ምንጭ፦ ሪፖርተር በሲዳማ ውስጥ አንዲት ስመ ገናና እና ታላቅ ንግሥት ነበረች፡፡ ይች ታላቅና ስመ ገናና ንግሥት የወንዶችን የበላይነት ሥርዓት አስወግዳ የሴቶችን የበላይነት ለመመሥረት ጥረት ያደረገች ስትሆን በጀግንነቷ ወደር እንዳልነበራት ይነገርላታል፡፡ ሆኖም ስለዚች ታላቅ ንግሥት ትኩረት የተሰጠው ካለፉት አሥር እና አሥራ አምስት ዓመታት ወዲህ ነው፡፡ በዚህ ረገድ በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል በሲዳማ ዞን መጠነኛ ሥራዎች ተሠርተዋል፡፡ ከእነዚህም ውስጥ በትውልድ ስፍራዋ በይርጋለም የምርምር ተቋም በስሟ ተቋቁሟል፡፡ በሐዋሳ ውስጥም አደባባይና የጉባኤ አዳራሹ እርሷን ለማስታወስ በሚያስችል መልኩ ተቋቁመዋል፡፡ ሆኖም ስለዚህ ታላቅ ንግሥት የምናገኛቸው የሥነጽሑፍ ሥራዎች ውሱን ናቸው፡፡ ስለሆነም ወጣቱ ትውልድ ንግሥት ፉራንና ሌሎችም በአፈታሪክ የምናውቃቸው የአገራችንን ታላላቅ ሴቶች የበለጠ እንዲያጠና በማሰብ ይህ ጽሑፍ ተዘጋጅቷል፡፡ የንግሥት ፉራን አፈታሪክ ስንመለከተው በጣም ትልቅ ነገር ግን የማይታወቅ ድንቅ ለልብ ወለድ፣ ለድራማ፣ ለፊልምና ለሌሎችም የሥነ ጽሑፍ ሥራ¬ዎ‹ የሚጠቅም ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ የንግሥት ፉራ አፈ ታሪክ እንደትልቅ ባህላዊ ሀብትና እሴት ባለመቆጠሩ ምክንያት በተለይም ያለፈው አንድ ትውልድ ይህችን ንግሥት በከፋ ሁኔታ ረስቷት፣ ወይም እርባና ቢስ ተረት ነው በሚል አስተሳሰብ ትቷት ነበር፡፡ ይህም ሆኖ ታሪኳ በጣም ጠንካራ በመሆኑ ምክንያት አልፎ አልፎም ቢሆን በመገኛኛ ብዙኃን ብቅ ማለቷ አልቀረም፡፡ ጸሐፊው ከ1970-1976 በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የሕፃናትና የወጣቶች ፕሮግራም አዘጋጅና አቅራቢ ሆኖ ሲሠራ የሲዳማ ወጣቶች ኪነት ቡድን አባል ሆኖ የተዋወቀው አብርሃም ረታ ዓለሙ
የለበሰው ያደፈ ቁምጣና ሹራብ ከቅዝቃዜው አላዳነውም፡፡ ካፊያው ልብሱን አርሶታል፡፡ ሽው እያለ ከሐይቁ የሚነሳው ነፋስ የሚፈጥረው ቅዝቃዜ ያንቀጠቅጠዋል፡፡ የተጫማው ያረጀ ሲሊፐር እግሩን ከምንም አላዳነውም፡፡ በባዶ እግሩ የሚራመድ ያህል ጨቅይቷል፡፡ ተደባዳቢ ይመስል ፊቱ የተሞነጫጨረ ነው፡፡ ገና 12 ዓመቱ ቢሆንም፣ ቁመናው እንደ ትልቅ ሰው ግዙፍ ነው፡፡ የሚለብሰውን እንደ ልቡ ባያገኝም፣ የሚያስፈልገውን ነገር ለማሟላት ቤሳቢስቲን የሌላቸው ወላጆቹን አያስቸግርም፡፡ ከቤተሰቦቹ ጋር ከሚኖሩበት ታቦር ተራራ ጀርባ ወዳለው ሐዋሳ ሐይቅ ከወረደ እንኳንስ የራሱን የቤተሰቦቹንም የዕለት ጉርስ የሚሸፍንበት ገንዘብ አያጣም፡፡ የአስጎብኚነት ዕውቀት፣ ከሐይቁም ውስጥ ዓሳ የሚያጠምድበት መረብም ሆነ ፈቃድ የለውም፡፡ ሙሉቀን (ስሙ ተቀይሯል) እና ጓደኞቹ ሐይቁን ለመጎብኘት የሚሄዱ ጎብኚዎች በካሜራቸው ጥሩ ፎቶ እንዲያስቀሩ ድባቡን የማሳመር ሥራ ይሠራሉ፡፡ ካሜራውን ይዞ ቁጭ ብድግ እያለ ጥሩ ፎቶ ለማንሳት ጥረት የሚያደርግ ሲያዩ፣ ቆርጠው የያዙትን የዓሳ ሥጋ ይዘው ጠጋ ጠጋ ይላሉ፡፡ ቁርጥራጩን የዓሳ ሥጋ ምግብ ለሚቀሙት አባኮዳዎች ሻሞ ይላሉ፡፡ የተወረወረላቸውን ቀድመው ለመቅለብ አባኮዳዎቹ ክንፋቸውን እየመቱ ወደ ላይ ብድግ ይላሉ፡፡ የናሽናል ጆግሪፊ የፎቶግራፍ ባለሙያዎች ያነሱት ዓይነት ፎቶዎች ሳያስቡት ያነሳሉ፡፡ በሁኔታው ተደስተው ደጋግመው ድንቅ ፎቶዎችን ለመውሰድ ሲዘጋጁ እነ ሙሉቀንም አጀንዳቸውን ይፋ ማድረግ ይጀምራሉ፡፡ አቶ ዳዊት አብርሃም ‹‹አንዱን ዓሳ በአሥር ብር ገዝቼ ነው እንዲህ የማዘጋጀው፤›› በማለት በቅድሚያ መረጃ ይሰጣሉ፡፡ ለቀጣዩ ዜና በዚህ መልኩ እንዲዘጋጁ ካደረጉ በኋላ፣ ሌሎች ሰዎች መቶም ሁለት መቶም ብር እንደሚሰጧቸው ቀለል