የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን "በተለያዩ ምክንያቶች" በሚል ያራዘማቸው የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ተስተካካይ ጨዋታዎች ከነገ ጀምሮ ይካሄዳሉ። ነገ በጅማ ስታዲየም ዘጠኝ ሰአት የጅማ አባጅፋር እግር ኳስ ክለብ ከወላይታ ድቻ አቻው ጋር ጨዋታውን ያደርጋል። በአሰልጣኝ ገብረመድሕን ሐይሌ የሚሰለጥነው ጅማ አባጅፋር በዘንድሮው የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር ከ14 ጨዋታዎች 22 ነጥብ በመሰብሰብ አምስተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። በአንጻሩ ወላይታ ድቻ በሊጉ የነበረውን ጥሩ አጀማመር መቀጠል ባለመቻሉ ከሁለት ወራት በፊት አሰልጣኝ መሳይ ተፈሪን በማሰናበት በዘነበ ፍስሀ ተክቷል። አሰልጣኝ ዘነበ ፍስሀ ቡድኑን ከያዙት ጊዜ ጀምሮ ባለፉት ስድስት ተከታታይ የፕሪሚየር ሊጉ ጨዋታዎች አልተሸነፈም። በአሁኑ ሰአትም በሊጉ 16 ነጥብ በመሰብሰብ ዘጠነኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። የነገው ጨዋታ በአፍሪካ ኮንፌደሬሽን ዋንጫ የቅድመ ማጣሪያ ጨዋታ የዛንዚባሩን ዚማሞቶ ክለብ በድምር ውጤት ሁለት ለአንድ ላሸነፈው ወላይታ ድቻ ከድሉ በኋላ የመጀመሪያው ነው። ሀሙስ የካቲት 22 ቀን 2010 ዓ.ም በሃዋሳ ስታዲየም ሃዋሳ ከተማ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ከቀኑ ዘጠኝ ሰአት ላይ የሚያደርገው ጨዋታ ሌላኛው የተስተካካይ ጨዋታ መርሃ ግብር ነው። በአሰልጣኝ ውበቱ አባተ የሚሰለጥነው ሃዋሳ ከተማ በዘንድሮው የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ያለው አቋም ደከም ያለ ነው ማለት ይቻላል። በአጠቃላይ በሊጉ 14 ጨዋታዎችን አድርጎ 15 ነጥብ በማግኘት በ11ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠ ሲሆን በወራጅ ቀጠና ከሚገኙ ክለቦች በሶስት ነጥብ ብቻ ርቆ ይገኛል። ቅዱስ ጊዮርጊስ ባለፉት አራት ተከታታይ የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ማሸነፍ አልቻለም። ሶስት ጊዜ አቻ ወጥቶ አንድ ጊዜ ተሸንፏል። የሐ
It's about Sidaama!