በፌዴራል ተቋማት የሠራተኞች የብሔር ስብጥር የተመጣጠነ እንዲሆን ሊደረግ ነው - የፓርላማ አባሉ በገጠማቸው ጉርምርምታ ተቃውሟቸውን ገለጹ በሁሉም የፌዴራል መንግሥት ተቋማት ውስጥ የሠራተኞች ብቃትና ክህሎትን ባረጋገጠ መንገድ የተመጣጠነ የብሔር ስብጥር እንዲፈጠር እየተሠራ መሆኑን፣ በተገቢው የሕግ ማዕቀፍ እንዲደገፍም እንደሚያደርግ የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የማኅበራዊ ዘርፍ አስተባባሪና የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ሚኒስትሯ ወ/ሮ አስቴር ማሞ፣ በሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ላይ ታኅሳስ 14 ቀን 2008 ዓ.ም. ፓርላማው በተወያየበት ወቅት ለተነሱ ጥያቄዎች በሰጡት ምላሽ ነው፣ የፌዴራል መንግሥት ተቋማት የፌዴራል ሥርዓቱን መምሰል እንዲችሉ የተመጣጠነ የብሔር ስብጥርን በተቋማቸው ውስጥ መፍጠር እንደሚገባቸው የተናገሩት፡፡ የተመጣጠነ የብሔር ስብጥር በፌዴራል ተቋማቱ ለመፍጠር ሲባል ሠራተኞችን በብቃትና በክህሎት መምረጥ መርህ ላይ ምንም ዓይነት ተፅዕኖ መፍጠር እንደማይገባ አፅንኦት ሰጥተዋል፡፡ ሚኒስቴሩ የብሔር ስብጥሩን ተግባራዊ ለማድረግ ጥናቶችንና ተሞክሮዎችን በመገምገም ላይ እንደሆነና ለትግበራውም ተገቢ የሆነ የሕግ ማዕቀፍ እንደሚዘጋጅ ወ/ሮ አስቴር ገልጸዋል፡፡ በአሁኑ ጊዜ በፌዴራል ተቋማት ውስጥ ያለውን ተሞክሮ ለመገምገም በተሞከረበት ወቅት፣ ብሔራዊ ባንክ ብቻ ሞዴል ሊሆን የሚችል ልምድ ይዞ እንደተገኘ፣ በባንኩ ውስጥ 37 ብሔሮችን የሚወክሉ ሠራተኞች በሥራ ላይ እንደሚገኙ በምሳሌነት አውስተዋል፡፡ ከብሔር ብሔረሰብ ስብጥር ውጪ የወጣቶችና የፆታ ስብጥር በየፌዴራል ተቋማቱ ተመጣጥኖ ሊቀመጥ እንደሚገባም ሚኒስትሯ ገልጸዋል፡፡ የፌዴራል ተቋማት ሠራተኞች የብሔር ስጥር
It's about Sidaama!