቁጣላ ቀበሌ ከሌሊቱ 11 ሰአት ላይ ወደ ሃዋሳ የመጡት፤ እኝህ የአራት ልጆች አባት ካላ ሌሊሶ ሌዳሞ የማንጎ ችግኝ፤ በሶ ብላ እና የእንሰት ችግኝ ይዘው በሃዋሳ ከተማ መንገዶች በመዘዋወር እና በጓሮአቸው ያለሙትን እነዚህን የግብርና ምርቶች በመሽጠት ይተዳደራሉ። መንግስት ለሲዳማ አርሶ አደሮች ተገቢውን የገበያ ትስስር መፍጠር ባለመቻሉ የተነሳ ካላ ሌሊሶ ከሌሊቱ 11 ሰአት ላይ ጉዞ ወደ ሃዋሳ እንዲደርጉ እና ቀኑን ሙሉ በከተማዋ መንገዶች በመዘዋወር የግብርና ምርቶቻቸውን እንዲሽጡ በመገደዳቸው፤ አገሪቱ በምግብ ዋስትና እራሷን እንድትችል ለማድረግ ያለባቸውን ሃላፊነት መወጣት አልቻሉም።

የሲዳማ አርሶ አደሮች ተገቢውን የገበያ ትስስር በማጣታቸው የተነሳ ለእንግልት ተዳርገዋል

ከሃዌላ ሙራንቾ ቁጣላ ቀበሌ ከሌሊቱ 11 ሰአት ላይ ወደ ሃዋሳ የመጡት፤ እኝህ የአራት ልጆች አባት ካላ ሌሊሶ ሌዳሞ የማንጎ ችግኝ፤ በሶ ብላ እና የእንሰት ችግኝ ይዘው በሃዋሳ ከተማ መንገዶች በመዘዋወር እና በጓሮአቸው ያለሙትን እነዚህን የግብርና ምርቶች በመሽጠት ይተዳደራሉ። መንግስት ለሲዳማ አርሶ አደሮች ተገቢውን የገበያ ትስስር መፍጠር ባለመቻሉ የተነሳ ካላ ሌሊሶ ከሌሊቱ 11 ሰአት ላይ ጉዞ ወደ ሃዋሳ እንዲደርጉ እና ቀኑን ሙሉ በከተማዋ መንገዶች በመዘዋወር የግብርና ምርቶቻቸውን እንዲሽጡ በመገደዳቸው፤ አገሪቱ በምግብ ዋስትና እራሷን እንድትችል ለማድረግ ያለባቸውን ሃላፊነት መወጣት አልቻሉም። የ ምስል ምንጭ

የብሔራዊ የፖለቲካ ድርጅቶች የምክክር መድረክ በሀዋሳ አደረጉ፡፡

በሀዋሳ ከተማ ዘላቂ የሆነ ሰላም እንድፈጠር እና በቅርቡ በተፈጠረው የፀጥታ መደፍረስ ምክንያት የተፈጠረውን የልማትና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ዘላቂነት ባለው መልኩ ለመፍታት በከተማችን ከሚገኙ የሀገራችን ብሄራዊ ድርጅቶች መካከል የኦህዴድ፣ የብአዴን፣እና የህዋሃት አደረጃጀቶች አመራር ጋር የምከከር መድረክ ተካህዷል።  በውይይቱ በርካታ ገንቢ አስተያዬቶች የተሰጡ ሲሆን በከተማ አስተዳደሩ የተፈጠረውን ያልተጠበቀ የፀጥታ ችግር ብዙ ጊዜ ሳይቆይ መፈታቱን በማድነቅ በአሁኑ ጊዜ በየ ጊዜያዊ ማቆያ ጣቢያዎች የሚገኙ ከቤታቸው እና ከተከራዩበት ቤት ተፈናቅለው የሚገኙትን ወደ ነበሩበት ለመመለስ የሚደረገውን ጥረትም ሆነ ስለ ከተማው ወቅታዊ ስራ እቅድ መሳካት የበኲላቸውን ድርሻ ለመወጣት ቃል ገብቷል።  ከዚህ ጋር ተያይዘውም የከተማችን አመራርም በቀጣይ አሁን የተጀመረው የጋራ መድረክ ተጠናክሮ እንድቀጥል እንደሚሰሩ ቃል በመግባት መድረኩ ተጠናቋል። ዜናው የሃዋሳ ከተማ ኢንፎርሚርሽን እና ኮሚኒኬሽን መምሪያ ነው 

የሃዋሳ ከተማ አስተዳደር በነካ እጁ የደቡብ ሬዲዮ እና ቴሌቪዥንን ከመሰል ጸረ ሲዳማ ፕሮፖጋንዳ እንድታቀቡ እና ለህዝቦች አንድነት እና ሰላም እንዲሰሩ ቢያሳስቡልን

በማህበራዊ ሚዲያ ላይ በታዋቂ የሚዲያ አውታሮች ስሞች በተከፈቱት የውሽት ገጾች የሚካሄደውን ጸረ ሲዳማ ፕሮፖጋንዳ ለማስቆም ለሚመለከታቸው አካላት ጥሪ ቀረበ የሃዋሳ ከተማ አስተዳደር፤ብሄሮች እና ብሄረሰቦች በሰላም በሚኖሩባት የሃዋሳ ከተማ የብሄር ግጭቶችን ለመቀስቀስ አላማ ያደረጉ በማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ላይ የተለያዩ ታዋቂ የሚዲያ አውታሮችን  ስያሜ በመጠቀም የምሰራጭ የተሳሳተ መረጃ ለማስቆም ይቻል ዘንድ ለሚመለከታቸው አካላት በደብዳቤ ጥሪ አቅርቧል። የከተማው አስተዳደር በጻፈው ደብዳቤ ላይ፤ በሰማቸው የተሳሳተ መረጃ ሲዳማን እና ከተማዋን በተመለከተ ተሰራጭቷል በማለት በማስረጃ አስደግፎ አቅርቧል። በደብዳቤው ውስጥ ስማቸው በተጠቀሱት የዜና ድርጅቶች ስም በተከፈቱ የውሽት የፌስ ቡክ አካውንቶች የከተማዋን ሰላም ለማደፈረስ የሚስሩ አካላት መኖራቸውን የሲዳማ አክትቪስቶች በተደጋጋሚ ከዚህ በፊት አጋልጠዋል። የከተማዋ አስተዳደር ከወራቶች በሓላም ብሆን መሰል እርምጃ መውሰዳቸው መልካም ሆኖ፤ በማህበራዊ ሚዲያ ገጿች ላይ ብቻ ሳይሆን እዛው በከተማው የከተሙት የክልሉ ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን የበኩላቸውን የከተማዋን ሰላም የማናጋት ተግባር በመፈጸም ላይ በመሆናቸው አንድ ልባሉ ይገባል። የሃዋሳ ከተማ አስተዳደር በነካ እጁ የደቡብ ሬዲዮ እና ቴሌቪዥንን ከመሰል ጸረ ሲዳማ ፕሮፖጋንዳ እንድታቀቡ እና ለህዝቦች አንድነት እና ሰላም እንዲሰሩ ቢያሳስቡልን መልካም ነው። የከተማዋን አስተዳደር ደብዳቤ ከታች አቅርበነዋል ያንቡት፤

በኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን ላይ ተገንብቶ የቆየው የመጀመሪያው የጥላቻ ግንብ ተንዷል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ

አዲስ አበባ 19/2010 በኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን መካከል ተገንብቶ የቆየው የጥላቻ ግንብ መናዱን የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ገለጹ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን ያሉት በአሜሪካ ዋሺንግተን ዲሲ እየተካሄደ ባለው በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ-ክርስቲያን የሚገኙ ሁለት ሲኖዶሶች መካከል ያለውን አለመግባባት ለመፍታት የተዘጋጀው የሰላም ማብሰሪያ ጉባኤ ላይ ነው። ዶክተር አብይ እንዳሉት የዛሬው ጉባኤ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን ላይ ተገንብቶ የቆየው የመጀመሪያው የጥላቻ ግንብ መናዱን በይፋ የሚያበስር ነው። የዚህ ግንብ መፍረስ የሚያመላክተው በፖለቲካ፣ በዘርና በተለያየ ጥቅማ ጥቅም ልዩነቱን ያሰፉት ጉዳዮች መናድ ጭምር ነው ብለዋል። ሁላችንም በጋራ ተባብረን ፖለቲካችን፣ ሃይማኖታችን፣ ብሔራችን፣ ቋንቋችንና ኢትዮጵያዊነታችን በአንድ ጥላ ስር እንደሚታይ ተስፋ አለኝ ብለዋል። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ-ክርስቲያን ራሷን ከማስታረቅ አልፋ ኢትዮጵያን ወደ አንድነትና የመደመር ጉዞ በማምራት እየተካሄደ ባለው ጥረት የበኩሏን ስራ እንደምታከናውንም እምነታቸው እንደሆነ ተናግረዋል። በቀጣይ የሁለቱ ሲኖዶሶች የሰላም ማብሰሪያ ጉባኤም በሚሊኒየም አዳራሽ እንደሚካሄድ አመልክተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በእርቀ ሰላሙ ሂደት አስተዋጽኦ ላደረጉት አካላትም ምስጋናቸውን  አቅርበዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዋሽንግተን ዳላስ አየር ማረፊያ ሲደርሱም በአሜሪካ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር አምባሳደር ካሳ ተክለብርሃንን ጨምሮ በአሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሎስ አንጀለስና በዋሽንግተን ዲ ሲ በሚኖራቸው ቆይታም ከኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ጋር ይወያ

በቁልቢ እና ሃዋሳ ዓመታዊው የቅዱስ ገብርኤል ንግስ በዓል በደማቅ ስነ ስርዓት ተከበረ

ሀዋሳ ሐምሌ 19/2010 በቁልቢ እና ሃዋሳ ዓመታዊው የቅዱስ ገብርኤል ንግስ በዓል ዛሬ በደማቅ ስነ ስርዓትና በሰላም መከበሩን ፖሊስ አስታወቀ፡፡ የምስራቅ ሐረርጌ ዞን ፖሊስ መምሪያ የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዲቪዥን ክፍል ኃላፊ  ኮማንደር ስዩም ደገፉ ለኢዜአ እንደገለጹት በሺዎች የሚቆጠሩ የእምነቱ ተከታይዎች በታደሙበት የንግስ በዓል በቁልቢ በሰላም ተከብሯል። ለዚህም የሀግ አስከባሪዎች  ከምንጊዜውም በላይ ያካሄዱት የወንጀል መከላከል ስራና ህብረተሰቡም ያደረገው ጥንቃቄ የተሞላበት እንቅስቃሴ  ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክተዋል፡፡ በንግስ በዓሉ ላይ ሞባይልና ገንዘብ  ሰርቀው እጅ ከፍንጅ የተያዙ አራት ተጠርጣሪዎችን በገዳሙ አካባቢ የተቋቋመው ጊዜያዊ ፍርድ ቤት ቀርበው ጥፋተኝነታቸው ተረጋግጦ ከአንድ ዓመት ከስድስት ወር እስከ ሁለት ዓመት በሚደርስ እስራት እንዲቀጡ መደረጉን አስታውቀዋል። እንዲሁም  ጾታው ወንድ ሆኖ ሳለ የሴት አልባሳት በመልበስ የማታለል ስራ ሲያከናውን የተገኘው አንድ ተጠርጣሪ ደግሞ በምክር መለቀቁን አመልክተዋል። የስለት ሙክት ሰርቀዋል የተባሉ ሁለት ተጠርጣሪዎች ማስረጃ አለን በማለታቸው ጉዳያቸው በመደበኛው የሜታ ወረዳ ፍርድ ቤት እንዲታይ መተላለፉም ተጠቅሷል፡፡ ወደ ንግስ በዓሉ ምዕመናኑ መምጣት ከጀመሩበት ካለፈው ሰኞ እስከ ፍጻሜው ድረስ ምንም ዓይነት የትራፊቅ አደጋ አለመድረሱን ጠቁመዋል። በቁልቢ ገብርኤል ገዳም የተካሄደው የንግስ በዓል ስነ ስርዓት ሲጠናቀቅ ምዕመናኑ ኃይማኖታዊ ስርዓቱን ጠብቀው ፈጣሪያቸውን በማመስገን ወደ መጡበት ተመልሰዋል፡፡ በተመሳሳይ በሃዋሳ የተከበረው የቅዱስ ገብርዔል ንግስ በዓል በሰላም መጠናቀቁን የከተማው ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ ምክትል ኮማንደር መሳፍንት ሙሉጌታ ገልጸዋል፡፡ በዓሉን

Sidama expect referendum on statehood within a year after zone backs autonomy demand

Sidama campaigners expect a referendum within a year on becoming a region after the Zone Administration in Hawassa voted for statehood. The constitutional demand follows deadly ethnic violence in southern Ethiopia and elsewhere in the country during the recent national political transition. The July 18 decision was made after all 19 woreda governments in the Zone voted to push the case for a Sidama state in the last three weeks, said UK-based analyst Seyoum Hameso. The  Fichee-Chambalaalla  Sidama new year festival triggered  fatal violence  in mid-June, leaving 10 dead, 89 injured, and 20,000 mostly ethnic Wolayta displaced in Hawassa, according to the UN. The self-rule request was today presented to the Southern Nations, Nationalities and People’s Regional State (SNNPRS) administration, which is also based in Hawassa, the location of Ethiopia’s most expensive and successful industrial park. A similar process occurred in 2006 but a referendum was not held. Around 100 people

ሲዳማ...10ኛው የኢትዮጵያ ክልል?

በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ክልል የሚገኘው የሲዳማ ዞን ምክር ቤት ዞኑ ወደ ክልል እንዲያድግ በትናንትናው ዕለት በሙሉ ድምፅ ወስኗል። የኢትዮጵያ ሕገ-መንግሥት በሚደነግገው መሠረት ውሳኔው ለክልሉ ምክር ቤት ቀርቦ በሕዝበ-ውሳኔ ከጸደቀ ሲዳማ 10ኛው የኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት ይሆናል።           አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:28 የሲዳማ ዞን ምክር ቤት ወደ ሕዝበ-ውሳኔ የሚመራ ጥያቄ አቅርቧል የሲዳማ ዞን ምክር ቤት ሐምሌ 11 ቀን 2010 ዓ.ም. ተሰብስቦ ሲዳማ 10ኛው የኢትዮጵያ ክልል ሆኖ እንዲዋቀር የሚጠይቅ የውሳኔ ሐሳብ በሙሉ ድምፅ አጽድቋል። የሲዳማ ዞን የባሕል፣ ቱሪዝም እና የመንግሥት ኮምዩንኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ጃጎ አገኘሁ ለዶይቼ ቬለ እንደተናገሩት ውሳኔው 161 ገደማ ከሚሆኑት የምክር ቤቱ አባላት አንድም ተቃውሞ አሊያም ድምፀ ተዓቅቦ ሳይገጥመው በሙሉ ድምፅ ጸድቋል። "በወጣቱ አዋቂው ውስጥ ያለ ጥያቄ በመሆኑ ሰፊ ውይይት ነው የተደረገበት። ከዚህ አንፃር ሕገ-መንግሥቱ በሚፈቅደው መሠረት በሲዳማ ሕዝብ ውስጥ በምሁራኑ፣ በወጣቶቹ እስከ አርሶ አደር ድረስ ማለት ይቻላል ሰፊ ውይይት ከተደረገ በኋላ የሲዳማ ሕዝብ በክልል መደራጀት አለብኝ በሚል ያቀረበው ጥያቄ ሕጋዊ እና ሕገ-መንግሥታዊ መሆኑን ታሳቢ በማድረግ የሲዳማ ዞን ምክር ቤት ትናትና ባካሔደው አራተኛ ዙር ሁለተኛ አስቸኳይ ጉባኤ ላይ ይኸን ውሳኔ በሙሉ ድምፅ አፅድቆታል" በሕገ-መንግሥት ባለሙያው አቶ ውብሸት ሙላት ማብራሪያ መሠረት የሲዳማ ዞን ምክር ቤት የውሳኔ ሐሳቡን ሲያጸድቅ ክልል ለመሆን ከሚያስፈልገው ሒደት ግማሽ ያክሉን አጠናቋል ማለት

ረፋድ አደባባይ የወጣው የሃዋሳና አካባቢዋ ህዝብ ኢትዮጵያዊ ጨዋነት በተላበሰ አክብሮት እንግዳውን ተቀብሏል

ከደቂቃዎች በፊት በሃዋሳ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ የገቡት የኤርትራው ፕሬዝዳንት ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል፡፡በአቀባባል ስነስርዓቱ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች፣ የሃገር ሽማግሌዎች የሃይማኖት አባቶችና የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች ተገኝተዋል፡፡በማርሽ ባንድና በኪነት ቡድን የታጀበ አቀባበል የተደረገላቸው ፕሬዝዳንቱ በፈረስ ጉግስና በእልልታ በታጀበ አቀባበል ሃዋሳ ኢንደስትሪ ፓርክ ደርሰዋል፡፡ረፋድ አደባባይ የወጣው የሃዋሳና አካባቢዋ ህዝብ ኢትዮጵያዊ ጨዋነት በተላበሰ አክብሮት እንግዳውን ተቀብሏል፡፡በፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ የተመራው ልዑክ ሀዋሳ ኢንዱስትሪያል ፓርክን ጎብኝቷል፡፡ Source

Eritrea’s President Visiting Hawassa

Eritrea’s President Isayas Afewerki has arrived in the town of Hawassa in Southern Ethiopia to visit the country’s flagship industrial park. The President has received a warm welcome from officials of the regional government, religious leaders and community elders and residents of the town upon his arrival. Prime Minister Abiy Ahmed and other high level federal government officials have also accompanied Isayas, arrived this morning in Addis Ababa for a three-day state visit, to Hawassa. In Hawassa, President Isayas will visit the Hawassa Industrial Park, which is the largest specialized apparel and textile park on the continent. Ethiopia inaugurated its largest industrial park in July 2016 to meet its development target and create enough job opportunities for the young population. By building the park, which expected to employ 60,000 people at full capacity, Ethiopia has targeted to generate one billion USD annually once the park starts operations at its full potential. E

የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ የሐዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክን ጎበኙ

  የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ የሐዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክን ጎበኙ፡፡ ፕሬዚደንቱ ወደ ሐዋሳ ከተማ ሲገቡ የአካባቢው ህዝብ ደማቅ አቀባበል አድርጎላቸዋል፡፡ በፕሬዚዳንት ኢሳያስ የሚመራው የኤርትራው ልኡክ የሐዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ ውስጥ የሚገኙ የተለያዩ የማምረቻ ፋብሪካዎችን የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ጋር በጋራ ጎብኝተዋል። በፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ የተመራው የኤርትራ ልኡክ በኢትዮጵያ የሶስት ቀናት ይፋዊ የስራ ጉብኝት ለማድረግ ዛሬ ነው ረፋድ ላይ አዲስ አበባ የገባው፡፡ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱም፥ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድን ጨምሮ የክልል ርዕሳነ መስተዳድራን፣ ሚኒስትሮች፣ የኃይማኖት አባቶች፣ ታዋቂ ግለሰቦች እና የጥበብ ሰዎች ተገኝተው ደማቅ አቀባበል አርጎላቸዋል። ፕሬዚዳንቱ በብሄራዊ ቤተመንግስት በተደረገላቸው የምሳ ግብዣ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር፥ የኢትዮጵያና ኤርትራ ህዝብ ለሰላም ያለው ፍላጎት እና ምኞች መግለፁን አንስተዋል። በዚህም "የኢትዮጵያና ኤርትራ ህዝቦች ከእንግዲህ ሁለት ህዝቦች ናቸው ብለው የሚገልፁ አካላት ካሉ ሀቁን የማያውቁ ናቸው" ብለዋል። የፊታችን እሁድ ዕለት ደግሞ በሚሊኒየም አዳራሽ 25 ሺህ ህዝብ የሚገኝበት "የኢትዮጵያ እና የኤርትራ ሰላም ማብሰሪያ" መድረክ ይካሄዳል። መድረኩ ላይም ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ እና ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ተገኝተው ንግግር ያደርጋሉ ተብሏል። በተጨማሪም የኪነ ጥበብ ባለሙያዎችም የሁለቱን ሀገራት ሰላም የሚያንፀባርቁ የተለያዩ ስራዎችን በመድረኩ ላይ እንደሚያቀርቡም ይጠበቃል። Source

PVH, Velocity Apparelz And Intrade UK Invest In Hawassa & Mekelle Industrial Parks

PVH, Velocity Apparelz and Intrade UK to invest in Hawassa. The companies are all manufacturing textile products in Ethiopia. Industrial parks up and down the country are employing thousands of people thanks to FDI which currently stands at a minimum of $200,000 for any business interested. All export of products made in Ethiopia to the US and Europe are duty free. Entry level salaries for workers range from $35 to $40 (32 to 37 Euros) per month – lower than Bangladesh’s minimum wage of $68 per month and far below the average wage of $500 in the Chinese textile sector. American based Philip Van Heusen (PVH) dominates the global apparel market and is exporting t-shirts made in the Hawassa Industrial Park, 273 km south of Addis Ababa. Also operating units in Kenya and Egypt, the company has established a joint venture with Indian manufacturer, Arvind, in Ethiopia and secured a 15,000 sqm shed in the park creating over 800 jobs. PVH owns brands such as Tommy Hilfiger, Calvin Klein a

Eritrean president to tour Chinese-built industrial park in historic Ethiopian visit

(Xinhua) -- Eritrean President Isaias Afwerki will pay a visit to Ethiopia's flagship Hawassa Industrial Park in the weekend, an Ethiopian official said on Friday. Afwerki is expected to start a historic three-day state visit to Ethiopia on Saturday, the first time the veteran Eritrean leader will visit Ethiopia in 20 years. The two countries started tentative steps towards reconciliation in June, two decades after a bloody border war in 1998-2000 killed an estimated 70,000 people from both sides and cut the countries' diplomatic and economic relations. Speaking to media, Ahmed Shide, Minister of Ethiopia Government Communications Affairs Office (GCAO), said Afwerki is scheduled to visit the Chinese-built industrial park which has been lauded for its positive contribution to Ethiopia's industrialization ambitions. Shide also said the Eritrean president is scheduled on Sunday to re-open the Eritrean Embassy in Ethiopia's capital Addis Ababa that was closed in t

የዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል፤ በማዕከሉ ስም በተከተፈተው ዋልታ ቲቪ በተባልው ፌክ የፌስቡክ አካውንት በሲዳማ ህዝብ እና በብሄሩ ተወላጆች ላይ ጸረ ህዝባዊ ዘመቻ የከፈቱትን ግለሰቦች ተከታትሎ ሊያስቆማቸው ይገባል።

የዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል፤ በማዕከሉ ስም በተከተፈተው ዋልታ ቲቪ በተባልው ፌክ የፌስቡክ አካውንት በሲዳማ ህዝብ እና በብሄሩ ተወላጆች ላይ ጸረ ህዝባዊ ዘመቻ የከፈቱትን ግለሰቦች ተከታትሎ ሊያስቆማቸው ይገባል። Walta Tv – ዋልታቲቪ በሚል ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች በተከፈተው የፌስ ቡክ አካውንት ላይ ላለፉት ሳምንታት ጸረሲዳማ ህዝብ እና በአንዳንድ የብሄሩ ተወላጆች ላይ በከፈቱት ስም የማጥፋት ዘመቻ፤ የሲዳማን ብሄር ለዘመናት በፍቅር እና በመልካም ጉርብትና አብረውት ከኖሩት ሌሎች ብሄረሰቦች ጋር ለማጋጨት ሆነ ብለው በመስራት ላይ ናቸው። ለዚህም ማሳያ እንድሆን በዚህ ሳምንት ማለትም ጁላይ 6 ላይ “ ትላንት ከሰአት በኃላ በአሜሪካ በተለያዩ ግዛቶች የሚኖሩ የከምባታ እና የሀዲያ ብሄር ተወላጆች በአዋሳ ከተማ በአንድ ብሄር የበላይነት በዜጎች ላይ እየተፈጸመ ያለውን ጥቃት አወገዙ። http.ethiogudy#.org.icomenglish” በሚል ከታች በፎቶ ላይ መመልከት እንደሚቻለው፤ የከንባታ እና የሀዲያ ብሄሮች የባህል አልባሳትን የለበሱትን ጨምሮ የሌሎች የክልሉ ብሄረሰቦች ባህላዊ አልባሳትን የለበሱ ግለሰቦች ፎቶን በመጠቀም የግል አጀንዳቸውን ለማሳካት እና ህዝብን ለማሳሳት በመጣር ላይ ይገኛሉ። ከዚህም በተጨማሪ ይሄው የፌስቡክ ገጽ አንዳንድ የሲዳማ ተወላጆችን ባላፈው በሃዋሳ ከተማ ተከስተው በነበረው ግጭት ላይ ተሳትፏል በማለት እና ያለ ምንም በቂ ማስረጃ ስም የማጥፋት ዘመቻ ታይይዘዋል። ሰለዚህም የዋልታ ኢንፎርሜሽን ሴንተር በማእከሉ ስም በተከተፈተው ዋልታ ቲቪ በተባልው ፌክ የፌስቡክ አካውንት ላይ በሲዳማ ህዝብ እና በብሄሩ ተወላጆች ላይ ጸረ ህዝባዊ ዘመቻ የከፈቱትን ግለሰቦች ተከታትሎ ሊያስቆማቸው

በሐዋሳ ከተማና በሲዳማ ብሔር ላይ የሚደረጉ ትንኮሳዎች ይቁሙ!

በሀዋሣ ከተማ ውስጥና በአንዳንድ የሲዳማ ዞን የወረዳ የተፈጠረውን ግጭት ተከትሎ መጠኑ ይለያይ እንጅ በሁለቱም ብሔሮች ተወላጆች ላይ የሕይወት መጥፋትና በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን ከዚህ በፊት በተለያዩ የሚዲያ አውታሮች የሲዳማ ዞንና ከተማ አስተዳደሩ አመራር አካላት ቀርቦ የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን መግለጻቸው ይታወቃል፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ የተፈጠረውን ጉዳት አስመልክቶ የክልሉ መንግስትና ደኢህዴን አመራርም ይቅርታ መጠየቃቸውንም ሁሉም የሚገነዘበው ሀቅ ነው፡፡ የግጭቱ መንስኤ እየተጣራ መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ ድርጊቱ እኩይ አላማ ባላቸው ግለሰቦች የተፈፀመ እንጅ ሰፊውን የሲዳማን እና የወላይታን ብሔር እንደማይወክል መታወቅ አለበት፡፡ በደረሰው የፀጥታ መደፍረስ የተፈናቀሉ አካላትን ከተማ አስተዳደሩ ከክልል መንግስት፣ ከሃይማኖት መሪዎችና፣ ከከተማው ህብረተሰብ እና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ጊዜያዊ መጠለያ በማመቻቸት የምግብ፣የአልባሳትና የሕክምና እርዳታ ቡድን በማቅረብ እና በማሰማራት እንዲሁም ንብረት ላይ ጉዳት የደረሰባቸውን መልሶ ለማቋቋም የጉዳት መጠኑን የሚያሳይ መረጃ እየተሰበሰበ ለውሳኔ ሰጪነት ለመጠቀም በተሠራው ሥራ በግጭቱ የተፈናቀሉ ዜጎች ወደነበሩበት መንደር ተመልሰው ጤናማ ኑሮ መምራት ከመቻላቸውም በላይ ከአካባቢው የሲዳማ ሕብረተሰብ ጋር የተለመደውን ማህበራዊ ትስስር ፈጥሯል፡፡  ይሁንና ቀሪዎቹን በጊዜያዊ መጠለያ ያሉትን ለመመለስ መጠነ ሰፊ ሥራዎች እየተሰሩ ቢሆንም አንዳንድ ሃላፊነት የማይሰማቸው ግለሰቦች አሁንም በሲዳማ ብሔር እና በሀዋሳ ከተማ ላይ ያላቸውን የተዛባና አፍራሽ ዘመቻቸውን ቀጥለውበታል፡፡  ከሚያራምዱት አፍራሽ ዘመቻዎች መካከል፡-  1. ከተማችን ሀዋሳ ከ8ዐ በላይ ብሔሮችና ብሔረሰቦች የሚገኙባት እና ሁሉም

Sidama Zone head, Hawassa mayor resign

The Administrator of Sidama Zone Aklilu Adula and the Mayor of Hawassa Tewodros Gebiba have resigned from their posts in connection to the recent conflict in the town of Hawassa and its surroundings,  The Reporter  has learnt. The conflict had resulted in the death of ten people and the injury of more than 80, while close to 3,500 people have been reported to be displaced from their homes. It is to be recalled that five senior officials from the Wolayta Zone have resigned from their position in relation to the conflict which took place in Wolayta Sodo town which began as a rally to denounce the attack on ethnic Wolaytas in Hawassa and its surrounding towns. The resignation of the officials in Wolayta came immediately after Prime Minister Abiy Ahmed (PhD) called up on Wolayta, Sidama, Kebena and Gurage zonal and woreda administrators to resign and take responsibility for the conflicts that happened in the area. The PM toured the conflict ridden areas days after the clash. Repo

የሲዳማ ዞን አስተዳዳሪና የሐዋሳ ከንቲባ ሥልጣናቸውን ለቀቁ

በቅርቡ በደቡብ ክልል በሐዋሳ ከተማ በነበረው ግጭት ምክንያት የሲዳማ ዞን አስተዳዳሪ አቶ አክሊሉ አዱላና የሐዋሳ ከተማ ከንቲባ  አቶ  ቴዎድሮስ ገቢባ  ከኃላፊነታቸው ለቀቁ፡፡ ከሦስት ሳምንታት በፊት በተከሰተው ግጭት አሥር ሰዎች ጉዳት ደርሶባቸው 80 ሰዎች የተጎዱ ሲሆን፣ 3500 ደግሞ ከመኖሪያቸው ተፈናቅለዋል፡፡ ካሁን ቀደም በሐዋሳው ጥቃት በወላይታ ተወላጆች ላይ ጥቃት እየተፈጸመ ነው በማለት ለተቃውሞ ሰልፍ በወጡ ሰዎች በተቀሰቀሰ ሁከት ምክንያት፣ አምስት የወላይታ ዞን ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ሥልጣናቸውን መልቀቃቸው ይታወሳል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) በደቡብ ክልል ግጭት የተከሰተባቸውን ሲዳማ፣ ወላይታና ወልቂጤ ከተሞች ከጎበኙ በኋላ የሲዳማ፣ የወላይታ፣ የጉራጌና የቀቤና የዞንና የወረዳ አስተዳዳሪዎች በገዛ ፈቃዳቸው ሥልጣናቸውን እንዲለቁ ጥሪ አቅርበው ነበር፡፡ Reporter

#EBC የደ.ኢ.ህ.ዴን ሊቀመንበር ወ/ሮ ሙፈሪያት ከኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ጉጂ ዞኖች የተፈናቀሉ የጌዲኦ ዞን ተወላ...

ወንድም የጌደኦ ህዝብ ለዘመናት ያጎሳቀሏሉትን የመልካም አስተዳድር ችግሮችን ከስር መሰረት ነቅሎ በመጣል፤ ብሎም ላለፉት በርካታ መቶ አመታት በሰላም፤ በጋራ እና በፍቅር እንዲሁም በመልካም ጉርብትና አብሮው ከኖረው ከሰላም ወዳዱ የኦሮሞ ህዝብ ጋር በሰላም እና በፍቅር ዳግመኛ እንዲኖር ድጋፍ ልንሰጠው እና በችግሩ ልንደርስለት ይገባል። 

የደቡብ ሚድያ አውታሮች ጸረ ሲዳማ እና ጸረ ፊቼ በአል ፕሮፖጋንዳ ሲያራግቡ፤ ከ600 ሺ በላይ የሚሆኑ የኦሮሞ እና ጌዴኦ ተፈናቃይ ተወላጆች ሰቆቃ ጆሮ ዳባ ብለዋል

በም እ ራብና ምስራቅ ጉጂ ዞን አካባቢ በተከሰተው የፀጥታ ችግር የተፈናቀሉ ዜጎች ያሉበት ሁኔታ አስቸ ኳ ይ እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው እና እኛም ሲዳማዎቹ ተደምረን ችግሩ የሚቀርፍ በትን መንገድ በመንግስት ባለመመቻቸቱ፤ ዛሬም የተፈናቃዮች ቁጥር በ ከ ፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ ነው። በችግሩ ምክንያት የ ተፈና ቀሉት ኢትዮጵያውያን፤ ለአብኔት ያህል በጌዴኦ ዞን በሚገኙ ወረዳዎች በትምህርት ቤቶች፣ በቀበሌ አዳራሾች እና በተለያዩ ስፍራዎች ተጠልለው ይገኛሉ። ቁጥራችው ከ 600 ሺህ በላይ ሆኗል ። ይሄ ቁጥር በሃገሪቱ ከተከሰቱ መፈናቀሎች ግንባር ቀደም ያደርግልዋል። ነገር ግን ልፍስፍሱ የደቡብ መንግስት እና እየሞተ ያለው የክልሉ ግዥው ፓርቲ ደኢህዴን፤ አዲስ አበባ ከሚገኘው ዋናው ጽ / ፍት ቢሮቸው ውስጥ ሆነው የራሳቸውን ኑሮ ከማጣጣም ሌላ፤ እንደ ችግርተኞቹ ብዛቱና እንደችግሩ መጠን ትኩረት አል ሰጡት ም። ቄያቸውን ለቀው በየትምህርት ቤቶች ከተጠለሉት ተፈናቃዮች መካከል ህፃናት እየሞቱ ነው፣ ተላላፊ በሽታዎች እየተስተዋሉ ነው፣ የተፈናቃዩ ቁጥር እየጨመረ ነው። ነገር ግን የሚቀርበው እርዳታ በቂ አይደለም። በርግጥ 600 ሺህ ህዝብ መርዳት ለደቡብ መንግስት ገዥ ፓርቲ አመራሮች ቀላል አይደለም። ከሁሉ በላይ ግን ችግሩን የተመለከቱት የሚዲያ ተቁዋማትም እነ አቶ ደሴ ዳልኬን ተከትለው መጥተው አንዴ አውርቶ መጥፋት ከሞያው የሚጠበቅ አይደለም ። ይህ ደግሞ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ውሎ ውጭ በአገሪቱ ምን እየተደረገ እንዳለ መዘጋብ ላልቻለው EBC እ ና በምንም የሙያ መለኪያ፣ ማለትም የጋዜጠኝነት ባህር ያልተላበሰው የደቡብ ክልል TV ። ችግሩን መጥቶ የተለመከ ቱት የክልሉ መንግስትም ሆነ መረጃው የደረሳቸው የመግስት አካላት ችግሩ የራሴ