ፎቶ ከAlthaia የቡና ጣዕም ያለው ሲዳማ ቢራ ሰሞኑን በኣገረ ስፔን መመረት ጀምሯል። ሲዳማ ቢራን ምርት የጀመሩት D·Origen Coffee Roasters እና Althaia Artesana የ ተባሉት ሁለት የስፔን ኣገር ኩባኒያዎች ናቸው። ኩባኒያዎቹ ቡናን ቆልቶ እና ፈጭቶ በማዘጋጀት የሚያከፋፍሉ፤ ብሎም የተለያዩ ጣዕሞች ያላቸው የቢራ ኣይነቶችን በማምረት የሚታወቁ ናቸው። የወራንቻ ኢንፎርሜሽን ኔትዎርክ ከኩባኒያዎቹ ድረገጽ ላይ ያሰባሰባቸው መረጃዎች እንደምያመለክቱት፤ ሲዳማ ቢራ SIDAMA – BROWN COFFEE PORTER ተብሎ የምጠራ እና የሲዳማ ቡና ከሌሎች ለቢራ መስሪያነት ከሚያገለግሉ ንጥረ ነገሮች ጋር ተደባልቆ የሚዘጋጅ ነው ። ቢራው በቅርቡ ተቆልቶ የተፈጭ የሲዳማ ቡና ጣዕም የያዘ እና 5 ፣ 8% የኣልኮል ይዘት ያለው ነው። እንደ ኩባኒያው ከሆነ፤ ቢራው በሲዳማ ስም የሚጠራ ቢሆንም ለቢራው መስሪያነት ጥቅም ላይ የሚውለው ቡና ምንጩ ግን ሲዳማ ሳይሆን የኦሮሚያው ጉጂ ዞን ነው። ለመሆኑ ኣንድ ከሲዳማ ያልሆነ ድርጅት ወይም ኩባኒያ ምርቶቹን በሲዳማ ህዝብ ስም መጥራት ይችላልን ? ይህንን በተመለከተ የሕግ ባለሙያዎች ምን ይላሉ ? ለተጨማሪ መረጃ ከታች ይጫኑ ሲዳማቢራ
የለበሰው ያደፈ ቁምጣና ሹራብ ከቅዝቃዜው አላዳነውም፡፡ ካፊያው ልብሱን አርሶታል፡፡ ሽው እያለ ከሐይቁ የሚነሳው ነፋስ የሚፈጥረው ቅዝቃዜ ያንቀጠቅጠዋል፡፡ የተጫማው ያረጀ ሲሊፐር እግሩን ከምንም አላዳነውም፡፡ በባዶ እግሩ የሚራመድ ያህል ጨቅይቷል፡፡ ተደባዳቢ ይመስል ፊቱ የተሞነጫጨረ ነው፡፡ ገና 12 ዓመቱ ቢሆንም፣ ቁመናው እንደ ትልቅ ሰው ግዙፍ ነው፡፡ የሚለብሰውን እንደ ልቡ ባያገኝም፣ የሚያስፈልገውን ነገር ለማሟላት ቤሳቢስቲን የሌላቸው ወላጆቹን አያስቸግርም፡፡ ከቤተሰቦቹ ጋር ከሚኖሩበት ታቦር ተራራ ጀርባ ወዳለው ሐዋሳ ሐይቅ ከወረደ እንኳንስ የራሱን የቤተሰቦቹንም የዕለት ጉርስ የሚሸፍንበት ገንዘብ አያጣም፡፡ የአስጎብኚነት ዕውቀት፣ ከሐይቁም ውስጥ ዓሳ የሚያጠምድበት መረብም ሆነ ፈቃድ የለውም፡፡ ሙሉቀን (ስሙ ተቀይሯል) እና ጓደኞቹ ሐይቁን ለመጎብኘት የሚሄዱ ጎብኚዎች በካሜራቸው ጥሩ ፎቶ እንዲያስቀሩ ድባቡን የማሳመር ሥራ ይሠራሉ፡፡ ካሜራውን ይዞ ቁጭ ብድግ እያለ ጥሩ ፎቶ ለማንሳት ጥረት የሚያደርግ ሲያዩ፣ ቆርጠው የያዙትን የዓሳ ሥጋ ይዘው ጠጋ ጠጋ ይላሉ፡፡ ቁርጥራጩን የዓሳ ሥጋ ምግብ ለሚቀሙት አባኮዳዎች ሻሞ ይላሉ፡፡ የተወረወረላቸውን ቀድመው ለመቅለብ አባኮዳዎቹ ክንፋቸውን እየመቱ ወደ ላይ ብድግ ይላሉ፡፡ የናሽናል ጆግሪፊ የፎቶግራፍ ባለሙያዎች ያነሱት ዓይነት ፎቶዎች ሳያስቡት ያነሳሉ፡፡ በሁኔታው ተደስተው ደጋግመው ድንቅ ፎቶዎችን ለመውሰድ ሲዘጋጁ እነ ሙሉቀንም አጀንዳቸውን ይፋ ማድረግ ይጀምራሉ፡፡ አቶ ዳዊት አብርሃም ‹‹አንዱን ዓሳ በአሥር ብር ገዝቼ ነው እንዲህ የማዘጋጀው፤›› በማለት በቅድሚያ መረጃ ይሰጣሉ፡፡ ለቀጣዩ ዜና በዚህ መልኩ እንዲዘጋጁ ካደረጉ በኋላ፣ ሌሎች ሰዎች መቶም ሁለት መቶም ብር እንደሚሰጧቸው ቀለል