ፎቶ ከAlthaia |
የቡና
ጣዕም ያለው ሲዳማ ቢራ ሰሞኑን በኣገረ ስፔን
መመረት ጀምሯል። ሲዳማ ቢራን ምርት የጀመሩት
D·Origen Coffee Roasters እና
Althaia Artesana የተባሉት
ሁለት የስፔን ኣገር ኩባኒያዎች
ናቸው። ኩባኒያዎቹ ቡናን ቆልቶ እና ፈጭቶ
በማዘጋጀት የሚያከፋፍሉ፤ ብሎም የተለያዩ
ጣዕሞች ያላቸው የቢራ ኣይነቶችን በማምረት
የሚታወቁ ናቸው።
የወራንቻ
ኢንፎርሜሽን ኔትዎርክ ከኩባኒያዎቹ ድረገጽ
ላይ ያሰባሰባቸው መረጃዎች እንደምያመለክቱት፤
ሲዳማ ቢራ SIDAMA – BROWN COFFEE PORTER ተብሎ የምጠራ እና የሲዳማ ቡና ከሌሎች ለቢራ መስሪያነት
ከሚያገለግሉ ንጥረ ነገሮች ጋር ተደባልቆ
የሚዘጋጅ ነው ። ቢራው በቅርቡ ተቆልቶ የተፈጭ የሲዳማ ቡና ጣዕም
የያዘ እና 5፣8% የኣልኮል ይዘት ያለው ነው።
እንደ
ኩባኒያው ከሆነ፤ ቢራው በሲዳማ ስም የሚጠራ
ቢሆንም ለቢራው መስሪያነት ጥቅም ላይ የሚውለው
ቡና ምንጩ ግን ሲዳማ ሳይሆን የኦሮሚያው ጉጂ
ዞን ነው።
ለመሆኑ
ኣንድ ከሲዳማ ያልሆነ ድርጅት ወይም ኩባኒያ
ምርቶቹን በሲዳማ ህዝብ ስም መጥራት ይችላልን?ይህንን
በተመለከተ የሕግ ባለሙያዎች ምን ይላሉ?
ለተጨማሪ
መረጃ ከታች ይጫኑ
Comments
Post a Comment