Skip to main content

Posts

Showing posts from April, 2018

በጠቅላይ ሚኒስትሩ የሃዋሳው ውይይት ላይ ዶ/ር ሚሊዮን ቱማቶ ቱቻ፤ የሲዳማ ኣርነት ንቅናቄ ኣመራር ምንድነው የተናገሩት?

Information on the Sidama Liberation Movement (SLM), including history, goals, and methods; whether the group uses violence and has participated in armed conflict; treatment of members by the authorities (2012-October 2016) Overview In correspondence with the Research Directorate, a lecturer in international development at the University of East London who has researched ethnic groups in Ethiopia, including the Sidama [1], characterized the Sidama Liberation Movement (SLM) as a "political organisation" that aims to "ensure Sidama peoples' national self-determination within the context of Ethiopia" (Lecturer 23 Oct. 2016). In correspondence with the Research Directorate, a research professor at Vrije Universiteit Amsterdam, who has researched history and culture in the horn of Africa, particularly Ethiopia, similarly stated that the SLM is "ethnically based and has a primarily Sidama-limited agenda" (Research Professor 21 Oct. 2016). The same s

ባለሃብቶች ሙስናን ከመስጠት መታቀብ አለባቸው-በቡና ንግድ የተሰማሩ ባለሃብቶች

ባለሃብቶች ሙስናን ከመስራት በመታቀብ መንግስት ላቀደው የፀረ-ሙስና ትግል የበኩላቸውን ድርሻ መወጣት እንዳለባቸው በሐዋሳ ከተማ ያሉ በቡና ንግድ ዘርፍ የተሰማሩ ባለሃብቶች ተናገሩ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከደቡብ፣ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል ከተውጣጡ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር በሐዋሳ ከተማ መወያየታቸው ይታወሳል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በውይይቱ ከታሳታፊዎች ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽ የሰጡ ሲሆን፤ በተለይ ሙስና በአገሪቷ ሁለንተናዊ ልማት ላይ ትልቅ አንቅፋት መፍጠሩን አብራርተዋል። ከችግሩ አስከፊነት አኳያ መንግስት የተለያዩ ስትራቴጂዎችን በመቀየስ ሙስናን እንደሚዋጋም ገልጸዋል። በኢትዮጵያ ከፍተኛውን የመንግስት እርከን የያዘ ሰው ከሁለት የምርጫ ጊዜያት በላይ በስልጣን እንዳይቆይ የሚደነግግ አንቀጽ በአገሪቷ ህገ መንግስት እንዳለም ለአብነት አንስተዋል። በውይይቱ ባለሃብቶች ሙስናን በመዋጋት ረገድ ከፍተኛ ድርሻ አንዲወጡም ጥሪ ማቅረባቸው ይታወቃል። ኢዜአ የጠቅላይ ሚኒስትሩን ጥሪ አስመልክቶ በሐዋሳ ከተማ በቡና ንግድ ዘርፍ የተሰማሩ ባለሃብቶችን አነጋግሯል። ባለሃብቶቹ "ሙስና ሰጭዎች  እኛ ባለሃብቶች በመሆናችን ከዚህ ድርጊት በፍጥነት በመውጣት በፀረ-ሙስና ትግሉ የበኩላችንን መወጣት አለብን ነው"ያሉት። አቶ ዱካሌ ዋቀዮ ኢትዮጵያ በሙስና ችግር ወደ ኋላ አንዳትሄድ "ባለሃብቶች ሙስና ከመስጠት እንዲታቀቡ" ጥሪ አቅርበዋል። "መስጠት ካለ ተቀባይ መኖሩ የማይቀር ነው" ያሉት አቶ ዱካሌ፤ በሙስና ትግል ውስጥ የባለሃብቶች ሚና ከፍተኛ መሆኑን ጠቁመዋል። አቶ ቶምቦላ ቱርባ  በበኩላቸው በአገሪቷ ተፈጥሮ ለነበረው ችግር "ሙስና ዋነኛ ምክንያት መ

ሲዳማ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ኣብይ ኣህመድ የጠበቀውን ኣግኝቶ ይሁን?

የጠቅላይ ሚኒስትር ዶ / ር ኣብይ ኣህመድ የትናንትናው የሃዋሳ ኣቀባበል በጣም የሚገርም ነው። ሲዳማ በታሪኩ ለኣንድ የኢትዮጵያ መሪ ይህን መሰል ኣቀባበል ኣድርጎ የሚያውቅ ኣይመስለኝም። በወቅቱ የነበረውን ቄጣላ ሳይ ልቤ ተነክቷል። የሲዳማ ህዝብ ምን ያህል ለኢትዮጵያ መሪዎች ክብር እንዳለው ተመልክቻለሁ። ምናልባትም የወቅቱ መሪ፤ ሲዳማን በብዙ መልኩ ከሚመስለው እና ተመሳሳይ የመልካም ኣስተዳደር እና ሰብኣዊ መብት ከተነፈገው ወንድም የኦሮሞ ህዝብ ኣብራክ የተነኙ በመሆናቸው የተነሳ መሆኑን በእርግጥ ላረጋግጥ ኣልቻልኩም። በሌላ ግኑ ግን፤ ሲዳማዎች ዶ / ር ኣብይን እንደየገዛ ልጃቸው፤ በለምለም ሳር ላይ ቁጥጥ ብለው ስመርቁት መስማቴ፦ ያ ሁሉ ክብር እና ምርቃት ምን ስለ ኣደረገ ነው? እንድል ኣስገድዶኛል ። የሆነ ሆኖ ሲዳማ የሚወደውን ሰው ነው ዳኤ ቡሹ የሚለው። '' ቡሻ '' ኣፈር ማለት ነው፤ እንዲሁ በቀላሉ እንዲመጣ የሚፈለግ ነገር ኣይደለም። እንዳው በዘፈቀደ ስንተረጉመው፦እኔ ለኣንተ ሞቼ ኣፈር ልልበስ እንደማለት ነው። ዳኤ ቡሹ በዚህ እንድምታው ሞት ይምጣብኝ ማለት ነው። ይህም ማለት ለምትወደውን ሰው ካልሆነ፤ ኣትመኘውም። እንግዲህ ሲዳማ ለጠ / ር ዶ / ር ኣብይ በዚህ መልኩ ነው ፍቅሩን የገለጻው ልባል ይችላል። በርግጥ በቄላው ላይ የነበረው ህዝብ በፍላጎቱ ነው ወይስ በደኢህዴን ካድሬ ተገዶ ነው የወጣው፤ ለሚለው ጥያቄ ለጊዜው ምላሻ የለኝም። ነገርግን ኣቶ ሽፈራው ሽጉጤ እና ኣቶ ዴሰ ዳልኬ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶ / ር ኣብይ ጎን ቆመው፤ በተለይ የሲዳማ ሽማግሌዎች ቄጣላ እና ምርቃ እስክያልቅ ድረስ ያሳዩት መቅጥበጥበጥ፤ እነርሱ የቄጣላው ዳራሲያን መሆናቸውን ኣሳብቆባቸዋል።  ነገር ግን ሲዳማ

Prime Minister Abiy Ahmed: Too Good to be True!

By Gizaw Legesse Everything seems too good to be true. I am talking about the political dynamics in Ethiopia. The numerous promises of the newly appointed PM and the bold responses he is giving – the dreamlike speeches he has been making – are pushing me to question: are we really living in that Ethiopia we used to know before. PM Abiy is speaking and acting totally differently than the two decads and plus long culture of EPRDF, the coalition of parties he is now in charge. His words and plans for the new Ethiopia couldn’t be dreamed of in the EPRDF reign. These two things have been vividly seen in the past few weeks: 1) Ethiopia has a parliamentary system of government, but what you see in Abiy is a president in a presidential system. 2) EPRDF adheres an ideology called “Revolutionary Democracy”, a typical Marxist-Leninist view. But if you have listened what Abiy is promising and looking forward to implement, then you will definitely say someone is highly advocating “L

ለውጤት የበቃው የኦሮሞ ህዝብ ንቅናቄ እና ሰሚ ያጣው የሲዳማ ጥያቄ

ዛሬ በሃዋሳ ከተማ የደኢህዴን ካድሬዎች ትክክለኛውን የሲዳማን ህዝብ የሚወክሉ ግለሰቦችን ሳይሆን፤ የራሳቸውን ፖለቲካዊ ፖሮፖጋንዳ የሚደሰኩሩን በመመልመል የሲዳማን ህዝብ ሕገመንግስታዊ የክልል ጥያቄ ለማደፋፈን ያደረጉት ተግባር ኣሳፋሪ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ኣብይ ኣሃመድ በሲዳማዋ የሃዋሳ ከተማ ከህዝብ ከተወጣጡ ተወካዮች ጋር ባደረጉት ውይይት፤ የሲዳማ ህዝብ የክልል ጥያቄ እንዳይቀርብ፤ የደኢህዴን ኣባላት የሰሩት ስራ ሕገመንግስቱ ሃሳብን በነጻነት ለመግለጽ ያስቀመጠውን መብት የጣሰ ብሎም በሲዳማ ህዝብ ላይ የተፈጸመ ኢሰብኣዊ ጥቃት ነው። በኦሮሚያ ተባብሶ የቀጠለዉ ተቃዉሞ ምክንያትና መፍትሄዉ ኢትዮጵያ ዉስጥ በተለያዩ አካባቢዎች በአገሪቱ መንግሥት ላይ ተቃዉሞዎች እየተቀሰቀሱ ነዉ። ከዚህ ቀደም የወልቃይት ጠገዴ አካባቢ ነዋሪዎች ወደ አማራ ክልል እንጠቃለል በማለት ያነሱትን ጥያቄ አሁንም እንዳቀጠሉ ነዉ። ጋምቤላና ሲዳማ አካባቢም ተቃዉሞና ግጭት መቀስቀሱ ተዘግቧል። ያዳምጡ ከሁሉም አካባቢዎች የከፋዉ ግን በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የተለያዩ አካባቢዎች የሚታየዉ ተቃዉሞና ግጭት ነዉ። ከአንድ ዓመት ተኩል በኋላ በድጋሚ ያገረሸውና አራተኛ ወሩን ለያዘው ለዚህ ተቃዉሞ የሚሰጠዉ ምክንያት የተለያየ ነዉ። ከዚህ በፊት ተግባራዊ ይደረጋል የተባለዉ የአዲስ አበባና የኦሮሚያ ልዩ ዞን የተቀናጀ የጋራ ማስተር ፕላን «ይሰረዝ» የሚለዉ ተቃዉሞ ከተነሳ በኋላ መንግሥት እቅዱን መሰረዙን ቢያስታዉቅም ተቃዉሞዉ ተባብሶ እንደቀጠለ ነዉ። በኦሮሚያ ክልል ዳግም ያገረሸዉ አመፅ እና ግጭት ተዋናይ ናቸዉ ባሏቸዉ ኃይሎች ላይ መንግሥት ሕጋዊና የማያዳግም እርምጃ እንደሚወስድ ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ አስታዉቀዋል። «ሂውመን ራይትስ ዎች» የ

በሐዋሳ የሚገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ከከተማዋ ነዋሪዎች ጋር ተወያይተዋል። በውይይታቸው ወቅት ለ...

Prime minister Abiy Ahmed held discussion with the public in Hawassa and addressed questions raised from the public. Here is the audio analysis of Sheger Fm about the questions and the response of the prime minister.

Sidama Buna Vs Buna F.C Yirgalem Stadium

Sidama Buna Vs Buna F.C Yirgalem Stadium

Tweet በጠቅላይ ሚ/ር ዶ/ር አብይ አህመድ የሚመራዉ የኢትዮጵያ መንግስት ለሲዳማ ሕዝብ በአስቸኳይ መመለስ ያለበትን አንገብጋቢ ጥያቄዎችን በተመለከተ ከሲዳማ ኤጀቶ የተሰጠ መግለጫ

Hawaasaa, April 24, 2018 የሲዳማ ህዝብ በታሪኩ ጭቆናን ኣሜን ብሎ ተቀብሎ የኖረበት ጊዜ የለም። ከኣፄዎቹ ጊዜ ኣንስቶ እስካሁኑ የኢህኣዴግ ዘመነ መንግስት ድረስ የተነጠቀዉን እራስን በራስ የማስተዳደርና ሌሎች ወሳኝ ደሞክራትክና ሰብዓዊ መብቶች ለማስመለስ ከፍተኛ ዋጋ ኢየከፈለ ቆይቷል። ለኣብነት ያክል ደርግን ለመጣል በተደረገ አልህ ኣስጨራሽ ትግል ብዙ ሺ የሲዳማ ጀግኖች ተሰዉተዉ ኣብዛኛዉን የሲዳማ ኣካባቢ ህወሃት ኣዲስ ኣበባ ሳይገባ ነፃ ማዉጣት ችለዋል። በኢህአዴግ አገዛዝ ዘመንም ለነጻነቱና ህገ መንግሥቱ የሚሰጠው መብቶቹ እንድተገበሩለት እየጠየቀና ብዙ መስዋዕትም እየከፈለ ያለ ህዝብ ነው። ይሁን እንጅ የኢህአዴግ አገዛዝ ላለፉት ለ27 ዓመታት እራሱ ያዘጋጀውን ህገ መንግስት ከመተግበር ይልቅ የሲዳማን ሕዝብ ማፈንንና መጨቆንን መርጦ ሕዝቡ በራሱ መሬት ላይ የራሱን እድል በራሱ እንዳይወስን ህገመንግሥታዊ መብቱን ተንፍጎ ቆይቷል። ከዚህም በላይ የሲዳማ ህዝብ ጠንክሮ እንዳይወጣና የሚገባውንና የሚመጥነውን ቦታ አንዳያገኝ ብዘ ደባ ሲመታበት ቆይቷል። ለምሳሌ ያህል፤ የዞኑና የክልል ምክር ቤቶች ያፀደቁትን ህገመንግስታዊ የክልል ጥያቄ ባለማስፈፀም የሲዳማን ህዝብ ልማትና ዕድገት ለ27 ኣመታት አንድጉኡተት ተደርጉኣል። ኢትዮጲያ ለዘመናት ለውጭ ምንዛሪ የምትተማንበት የቡና ምርት 40% የሚገኘው ሲዳማ ኣካባቢ ነው። በዚህም ምክናያት ብዙ ነጋዴዎች ጥሩ መንቀሳቀስ ሲጀምሩና ኣቅማቸዉ አየጎለበተ ሲመጣ TPLF ኣልተመቸዉም። ስለዚህ የሲዳማ ነጋዴውች ኣንዴ በደረቅ ቼክ ሌላ ጊዜ ብድር በመከልከል ክፉኛ ኢንዲመቱ ተደረገ። አስከ ዛሬ ድረስ ከጥቂት ነጋዴውች በስተቀር ብዙዎቹ በባንክ እዳ ተጠፍረው ይገኛሉ። በሃዋሳ ከተማና ኣካባቢ የሚኖሩ ገበሬዎች

ለጠቅላይ ሚኒስትሩ አቀባበል ለማድረግ ተዘጋጅተናል.....የሃዋሳ ከተማ ነዋሪዎች

 ለሥራ ጉብኝት ወደ ሃዋሳ ከተማ ለሚመጡት ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ አህመድ አቀባበል ለማድረግ መዘጋጀታቸውን አስተያየታቸውን ለኢዜአ የሰጡ የከተማዋ ነዋሪዎች ገለጹ፡፡ ነዋሪዎቹ እንዳሉት ጠቅላይ ሚንስትሩ ወደ ስልጣን ከመጡበት ጊዜ አንስቶ በተለያዩ የሀገሪቱ ክልሎች በመንቀሳቀስ ከህዝቡ ጋር ያደረጉት ውይይት በህዝቡ የሚነሱ የመልካም አስተዳደርና መሰል ጥያቄዎችን ከምንጩ ለይቶ ለመፍታት ያስችላል፡፡ ከከተማዋ ነዋሪዎች መካከል አቶ ወጤ ቶሼ እንዳሉት፣ ጉብኝቱ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከህዝቡ ጋር የበለጠ እንዲተዋቁና ህዝቡም መሪውን በአግባቡ ተገንዝቦ የሚጠበቅበትን ድጋፍ ለማድረግ ያግዛል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጉብኝቱ ወቅት ከህዝቡ ጋር ውይይት ማድረጋቸው ምላሽ ያላገኙ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመለየት ያስችላል ብለዋል፡፡ በከተማዋ የዱሜ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት ወይዘሮ ሙሉነሽ ልሳኑ በበኩላቸው “ጠቅላይ ሚኒስተሩ  ከተመረጡ ጊዜ አንስቶ በሀገሪቱ ያለው ሰላምና ጸጥታ ይበልጥ እየተጠናከረ መጥቷል፤ በቀጣይም ከእሳቸው ብዙ ነገር እንጠብቃለን” ብለዋል፡፡ ጠቅላይ ሚንስትሩ ወደ ሃዋሳ እንደሚመጡ ከሰሙበት ጊዜ ጀምሮ አቀባበል ለማድረግ በጉጉት እየጠበቁ መሆናቸውንም ነው ወይዘሮ ሙሉነሽ ልሳኑ  የተናገሩት፡፡ በከተማዋ በጀበና ቡና ሥራ የተሰማራችው ወጣት አስራት በዛብህ በበኩሏ የጠቅላይ ሚንስትሩ መምጣት ከተነገራት ጊዜ ጀምሮ ከህብረተሰቡ ጋር በመሆን አቀባበል ለማድረግ መዘጋጀቷን ተናግራለች፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች በመሄድ ከህዝቡ ጋር እያደረጉት ያለው ውይይት ከሕብረተሰቡ ጋር ይበልጥ ተቀራርበው ለመስራት ያላቸውን ፍላጎት የሚያሳይ መሆኑን ገልጻለች። "ህዝቡን በየቦታው እየተዘዋወረ የሚያነጋግር መሪ ሳይ ለመጀ

የደቡብ ሕዝቦችና ኦሮሚያ ክልል አጎራባች ነዋሪዎች የጠቅላይ ሚኒስትሩን በሐዋሳ መገኘት እየተጠባበቁ ነው

ምንጭ ኢዜኣ በደቡብ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦችና አጎራባች ኦሮሚያ ክልል ነዋሪዎች የጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አቢይ አህመድን በሐዋሳ ከተማ መገኘት በጉጉት እየተጠባበቁ ነው፡፡ ዶክተር አቢይ አሕመድ መጋቢት 24 ቀን 2010 ዓ.ም በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት  በጠቅላይ ሚኒስትርነት ሲሾሙ "መጪው ጊዜ በኢትዮጵያችን የፍቅርና የይቅርታ ጊዜ ነው!" በማለት በገለጹት መሰረት ወደ ተለያዩ ክልሎች እየተንሳቀሱ ይገኛሉ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በወቅቱ ባደረጉት ንግግር በኢትዮጵያ ያለውን የመልካም አስተዳደር እጦት፣ ስር የሰደደ ድህነት፣ የዳበረ የዲሞክራሲ ባህል አለመኖርና የተደራጀ የሙስናና ብልሹ አሰራር መስፋፋት ለመዋጋት ከመላው ህዝብ ጋር በመተባበር ለመስራት ቃል መግባታቸው ይታወሳል። ይህን ተከትሎም ወደ ተለያዩ የአገሪቷ አካባቢዎች በመዘዋወር ሰላምና አንድነትን የሚያጠናክር መልዕክት አስተላልፈዋል። ነገ የደቡብ ብሄር፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት መቀመጫ ወደ ሆነችው ሐዋሳ ከተማ በማቅናት ከተለያዩ ህብረተሰብ ክፍሎች ጋር ትውውቅና ውይይት ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ የኢዜአ ሪፖርተር ያነጋገራቸው የሃዋሳ ከተማና የአጎራባች ኦሮሚያ ክልል ነዋሪዎች እንዳሉት የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉብኝት ልዩ ስሜት ፈጥሮባቸዋል፡፡ አቶ ግርሙ ቃውቶ  የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉብኝት እንዳስደሰታቸው ተናግረው፤ በቀጣይ የአገሪቱን አንድነት ጠብቆ ለማስቀጠል ተስፋ መኖሩን ገልፀዋል፡፡ ህዝቡ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር በመተባበር ፊቱን ወደ ልማት እንዲያዞርም መክረዋል፡፡ የአጎራባች ኦሮሚያ ክልል ነዋሪ የሆኑት አቶ አምቤ ጫንጊቻ በበኩላቸው የሲዳማና ኦሮሞ ህዝቦች ለረዥም ጊዜ በአብሮነት የኖሩ ህዝቦች መሆናቸውን ተናግረው፤ “የእነርሱ

An Immediate Demand by the Sidama Nation from PM Abiy Ahmed is Restoration of the Sidama Regional Administration

The Sidama nation has paid immense sacrifices  for regional self determination in the past 130 years. The Sidama King Baallichcha Worawo was brutally assassinated by Lul Seged, the general of King Minelik, in 1895 resisting the forced occupation of the Sidamaland. The Sidama nation never accepted forced annexation and imposition of babaric serfdom by the feudal regime. Led by its renowned heroes such as Mengistu Hamesso, Laanqamo Naare, Takilu Yota, Yetera Boolle, Fiisa Fichcho, Hushula Xaadisso and many others, the Sidama nation fiercely fought against serfdom imposed by the feudal regime. Although serfdom was abolished in 1974, the military regime that usurped political power imposed misguided policies of villagisation and collectivisation that ruined the country’s economy and Sidama was not spared. The Sidama nation took up arms againt the military regime in 1978 under the leadership of the Sidama Liberation Movement and liberated three districts from the regime until 1984.

ኣለታን እና ኣከባቢዋን ይጎብኙ

Ālēta in Southern Nations, Nationalities, and People's Region is a city in Ethiopia about 169 mi (or 272 km) south of Addis Ababa, the country's capital. Local time in Ālēta is now 11:54 PM (Monday). The local timezone is named Africa / Addis Ababa with an UTC offset of 3 hours. We know of 8 airports in the vicinity of Ālēta. The closest airport in Ethiopia is Awassa Airport in a distance of 32 mi (or 52 km), North. Besides the airports, there are other travel options available (check left side). There is one Unesco world heritage site nearby. It's Konso Cultural Landscape in a distance of 115 mi (or 185 km), South-West. Depending on your travel schedule, you might want to pay a visit to some of the following locations: Hawassa, Addis Ababa, Gambela, Marsabit and Mandera. To further explore this place, just scroll down and browse the available info. Let's start with some photos from the area.

የሲዳማ ህዝብ ክልል ይገባኛል ሕገመንግስታዊ ጥያቄ በዶ/ር ኣብይ መፍትሄ ያገኛል የሚል ተስፋ ተሰንቋል

የሲዳማ ህዝብ ክልል ይገባኛል ሕገመንግስታዊ ጥያቄ በዶ / ር ኣብይ መፍትሄ ያገኛል የሚል ተስፋ ሰንቋል በፊታችን ሃሙስ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶ / ር ኣብይ ጋር በሚደረገው ውይይት ላይ የሲዳማ ክልል ጥያቄ ቁጥር ኣንድ ኣጄንዳ ነው ተብሏል። የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከሃዋሳ ከተማና አካባቢው ነዋሪዎች ጋር ሊወያዩ መሆኑን የፋና ብሮድካስቲን ኮፖሬት ሰሞኑን ዘግባል ። በዘጋባው እንደተገለጸው፤ ውይይቱ የፊታችን ሃሙስ የሚደረግ ሲሆን፥ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ም ረቡዕ ሃዋሳ እንደሚገቡ ከ ደቡብ ክልል የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት የወጣ መረጃ ያመላክታል። በቆይታቸውም ከነዋሪዎቹ ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ የሚወያዩ ይሆናል ተብሏል ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከዚህ ቀደም በጅግጅጋ ፤ በጎንደርና ባህር ዳር እና መቐለ ከተሞች በመገኘት ከነዋሪዎች ጋር ውይይት ማድረጋቸው ይታወሳል። የጠቅላይ ሚኒስትሩ የሃዋሳው ውይይት በተመለከተ የወራንቻ ኢንፎርሜችን ኔትዎርክ ያነጋገራቸው የሲዳማ ተወላጆች እንደተናገሩት፤ የሲዳማ ህዝብ በተለያየ ጊዜ ለኣገሪቱ ገዥው ፓርቲ መሪዎች ያቀረባቸው የክልል ይገባኛል ሕገመንግስታዊ ጥያቄ በመጨረሻ በዶ / ር ኣብይ መፍትሄ ያገኛል የሚል ተስፋ ሰንቀዋል።

በሲዳማ ዞን የደኢህዴን ኣመራር ብቃት ማነስ የተነሳ በሚሊዮኖች የሚጠጉ የዞኑ ኣርሶ ኣደሮች በማዳበሪያ እዳ ተዘፍቀዋል

ፎቶ ከክልሉ መንግስት የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ  የፌስቡክገጽ በሲዳማ ዞን የደኢህዴን ኣመራር ብቃት ማነስ የተነሳ በዞኑ ውስጥ በሚገኙ 13 ወረዳዎች ነዋሪ የሆኑ፤ ቀደም ሲል ምርትና ምርታማነትን ለማሰደግ በሚል ሰበብ በቀበሌ ኣመራሮች ተገደው የአፈር ማዳበሪያ የወሰዱ የሲዳማ ኣርሶ ኣደሮች ከግማሽ ቢሊዮን ብር በላይ እዳ መዘፈቃቸው ሰሞኑን በሃዋሳ ከተማ በተካሄደ የዞኑ ምክር ቤት ጉባኤ ላይ ተነግሯል። የወራንቻ ኢንፎርሜሽን ኔትዎርክ ባልደረቦች ከክልሉ መንግስት የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ የፌስቡክ ገጽ ላይ ያገኙት መረጃ እንደሚያመለክተው፤ የሲዳማ ዞን ምክር ቤት በሀዋሳ ከተማ በሲዳማ ባህል አዳራሽ የ 2010 በጀት ዓመት የ 6 ወራት የስራ አፈፃፀሙን፡ የምክር ቤቱን 4 ኛ ዙር 11 ኛ መደበኛ ጉባዔውን በማካሄድ ገምግሟል፡፡ በጉባኤው ላይ የዞኑ ምክር ቤት ዋና ኣፈ ጉባኤ ካላ ሰለሞን ላሌ እንደተናገሩት፦ ቀደም ሲል ምርትና ምርታማነትን ለማሰደግ የተወሰደው የአፈር ማዳበሪያ በአመራሮች አፈፃፀም ውስንነት ምክንያት በወቅቱ እንዲመለስ ባለመደረጉ የተለያዩ ወረዳዎች ከግማሽ ቢሊዮን ብር በላይ ባለዕዳ ሆነዋል። በእዳ ተይዘዋል ከተባሉት ወረዳዎች መካከል በዋናነት፦ የሎካ አባያ 14 ሚሊዮን ብር፣ ቦሪቻ 9 ሚሊዮን ብር፤ በንሳ 9 ሚሊዮን ብር እና አለታ ወንዶ 7 ሚሊዮን ብር በስም የተጠቀሱ ወረዳዎች ሲሆን፤ እነዚህን ጨምሮ በኣጠቃላይ በዞኑ ከሚገኙ ወረዳዎች መካከል 13 ቱ ከግማሽ ቢሊዮን ብር በላይ እዳ ኣለባቸው ተብሏል። ምንም እንኳን ወረዳዎች በገዥው ፓርቲ ደኢህዴን ኣመራሮች የብቃት ማነስ የተነሳ በእዳ የተዘፈቁ ቢሆንም፤ የክልሉ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ወረዳዎቹ ለተለያዩ የመሰረት ልማት ግንባታዎች መተግበሪያነት ከተመደበላቸው ባጄት ላይ

PVH and WWF will work together to help conserve Lake Hawassa

PVH Corp. Announces Partnership with WWF to Preserve and Protect Global Water Resources Makes Three-Year Commitment To Focus on Freshwater Conservation in Ethiopia, India, China and Vietnam Source NEW YORK--( BUSINESS WIRE )--PVH Corp. [NYSE:PVH], parent company of iconic internationally and nationally known brands including   TOMMY HILFIGER ,   CALVIN KLEIN ,   Van Heusen ,   ARROW   and   IZOD , today announced a three-year partnership with leading conservation organization World Wildlife Fund (WWF) to support water stewardship efforts in key sourcing communities for PVH’s businesses and the broader apparel industry. WWF will also work with PVH to develop its water stewardship strategies and connection points to other key sustainability matters. “PVH is excited to announce our partnership with leading environmental nonprofit organization WWF and reinforce our commitment to safeguarding and preserving water resources in our sourcing communities” Under the new agr