ሰሞኑን በመቀሌ ከተማ ሲካሄድ የሰነበተው 10ኛ የኢህኣዴግ ድርጅታዊ ጉባኤ የፓርቲውን ከፍተኛ ኣመራሮች በመምረጥ የተጠናቀቀ ሲሆን፤ ድርጅቱ በመከተል ላይ ባለው የመተካካት ፖሊሲ መስረት ኣዳዲስ የፓርቲው መርዎች ብጠበቁም ኣዲስ ፍት ሳይታይ ቀርቷል። ፎቶ ከፋና ድረገጽ ዝርዝር ወሬው ያፋና ነው፦ ( ኤፍ.ቢ.ሲ ) ካለፈው አርብ ጀምሮ 10ኛ ድርጅታዊ ጉባኤውን በመቀሌ ሲያካሂድ የቆየው የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር /ኢህአዴግ/ አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝን የግንባሩ ሊቀመንበር በማድረግ በድጋሚ መርጧል። ድርጅቱ አቶ ደመቀ መኮንንን ደግሞ በምክትል ሊቀመንበርነት መርጧል። አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ መስከረም ወር 2005 ዓመተ ምህረት በተካሄደው የኢህአዴግ ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤ ለመጀመሪያ ጊዜ በሊቀመንበርነት መመረጣቸው ይታወሳል። ዛሬም 180 አባላት ያሉት የኢህአዴግ ምክር ቤት አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝን በድጋሚ ግንባሩን ለቀጣዮቹ ሁለት ዓመታት ተኩል ግንባሩን በሊቀመንበርነት እንዲመሩ መርጧል። አቶ ሀይለማርያም ባለፈው ሳምንት በሀዋሳ በተካሄደው የኢህአዴግ አባል ድርጅት በሆነው የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ /ደኢህዴን/ የንቅናቄው ሊቀመንበር አድርጎ እንደመረጣቸው ይታወቃል። እንዲሁም የድርጅቱ የኦዲት እና ቁጥጥር ኮሚሽን አባላት እና አመራሮች ተሰይመዋል። 10ኛው ድርጅታዊ ጉባኤ ባለ ዘጠኝ ነጥብ የአቋም መግለጫ በማውጣትም ተጠናቋል። ጉባኤተኞቹ በአገሪቱ የተጀመረውን ፈጣን እድገት ከህዝቡ ጋር በመሆን ለማስቀጠል ቃል ገብተዋል በመግለጫቸው። የመልካም አስተዳደር ችግርን ለመፍታትም የሞት ሽረት ትግል እናደርጋለን ብለዋል። የኢህአዴግ ሊቀመንበር አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ የጉባኤውን መጠናቀቅ አስመ
የለበሰው ያደፈ ቁምጣና ሹራብ ከቅዝቃዜው አላዳነውም፡፡ ካፊያው ልብሱን አርሶታል፡፡ ሽው እያለ ከሐይቁ የሚነሳው ነፋስ የሚፈጥረው ቅዝቃዜ ያንቀጠቅጠዋል፡፡ የተጫማው ያረጀ ሲሊፐር እግሩን ከምንም አላዳነውም፡፡ በባዶ እግሩ የሚራመድ ያህል ጨቅይቷል፡፡ ተደባዳቢ ይመስል ፊቱ የተሞነጫጨረ ነው፡፡ ገና 12 ዓመቱ ቢሆንም፣ ቁመናው እንደ ትልቅ ሰው ግዙፍ ነው፡፡ የሚለብሰውን እንደ ልቡ ባያገኝም፣ የሚያስፈልገውን ነገር ለማሟላት ቤሳቢስቲን የሌላቸው ወላጆቹን አያስቸግርም፡፡ ከቤተሰቦቹ ጋር ከሚኖሩበት ታቦር ተራራ ጀርባ ወዳለው ሐዋሳ ሐይቅ ከወረደ እንኳንስ የራሱን የቤተሰቦቹንም የዕለት ጉርስ የሚሸፍንበት ገንዘብ አያጣም፡፡ የአስጎብኚነት ዕውቀት፣ ከሐይቁም ውስጥ ዓሳ የሚያጠምድበት መረብም ሆነ ፈቃድ የለውም፡፡ ሙሉቀን (ስሙ ተቀይሯል) እና ጓደኞቹ ሐይቁን ለመጎብኘት የሚሄዱ ጎብኚዎች በካሜራቸው ጥሩ ፎቶ እንዲያስቀሩ ድባቡን የማሳመር ሥራ ይሠራሉ፡፡ ካሜራውን ይዞ ቁጭ ብድግ እያለ ጥሩ ፎቶ ለማንሳት ጥረት የሚያደርግ ሲያዩ፣ ቆርጠው የያዙትን የዓሳ ሥጋ ይዘው ጠጋ ጠጋ ይላሉ፡፡ ቁርጥራጩን የዓሳ ሥጋ ምግብ ለሚቀሙት አባኮዳዎች ሻሞ ይላሉ፡፡ የተወረወረላቸውን ቀድመው ለመቅለብ አባኮዳዎቹ ክንፋቸውን እየመቱ ወደ ላይ ብድግ ይላሉ፡፡ የናሽናል ጆግሪፊ የፎቶግራፍ ባለሙያዎች ያነሱት ዓይነት ፎቶዎች ሳያስቡት ያነሳሉ፡፡ በሁኔታው ተደስተው ደጋግመው ድንቅ ፎቶዎችን ለመውሰድ ሲዘጋጁ እነ ሙሉቀንም አጀንዳቸውን ይፋ ማድረግ ይጀምራሉ፡፡ አቶ ዳዊት አብርሃም ‹‹አንዱን ዓሳ በአሥር ብር ገዝቼ ነው እንዲህ የማዘጋጀው፤›› በማለት በቅድሚያ መረጃ ይሰጣሉ፡፡ ለቀጣዩ ዜና በዚህ መልኩ እንዲዘጋጁ ካደረጉ በኋላ፣ ሌሎች ሰዎች መቶም ሁለት መቶም ብር እንደሚሰጧቸው ቀለል