Skip to main content

ባለሃብቶች ሙስናን ከመስጠት መታቀብ አለባቸው-በቡና ንግድ የተሰማሩ ባለሃብቶች

ባለሃብቶች ሙስናን ከመስራት በመታቀብ መንግስት ላቀደው የፀረ-ሙስና ትግል የበኩላቸውን ድርሻ መወጣት እንዳለባቸው በሐዋሳ ከተማ ያሉ በቡና ንግድ ዘርፍ የተሰማሩ ባለሃብቶች ተናገሩ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከደቡብ፣ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል ከተውጣጡ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር በሐዋሳ ከተማ መወያየታቸው ይታወሳል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በውይይቱ ከታሳታፊዎች ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽ የሰጡ ሲሆን፤ በተለይ ሙስና በአገሪቷ ሁለንተናዊ ልማት ላይ ትልቅ አንቅፋት መፍጠሩን አብራርተዋል።
ከችግሩ አስከፊነት አኳያ መንግስት የተለያዩ ስትራቴጂዎችን በመቀየስ ሙስናን እንደሚዋጋም ገልጸዋል።
በኢትዮጵያ ከፍተኛውን የመንግስት እርከን የያዘ ሰው ከሁለት የምርጫ ጊዜያት በላይ በስልጣን እንዳይቆይ የሚደነግግ አንቀጽ በአገሪቷ ህገ መንግስት እንዳለም ለአብነት አንስተዋል።
በውይይቱ ባለሃብቶች ሙስናን በመዋጋት ረገድ ከፍተኛ ድርሻ አንዲወጡም ጥሪ ማቅረባቸው ይታወቃል።
ኢዜአ የጠቅላይ ሚኒስትሩን ጥሪ አስመልክቶ በሐዋሳ ከተማ በቡና ንግድ ዘርፍ የተሰማሩ ባለሃብቶችን አነጋግሯል።
ባለሃብቶቹ "ሙስና ሰጭዎች  እኛ ባለሃብቶች በመሆናችን ከዚህ ድርጊት በፍጥነት በመውጣት በፀረ-ሙስና ትግሉ የበኩላችንን መወጣት አለብን ነው"ያሉት።
አቶ ዱካሌ ዋቀዮ ኢትዮጵያ በሙስና ችግር ወደ ኋላ አንዳትሄድ "ባለሃብቶች ሙስና ከመስጠት እንዲታቀቡ" ጥሪ አቅርበዋል።
"መስጠት ካለ ተቀባይ መኖሩ የማይቀር ነው" ያሉት አቶ ዱካሌ፤ በሙስና ትግል ውስጥ የባለሃብቶች ሚና ከፍተኛ መሆኑን ጠቁመዋል።
አቶ ቶምቦላ ቱርባ  በበኩላቸው በአገሪቷ ተፈጥሮ ለነበረው ችግር "ሙስና ዋነኛ ምክንያት መሆኑን" ጠቅሰው፤ ድርጊቱን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ብቻውን ስለማያስቀረው ሁሉም ሊተባበር እንደሚገባ አውስተዋል።
"ባለስልጣኑን የምናባልግ እኛ ነን" ያሉት ደግሞ በክልሉ የቡና አቅራቢዎች ዘርፍ ማህበር ፕሬዝዳንት አቶ ዘርይሁን ቃሚሶ ናቸው።
አቶ ዘርይሁን ባለሃብቶች ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያስተላለፉትን መልእክት ተግባራዊ በማድረግ ከእርሳቸው ጋር የጋራ የሆነ የሙስና መከላከል ውስጥ እንደሚገቡም ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ  እስከ ታችኛው የቀበሌ መዋቅር ድረስ ሙስናን የሚፀየፍ አመራር መፍጠር እንደሚገባም ጥሪ አቅርበዋል።

Comments

Popular posts from this blog

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

የለበሰው ያደፈ ቁምጣና ሹራብ ከቅዝቃዜው አላዳነውም፡፡ ካፊያው ልብሱን አርሶታል፡፡ ሽው እያለ ከሐይቁ የሚነሳው ነፋስ የሚፈጥረው ቅዝቃዜ ያንቀጠቅጠዋል፡፡ የተጫማው ያረጀ ሲሊፐር እግሩን ከምንም አላዳነውም፡፡ በባዶ እግሩ የሚራመድ ያህል ጨቅይቷል፡፡ ተደባዳቢ ይመስል ፊቱ የተሞነጫጨረ ነው፡፡ ገና 12 ዓመቱ ቢሆንም፣ ቁመናው እንደ ትልቅ ሰው ግዙፍ ነው፡፡ የሚለብሰውን እንደ ልቡ ባያገኝም፣ የሚያስፈልገውን ነገር ለማሟላት ቤሳቢስቲን የሌላቸው ወላጆቹን አያስቸግርም፡፡ ከቤተሰቦቹ ጋር ከሚኖሩበት ታቦር ተራራ ጀርባ ወዳለው ሐዋሳ ሐይቅ ከወረደ እንኳንስ የራሱን የቤተሰቦቹንም የዕለት ጉርስ የሚሸፍንበት ገንዘብ አያጣም፡፡ የአስጎብኚነት ዕውቀት፣ ከሐይቁም ውስጥ ዓሳ የሚያጠምድበት መረብም ሆነ ፈቃድ የለውም፡፡ ሙሉቀን (ስሙ ተቀይሯል) እና ጓደኞቹ ሐይቁን ለመጎብኘት የሚሄዱ ጎብኚዎች በካሜራቸው ጥሩ ፎቶ እንዲያስቀሩ ድባቡን የማሳመር ሥራ ይሠራሉ፡፡ ካሜራውን ይዞ ቁጭ ብድግ እያለ ጥሩ ፎቶ ለማንሳት ጥረት የሚያደርግ ሲያዩ፣ ቆርጠው የያዙትን የዓሳ ሥጋ ይዘው ጠጋ ጠጋ ይላሉ፡፡ ቁርጥራጩን የዓሳ ሥጋ ምግብ ለሚቀሙት አባኮዳዎች ሻሞ ይላሉ፡፡ የተወረወረላቸውን ቀድመው ለመቅለብ አባኮዳዎቹ ክንፋቸውን እየመቱ ወደ ላይ ብድግ ይላሉ፡፡ የናሽናል ጆግሪፊ የፎቶግራፍ ባለሙያዎች ያነሱት ዓይነት ፎቶዎች ሳያስቡት ያነሳሉ፡፡ በሁኔታው ተደስተው ደጋግመው ድንቅ ፎቶዎችን ለመውሰድ ሲዘጋጁ እነ ሙሉቀንም አጀንዳቸውን ይፋ ማድረግ ይጀምራሉ፡፡ አቶ ዳዊት አብርሃም ‹‹አንዱን ዓሳ በአሥር ብር ገዝቼ ነው እንዲህ የማዘጋጀው፤›› በማለት በቅድሚያ  መረጃ ይሰጣሉ፡፡ ለቀጣዩ ዜና በዚህ መልኩ እንዲዘጋጁ ካደረጉ በኋላ፣ ሌሎች ሰዎች መቶም ሁለት መቶም ብር እንደሚሰጧቸው ቀለል

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የመንግሥት ስልጠና የምርጫ ቅስቀሳ አካል ነው ብሏል  የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ለምን ወጣ መባሉ ተገቢ አይደለም - ምርጫ ቦርድ ምርጫ ቦርድ ከኢህአዴግ ተፅዕኖ ሙሉ ለሙሉ ነፃ መሆኑ ሳይረጋገጥና የምርጫ አፈፃፀም ችግሮች ሳይወገዱ የምርጫ የጊዜ ሰሌዳ ለማወጅ መዘጋጀቱ ተገቢ አይደለም ሲል ፕ/ር በየነ ጴጥሮስ የሚመሩት ኢማዴ-ደህአፓ ተቃወመ፡፡ መንግስት፤ የዩኒቨርሲቲ መምህራንና ተማሪዎችን ጨምሮ ለተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች እየሰጠ ያለው ስልጠና የምርጫ ቅስቀሳ አካል ነው ሲልም ፓርቲው ኮንኗል፡፡  የኢትዮጵያ ማህበረ ዴሞክራሲ ደቡብ ህዝቦች አንድነት ፓርቲ ሰሞኑን ለብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ባስገባው ግልፅ ደብዳቤ፤ ያለፉት አገር አቀፍና የአካባቢ ምርጫዎች ከመካሄዳቸው በፊት በምርጫ ችግሮችና መፍትሄዎቻቸው ዙሪያ ኢህአዴግ ከተቃዋሚዎች ጋር የሚወያይበት መድረክ እንዲዘጋጅ በተደጋጋሚ ብንጠይቅም እስካሁን ከቦርዱ የተሰጠ ተግባራዊ ምላሽ የለም ብሏል፡፡  ሃገሪቱ “በአንድ አውራ ፓርቲ” ብቸኛ ቁጥጥር ስር መውደቋ አደገኛና አሳሳቢ ነው ያለው ፓርቲው፤ የመድብለ ፓርቲ ስርአት የመገንባት ተስፋችን ጨርሶ እንዳይከስም ቦርዱ ሃላፊነቱን መወጣት እንዳለበት አሳስቧል፡፡ ነፃና ፍትሃዊ ምርጫ የሚካሄድበትን ሁኔታ ለመፍጠር ገዥው ፓርቲና ሃቀኛ ተቃዋሚ ፓርቲዎች የሚወያዩበት መድረክ እንዲያመቻች በህግ ስልጣን የተሰጠው ምርጫ ቦርድ የገባውን ቃል በማጠፍ መድረኩን ሳያመቻች የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማዘጋጀቱ ፋይዳ የለውም ብሏል - ፓርቲው፡፡  ገዥው ፓርቲ ኢህአዴግ በተሻሻለው የምርጫ ህግ፣ ለቦርዱ የተሰጠውን የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ መድረክ የማስተባበር ስልጣን ለመቀማት ታማኝ ፓርቲዎችን በተቃዋሚ ስም አሰባስቦ “የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ መድረክ” በመፍጠር የምርጫ ውድድር አሯሯጭ አሰልፏል ሲ

የጀርመን መንግስት ዜጎቹ ወደ ሀዋሳ እና አከባቢዋ በሚጓዙበት ጊዜ ጥንቃቄ እንዲያድርጉ መከረ

የጀርመን መንግስት ዜጎቹ ወደ ሀዋሳ እና አከባቢዋ በሚጓዙበት ጊዜ ጥንቃቄ እንዲያድርጉ አስጠነቀቀ ዛሬ በአገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ድረገጽ ላይ ባወጣው ማስጠንቀቂያ እንዳመለከተው፤ የጀርመን ዜጎች በኢትዮጵያ ውስጥ በሚቀሳቀሱበት ጊዜ ከጸጥታ አንጻር ማድረግ ባለባቸው እና መሄድ በሌለባቸው የኢትዮጵያ አከባቢዎች ላይ ሰፋ ያለ መረጃ ስጥቷል። በጽሁፉ ላይ እንደተጠቀሰው በኢትዮጵያ በበርካታ አከባቢዎች ግጭቶች መኖራቸው የተጠቀስ ሲሆን፤ በሲዳማ ክልል የነበረውን ግጭት አስታውሷል። አክሎም በወላይታ ዞን የጸጥታ ስጋት መኖሩን ጠቅሶ ወደ ሲዳማዋ ዋና ከተማ ሀዋሳ የምንቀሳቀሱ ዜጎቿ የተለየ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ መክሯል። ዝርዝሩን ከታች ከሊንኩ ላይ ያንቡ Äthiopien: Reise- und Sicherheitshinweise