Skip to main content

ኢዴፓ አንድ ጠንካራ ተቃዋሚ ፓርቲ እንዲፈጠር ጠየቀ

 አዴፓ በሃገሪቱ አንድ ጠንካራ ተቃዋሚ ፓርቲ እንዲፈጠር ለተቃዋሚዎች፣ ለምሁራንና ለህዝቡ ጥያቄ ያቀረበ ሲሆን በሚቀጥሉት 6 ወራት ይህን ውጥን እውን ለማድረግ በትጋት እንደሚሰራም አስታውቋል፡፡ 
‹‹ጠንካራ ተቃዋሚ ፓርቲ መፍጠር የወቅቱ ቀዳሚና አንገብጋቢ ጥያቄ ነው›› በሚል ፓርቲው ለአዲስ አድማስ በላከው መግለጫ፤ ኢዴፓ የራሱን ጠቅላላ ጉባኤ ለማዘጋጀት ኮሚቴ አቋቁሞ እየተንቀሣቀሰ መሆኑን በመግለፅ ህዝቡ ድጋፉን እንዲሰጠው ጠይቋል፡፡ ‹‹ህዝቡ ባልተደራጀና ባልተቀናጀ ሁኔታ በሃይልና በነውጥ ጭምር እያደረገ ያለው እንቅስቃሴ የሚፈለገውን ለውጥ ሊያመጣ አይችልም›› ያለው ፓርቲው፤ ከዚህ ስጋት በመነሣት ኢዴፓ  ተቃዋሚ ፓርቲዎችና ምሁራን የህዝቡን ትግል በአግባቡ የሚመራ ጠንካራ ፓርቲ ለመፍጠር ተግተው መስራት አለባቸው ብሏል፡፡ 
ቀጣዮቹን 6 ወራት በመጠቀምም ፓርቲው ተጠናክሮ ሊመጣ የሚያስችለውን ጥረት ሁሉ እያደረገ መሆኑን በመግለፅ፤ የጉዳዩ ባለቤት የሆነው ህዝብ፣ መንግስትና ተቃዋሚ ፓርቲዎች ድጋፍ እንዲያደርጉለት ጠይቋል፡፡ 
መንግስት አንድ ጠንካራ ፓርቲ እንዲፈጠር ተገቢውን ድጋፍ ሊያደርግ ይገባል ያለው ኢዴፓ፤ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ውስጣዊ ድክመታቸውን በሃቅ በመገምገምና፣ ራሳቸውን በጥራት በማጠናከር፣ ከእርስ በእርስ መጠላለፍና መነቋቆር ወጥተው አንድ መሆን አለባቸው ብሏል፡፡
‹‹ኢዴፓ በዚህ አጀንዳ እውን መሆን የሚሠጠው ትኩረት ከፍተኛ ነው›› ያለው መግለጫው፤ የፓርቲን ደንብና መመሪያ እንዲሁም ፕሮግራም ከማሻሻል ጀምሮ የፓርቲውን ስያሜ እስከመቀየርና የተናጥል ህልውናውን እስከ ማክሰም የሚደርስ እርምጃ ለመውሠድ ዝግጁ መሆኑን ጠቁሟል፡፡ ይህን የሚያደርገውም አንድ ጠንካራ ተቃዋሚ ፓርቲ በመፍጠር መሆኑን የጠቀሰው ኢዴፓ፤ የሃገሪቱ ምሁራንም ዳር ቆመው ከመታዘብና ከመተቸት ፓርቲዎችን በእውቀታቸውና በገንዘባቸው እንዲደግፉ ጥሪ አቅርቧል፡፡ 
በሃገሪቱ የተፈጠረው የፖለቲካ ቀውስ ረግቦ እውነተኛ የብዙሃን ፓርቲ ስርአት የሚፈጠርበት ሁኔታ እንደሚኖር ፓርቲው ያለውን ተስፋ በመግለጫው አመላክቷል፡፡
source

Comments

Popular posts from this blog

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

የለበሰው ያደፈ ቁምጣና ሹራብ ከቅዝቃዜው አላዳነውም፡፡ ካፊያው ልብሱን አርሶታል፡፡ ሽው እያለ ከሐይቁ የሚነሳው ነፋስ የሚፈጥረው ቅዝቃዜ ያንቀጠቅጠዋል፡፡ የተጫማው ያረጀ ሲሊፐር እግሩን ከምንም አላዳነውም፡፡ በባዶ እግሩ የሚራመድ ያህል ጨቅይቷል፡፡ ተደባዳቢ ይመስል ፊቱ የተሞነጫጨረ ነው፡፡ ገና 12 ዓመቱ ቢሆንም፣ ቁመናው እንደ ትልቅ ሰው ግዙፍ ነው፡፡ የሚለብሰውን እንደ ልቡ ባያገኝም፣ የሚያስፈልገውን ነገር ለማሟላት ቤሳቢስቲን የሌላቸው ወላጆቹን አያስቸግርም፡፡ ከቤተሰቦቹ ጋር ከሚኖሩበት ታቦር ተራራ ጀርባ ወዳለው ሐዋሳ ሐይቅ ከወረደ እንኳንስ የራሱን የቤተሰቦቹንም የዕለት ጉርስ የሚሸፍንበት ገንዘብ አያጣም፡፡ የአስጎብኚነት ዕውቀት፣ ከሐይቁም ውስጥ ዓሳ የሚያጠምድበት መረብም ሆነ ፈቃድ የለውም፡፡ ሙሉቀን (ስሙ ተቀይሯል) እና ጓደኞቹ ሐይቁን ለመጎብኘት የሚሄዱ ጎብኚዎች በካሜራቸው ጥሩ ፎቶ እንዲያስቀሩ ድባቡን የማሳመር ሥራ ይሠራሉ፡፡ ካሜራውን ይዞ ቁጭ ብድግ እያለ ጥሩ ፎቶ ለማንሳት ጥረት የሚያደርግ ሲያዩ፣ ቆርጠው የያዙትን የዓሳ ሥጋ ይዘው ጠጋ ጠጋ ይላሉ፡፡ ቁርጥራጩን የዓሳ ሥጋ ምግብ ለሚቀሙት አባኮዳዎች ሻሞ ይላሉ፡፡ የተወረወረላቸውን ቀድመው ለመቅለብ አባኮዳዎቹ ክንፋቸውን እየመቱ ወደ ላይ ብድግ ይላሉ፡፡ የናሽናል ጆግሪፊ የፎቶግራፍ ባለሙያዎች ያነሱት ዓይነት ፎቶዎች ሳያስቡት ያነሳሉ፡፡ በሁኔታው ተደስተው ደጋግመው ድንቅ ፎቶዎችን ለመውሰድ ሲዘጋጁ እነ ሙሉቀንም አጀንዳቸውን ይፋ ማድረግ ይጀምራሉ፡፡ አቶ ዳዊት አብርሃም ‹‹አንዱን ዓሳ በአሥር ብር ገዝቼ ነው እንዲህ የማዘጋጀው፤›› በማለት በቅድሚያ  መረጃ ይሰጣሉ፡፡ ለቀጣዩ ዜና በዚህ መልኩ እንዲዘጋጁ ካደረጉ በኋላ፣ ሌሎች ሰዎች መቶም ሁለት መቶም ብር እንደሚሰጧቸው ቀለል

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የመንግሥት ስልጠና የምርጫ ቅስቀሳ አካል ነው ብሏል  የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ለምን ወጣ መባሉ ተገቢ አይደለም - ምርጫ ቦርድ ምርጫ ቦርድ ከኢህአዴግ ተፅዕኖ ሙሉ ለሙሉ ነፃ መሆኑ ሳይረጋገጥና የምርጫ አፈፃፀም ችግሮች ሳይወገዱ የምርጫ የጊዜ ሰሌዳ ለማወጅ መዘጋጀቱ ተገቢ አይደለም ሲል ፕ/ር በየነ ጴጥሮስ የሚመሩት ኢማዴ-ደህአፓ ተቃወመ፡፡ መንግስት፤ የዩኒቨርሲቲ መምህራንና ተማሪዎችን ጨምሮ ለተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች እየሰጠ ያለው ስልጠና የምርጫ ቅስቀሳ አካል ነው ሲልም ፓርቲው ኮንኗል፡፡  የኢትዮጵያ ማህበረ ዴሞክራሲ ደቡብ ህዝቦች አንድነት ፓርቲ ሰሞኑን ለብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ባስገባው ግልፅ ደብዳቤ፤ ያለፉት አገር አቀፍና የአካባቢ ምርጫዎች ከመካሄዳቸው በፊት በምርጫ ችግሮችና መፍትሄዎቻቸው ዙሪያ ኢህአዴግ ከተቃዋሚዎች ጋር የሚወያይበት መድረክ እንዲዘጋጅ በተደጋጋሚ ብንጠይቅም እስካሁን ከቦርዱ የተሰጠ ተግባራዊ ምላሽ የለም ብሏል፡፡  ሃገሪቱ “በአንድ አውራ ፓርቲ” ብቸኛ ቁጥጥር ስር መውደቋ አደገኛና አሳሳቢ ነው ያለው ፓርቲው፤ የመድብለ ፓርቲ ስርአት የመገንባት ተስፋችን ጨርሶ እንዳይከስም ቦርዱ ሃላፊነቱን መወጣት እንዳለበት አሳስቧል፡፡ ነፃና ፍትሃዊ ምርጫ የሚካሄድበትን ሁኔታ ለመፍጠር ገዥው ፓርቲና ሃቀኛ ተቃዋሚ ፓርቲዎች የሚወያዩበት መድረክ እንዲያመቻች በህግ ስልጣን የተሰጠው ምርጫ ቦርድ የገባውን ቃል በማጠፍ መድረኩን ሳያመቻች የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማዘጋጀቱ ፋይዳ የለውም ብሏል - ፓርቲው፡፡  ገዥው ፓርቲ ኢህአዴግ በተሻሻለው የምርጫ ህግ፣ ለቦርዱ የተሰጠውን የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ መድረክ የማስተባበር ስልጣን ለመቀማት ታማኝ ፓርቲዎችን በተቃዋሚ ስም አሰባስቦ “የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ መድረክ” በመፍጠር የምርጫ ውድድር አሯሯጭ አሰልፏል ሲ

የጀርመን መንግስት ዜጎቹ ወደ ሀዋሳ እና አከባቢዋ በሚጓዙበት ጊዜ ጥንቃቄ እንዲያድርጉ መከረ

የጀርመን መንግስት ዜጎቹ ወደ ሀዋሳ እና አከባቢዋ በሚጓዙበት ጊዜ ጥንቃቄ እንዲያድርጉ አስጠነቀቀ ዛሬ በአገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ድረገጽ ላይ ባወጣው ማስጠንቀቂያ እንዳመለከተው፤ የጀርመን ዜጎች በኢትዮጵያ ውስጥ በሚቀሳቀሱበት ጊዜ ከጸጥታ አንጻር ማድረግ ባለባቸው እና መሄድ በሌለባቸው የኢትዮጵያ አከባቢዎች ላይ ሰፋ ያለ መረጃ ስጥቷል። በጽሁፉ ላይ እንደተጠቀሰው በኢትዮጵያ በበርካታ አከባቢዎች ግጭቶች መኖራቸው የተጠቀስ ሲሆን፤ በሲዳማ ክልል የነበረውን ግጭት አስታውሷል። አክሎም በወላይታ ዞን የጸጥታ ስጋት መኖሩን ጠቅሶ ወደ ሲዳማዋ ዋና ከተማ ሀዋሳ የምንቀሳቀሱ ዜጎቿ የተለየ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ መክሯል። ዝርዝሩን ከታች ከሊንኩ ላይ ያንቡ Äthiopien: Reise- und Sicherheitshinweise