Skip to main content

Posts

Showing posts from March, 2018

ሃዋሳ፣ አባያ፣ ጫሞ፣ ዝዋይና ሻላ ሐይቆችን ከደለል ለመታደግ እየተሰራ ነው

የሃዋሳ፣ አባያ፣ ጫሞ፣ ዝዋይና ሻላ ሐይቆችን ከደለል ሙላት ለመከላከል በ65ሺህ ሄክታር መሬት ላይ የአፈርና ውሃ ጥበቃ ሥራ እየተካሄደ መሆኑን የፌደራል ስምጥ ሸለቆ ሐይቆች ባለስልጣን አስታወቀ። ባለስልጣኑ ሰሞኑን በሃዋሳ ከተማ ባዘጋጀው መድረክ የአፈርና ውሃ ጥበቃ ሥራ የስድስት ወራት አፈጻጸምን ገምግሟል። በባለስልጣኑ የተቀናጀ ተፋሰስ እንክብካቤና ወንዝ አመራር ዳይሬክተር አቶ ኤሊያስ ዶጊሶ እንደገለጹት፣ በበጀት ዓመቱ ሐይቆቹን ከደለል ለመከላከል በ23 ወረዳዎች ለሚካሄደው የአፈርና ውሃ ጥበቃ ሥራ ከ12 ሚሊዮን ብር በላይ በጀት ተመድቧል። “እስካሁን በተከናወኑ ተግባራት ከታቀደው መሬት ግማሽ ያክሉ ለምቷል” ያሉት ዳይሬክተሩ፣ የሃዋሳን ሐይቅ ከደለል ለመከላከል በሲዳማ ዞን ቦርቻ ፣ ሸበዲኖና ወንዶገነት ወረዳዎች እንዲሁም በምዕራብ አርሲ ሻላ ወረዳ ላይ የተከናወኑ የእርከንና ሌሎች ስራዎች በተሞክሮነት የሚወሰዱ መሆናቸውን ለአብነት ጠቅሰዋል ። የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ከበደ ካንቹላ በበኩላቸው በተፋሰሶቹ የሚከናወኑ ተግባራት ጠቃሚ ቢሆኑም ሳይንሳዊ ይዘት እንዲኖራቸው ለማድረግ ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጋር በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል ። ሐይቆቹ እየደረሰባቸው ያሉ የጉዳት አይነቶችና መንስኤዎችን ለመለየት ጥናት እየተካሄደ መሆኑንም ተናግረዋል። ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በመንግስት በጀት ታግዞ በሚያከናውነው ሥራ ብቻ ሐይቆቹን በዘላቂነት ከደለል መታደግ ስለማይቻል የተቀናጀ ጥረት ያስፈልጋል" ብለዋል። በተለይ በሐይቆቹ ዳርቻ የሚከናወኑ የኢንቨስትመንት ሥራዎች ተፅዕኖ እንዳይኖራቸው ጥንቃቄ ሊደረግ እንደሚገባ አስገንዘበዋል። በደቡብ ክልል ሲዳማ ዞን ወንዶገነት ወረዳ የአፈርና ውሃ ጥበቃ ሥራ አስተባባሪ አቶ

በተደጋጋሚ ጎርፍ እያጠቃት ያለው ሀዋሳ ከተማ አሳሳቢ ጉዳይ

የሀዋሳ ውብ ከተማ ፊት ፊቱን ከሚታዩት ውብ ስፍራዎች በተጨማሪ ውስጥ ውስጡን ህመም አለባት። ከእድገቷ እኩል እየተፋጠኑ ያሉት የኮብል እስቶን መንገዶቿ ውሃ ቋጥረው መተላለፊያ ይነሳሉ። ውሃ ለማፋሰስ የተዘረጉ ቦዮቿም በዝናብ ወቅት አቅም አጥተው ከተማዋን ለጎርፍ ይዳርጓታል። ምንጭ

Ethiopian Children Learn Human-Centered Design from Carderock Engineer

Photo @ Yared Amanuel spends his spare time using skills he has learned on the job at Naval Surface Warfare Center, Carderock Division – not his engineering skills, but what he has learned in human-centered design. Amanuel, an engineer with Carderock’s Naval Architecture and Engineering Department, just spent a couple of weeks in March in his home country of Ethiopia in the Horn of Africa. While there, he gave several human-centered design seminars to local companies. He also extended his human-centered design knowledge to his non-profit organization, EthioAthletics, which has a mission to “advance lifetime wellness through participation in athletics in Ethiopia.”  According to Garth Jensen, Carderock’s director of innovation, human-centered design starts by putting people at the center – observing and understanding human experience: how people’s complex behaviors, mental models and needs (articulated and not) inform the problem and the solution. It blends design, strategy, quali

Consultant gets award for life-saving surgery in Ethiopia

Mr Tony Clayson (right) seeing patients and doing ward rounds with a colleague from the Orthopaedic Unit in Hawassa Mr Tony Clayson, Consultant Orthopaedic Surgeon at BMI The Highfield Hospital, Rochdale, is being honoured by Rotary International in Great Britain and Ireland’s Champions of Change award for the outstanding volunteering and mentoring work he does in Ethiopia. Poor outcomes and sometimes amputations are common as medical teams do not always understand fully how best to treat severe injuries and sterility of all instruments used has been almost non-existent so the chance of secondary infection following surgery has been very high. Trauma is currently a major cause of death and disability in Africa with ever increasing road traffic development and building programmes but little education in road safety. Mr Clayson's overseas work, in establishing and leading the ‘Developing Sustainable Orthopaedic Trauma Services in Africa’ project supported by Rotary, has

የደቡብ ክልል ቡና አቅራቢዎች ወደ ውጭ በቀጥታ መላክ የሚችሉበትን ስምምነት ፈጸሙ

በአዲሱ የቡና ንግድ አዋጅ መሠረት አቅራቢና ላኪዎች በጋራ እንዲሠሩ ባስቀመጠው ሥርዓት በመጠቀም፣ የደቡብ ቡና አቅራቢዎች ዘርፍ ማኅበር ከመንግሥታዊው የኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ጋር በገባው ስምምነት መሠረት ቡናን በቀጥታ መላክ የሚችልበትን ዕድል አስጠብቋል፡፡ ስምምነቱ ማክሰኞ፣ መጋቢት 4 ቀን 2010 ዓ.ም. በተፈረመበት ወቅት እንደተገለጸው፣ የስምምነቱ ዓላማ ቡና አቅራቢዎች ከላኪዎች ጋር በመሆን ቡናቸውን በቀጥታ ለውጭ ገበያ ማቅረብ እንዲችሉ የሚያበረታታ የአሠራር ሥርዓትን ለማስፈን ነው፡፡ ከዚህ ቀደም አቅራቢዎች ከአምራቾች ያሰባሰቡትን ቡና በቀጥታ ወደ ውጭ ለመላክ ይቸገሩ እንደነበር የቡና አቅራቢዎቹ አማካሪ አቶ ብሩክ ቢተው ገልጸዋል፡፡ ከቡና አላላክ ጋር በተያያዘ ከዚህ ቀደም ሲታይ የቆየውን የገበያ ችግር አዲሱ አዋጁ በመቅረፉ፣ የደቡብ ክልል ቡና አቅራቢዎች እንደ አቅራቢ፣ ኮርፖሬሽኑም እንደ ገዥ በመሆን ቀጥተኛ የንግድ ትስስር የፈጠሩበት የመጀመርያው የግብይት ስምምነት ሆኗል፡፡ ዝርዝር 

Popular posts from this blog

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

የለበሰው ያደፈ ቁምጣና ሹራብ ከቅዝቃዜው አላዳነውም፡፡ ካፊያው ልብሱን አርሶታል፡፡ ሽው እያለ ከሐይቁ የሚነሳው ነፋስ የሚፈጥረው ቅዝቃዜ ያንቀጠቅጠዋል፡፡ የተጫማው ያረጀ ሲሊፐር እግሩን ከምንም አላዳነውም፡፡ በባዶ እግሩ የሚራመድ ያህል ጨቅይቷል፡፡ ተደባዳቢ ይመስል ፊቱ የተሞነጫጨረ ነው፡፡ ገና 12 ዓመቱ ቢሆንም፣ ቁመናው እንደ ትልቅ ሰው ግዙፍ ነው፡፡ የሚለብሰውን እንደ ልቡ ባያገኝም፣ የሚያስፈልገውን ነገር ለማሟላት ቤሳቢስቲን የሌላቸው ወላጆቹን አያስቸግርም፡፡ ከቤተሰቦቹ ጋር ከሚኖሩበት ታቦር ተራራ ጀርባ ወዳለው ሐዋሳ ሐይቅ ከወረደ እንኳንስ የራሱን የቤተሰቦቹንም የዕለት ጉርስ የሚሸፍንበት ገንዘብ አያጣም፡፡ የአስጎብኚነት ዕውቀት፣ ከሐይቁም ውስጥ ዓሳ የሚያጠምድበት መረብም ሆነ ፈቃድ የለውም፡፡ ሙሉቀን (ስሙ ተቀይሯል) እና ጓደኞቹ ሐይቁን ለመጎብኘት የሚሄዱ ጎብኚዎች በካሜራቸው ጥሩ ፎቶ እንዲያስቀሩ ድባቡን የማሳመር ሥራ ይሠራሉ፡፡ ካሜራውን ይዞ ቁጭ ብድግ እያለ ጥሩ ፎቶ ለማንሳት ጥረት የሚያደርግ ሲያዩ፣ ቆርጠው የያዙትን የዓሳ ሥጋ ይዘው ጠጋ ጠጋ ይላሉ፡፡ ቁርጥራጩን የዓሳ ሥጋ ምግብ ለሚቀሙት አባኮዳዎች ሻሞ ይላሉ፡፡ የተወረወረላቸውን ቀድመው ለመቅለብ አባኮዳዎቹ ክንፋቸውን እየመቱ ወደ ላይ ብድግ ይላሉ፡፡ የናሽናል ጆግሪፊ የፎቶግራፍ ባለሙያዎች ያነሱት ዓይነት ፎቶዎች ሳያስቡት ያነሳሉ፡፡ በሁኔታው ተደስተው ደጋግመው ድንቅ ፎቶዎችን ለመውሰድ ሲዘጋጁ እነ ሙሉቀንም አጀንዳቸውን ይፋ ማድረግ ይጀምራሉ፡፡ አቶ ዳዊት አብርሃም ‹‹አንዱን ዓሳ በአሥር ብር ገዝቼ ነው እንዲህ የማዘጋጀው፤›› በማለት በቅድሚያ  መረጃ ይሰጣሉ፡፡ ለቀጣዩ ዜና በዚህ መልኩ እንዲዘጋጁ ካደረጉ በኋላ፣ ሌሎች ሰዎች መቶም ሁለት መቶም ብር እንደሚሰጧቸው ቀለል

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የመንግሥት ስልጠና የምርጫ ቅስቀሳ አካል ነው ብሏል  የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ለምን ወጣ መባሉ ተገቢ አይደለም - ምርጫ ቦርድ ምርጫ ቦርድ ከኢህአዴግ ተፅዕኖ ሙሉ ለሙሉ ነፃ መሆኑ ሳይረጋገጥና የምርጫ አፈፃፀም ችግሮች ሳይወገዱ የምርጫ የጊዜ ሰሌዳ ለማወጅ መዘጋጀቱ ተገቢ አይደለም ሲል ፕ/ር በየነ ጴጥሮስ የሚመሩት ኢማዴ-ደህአፓ ተቃወመ፡፡ መንግስት፤ የዩኒቨርሲቲ መምህራንና ተማሪዎችን ጨምሮ ለተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች እየሰጠ ያለው ስልጠና የምርጫ ቅስቀሳ አካል ነው ሲልም ፓርቲው ኮንኗል፡፡  የኢትዮጵያ ማህበረ ዴሞክራሲ ደቡብ ህዝቦች አንድነት ፓርቲ ሰሞኑን ለብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ባስገባው ግልፅ ደብዳቤ፤ ያለፉት አገር አቀፍና የአካባቢ ምርጫዎች ከመካሄዳቸው በፊት በምርጫ ችግሮችና መፍትሄዎቻቸው ዙሪያ ኢህአዴግ ከተቃዋሚዎች ጋር የሚወያይበት መድረክ እንዲዘጋጅ በተደጋጋሚ ብንጠይቅም እስካሁን ከቦርዱ የተሰጠ ተግባራዊ ምላሽ የለም ብሏል፡፡  ሃገሪቱ “በአንድ አውራ ፓርቲ” ብቸኛ ቁጥጥር ስር መውደቋ አደገኛና አሳሳቢ ነው ያለው ፓርቲው፤ የመድብለ ፓርቲ ስርአት የመገንባት ተስፋችን ጨርሶ እንዳይከስም ቦርዱ ሃላፊነቱን መወጣት እንዳለበት አሳስቧል፡፡ ነፃና ፍትሃዊ ምርጫ የሚካሄድበትን ሁኔታ ለመፍጠር ገዥው ፓርቲና ሃቀኛ ተቃዋሚ ፓርቲዎች የሚወያዩበት መድረክ እንዲያመቻች በህግ ስልጣን የተሰጠው ምርጫ ቦርድ የገባውን ቃል በማጠፍ መድረኩን ሳያመቻች የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማዘጋጀቱ ፋይዳ የለውም ብሏል - ፓርቲው፡፡  ገዥው ፓርቲ ኢህአዴግ በተሻሻለው የምርጫ ህግ፣ ለቦርዱ የተሰጠውን የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ መድረክ የማስተባበር ስልጣን ለመቀማት ታማኝ ፓርቲዎችን በተቃዋሚ ስም አሰባስቦ “የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ መድረክ” በመፍጠር የምርጫ ውድድር አሯሯጭ አሰልፏል ሲ

የ10ኛ እና የ12ኛ ክፍል ማለፊያ ነጥብ ውጤት ነገ ይፋ ይሆናል

አዲስ አበባ ፣ ነሃሴ 23 ፣ 2005 (ኤፍ ቢ ሲ) የ10ኛ ክፍል ማጠቃለያና የ12ኛ ክፍል መሰናዶ ማለፊያ ነጥብ ውጤትን ነገ ይፋ እንደሚያደርግ የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ። የዩኒቨርስቲ መግቢያና ወደ መሰናዶ ማለፊያ ነጥብን ለመወሰን  ፥ የዩኒቨርስቲዎችን ቀጣይ የመቀበል አቅም ከግምት ውስጥ በማስገባት መወሰኑንም ነው ሚኒስቴሩ የገለጸው። በአጠቃላይ 548 ሺህ 138 ተማሪዎች የ10 ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተናውን ወስደው 70 በመቶዎቹ 2 ነጥብ እና ካዛ በላይ ውጤት ሲያስመዘግቡ ፥ በተመሳሳይም የ12ኛ ክፍልን የዩኒቨርስቲ መግቢያ ፈተናን ከወሰዱት መካከል 70 በመቶ የሚሆኑት ተፈታኞች ከ350 ነጥብ በላይ ውጤት ማስመዝገባቸውን ቀደም ሲል  የሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና የፈተናዎች ኤጀንሲ አስታውሷል ። በነገው እለትም የሁለቱም ፈተናዎች የመቁረጫ ውጤት ይፋ ይደረጋል ተብሏል።