Skip to main content

Posts

Showing posts from February, 2015

ካላ ዳንቦባ ናቲ ስለ ሲዳማ ምን ኣሉ?

‹‹ገዥው ፓርቲም ሆነ ተቃዋሚዎች እንዲህ እናደርጋቸዋለን የሚሏቸው ነገሮች እጅግ ጠቅለል ያሉና ያልተጣሩ ናቸው›› ዶ/ር ካሣሁን ብርሃኑ፣ የፖለቲካ ሳይንስ ባለሙያ

ዶ/ር ካሣሁን ብርሃኑ የፖለቲካ ሳይንስ ባለሙያ ሲሆኑ፣ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ጉልህ ሥፍራ የሚሰጣቸው ጉዳዮች ላይ በርካታ የምርምር ሥራዎችን አሳትመዋል፡፡ ከእነዚህ ሥራዎች መካከል ትልቅ ትኩረት የሰጡት በገዥውና በተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች ባህርይ ላይ ነው፡፡ ይህን ምክንያት በማድረግ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች በምርጫ ቅስቀሳ በሚያሳዩት ባህርይ ዙሪያ  ሰለሞን ጎሹ  ዶ/ር ካሣሁን ብርሃኑን አነጋግሯቸዋል፡፡ ሪፖርተር፡- የምርጫ ቅስቀሳ አስፈላጊነትን እንዴት ይገልጹታል? ዶ/ር ካሣሁን፡-   ብዙ ፓርቲዎች በሕግ ተፈቅዶ በሚንቀሳቀሱበት የፖለቲካ ሥርዓት ውስጥ የምርጫ ቅስቀሳ አስፈላጊ ነው፡፡ ፓርቲዎች የፖለቲካ፣ የማኅበራዊና የኢኮኖሚያዊ ፕሮግራም ሊኖራቸው ይገባል፡፡ የምርጫ ቅስቀሳ ለማድረግ ሥርዓቱ የምርጫ ውድድርን የሚፈቅድ መሆን አለበት፡፡ ምክንያቱም የምርጫ ቅስቀሳ እንደ ኢሕአፓና መኢሶን በድብቅ የምታካሂደው አይደለም፡፡ ሕዝቡን በግልጽ ሰብስበህ ፕሮግራምህን የምታስተዋውቅበትና ከሌሎች የሚሻልበትን መንገድ የምታሳይበት ዘዴ ነው፡፡ ፓርቲው ሥልጣን ቢይዝ ከሌሎች በተሻለ የመራጩን ሕዝብ ፍላጎት እንደሚያሟላ፣ የአገሪቱን ጥቅም እንደሚያስጠብቅ፣ የኅብረተሰቡን ደኅንነት እንደሚጠብቅ የሚገልጽበት መሣሪያ ነው፡፡ ፓርቲዎች ፕሮግራማቸውን በየጊዜው ሊያስተዋውቁ ይችላሉ፡፡ የምርጫ ቅስቀሳ ግን በምርጫ ጊዜ ነው የሚካሄደው፡፡ በተቻለ መጠን የምርጫ ድጋፍ የሚያሰባስቡበት ነው፡፡ የምርጫ ቅስቀሳን በተሳካ ሁኔታ ለመፈጸም የገንዘብ አቅም፣ የሚዲያ ተደራሽነት፣ አመቺ ደኅንነትና ነፃነት ያስፈልጋል፡፡ የፖለቲካ ሥርዓቱ ለጤናማ የብዙኃን ፓርቲ ውድድር አመቺ ነው ወይ የሚለው በእርግጥ አጠያያቂ ነው፡፡ ለምሳሌ የሕዝብ ወይም የመንግሥት ሚዲያን በእኩልነት ባይሆን እንኳን

ከበልግ ዝናብ መዘገየት ጋር ተያይዞ በሲዳማ የምግብ እጥረት ልከሰት ይችላል ተባለ

ከበልግ ዝናብ መዘገየት ጋር ተያይዞ በሲዳማ የምግብ እጥረት ልከሰት ይችላል ተባለ፤ ካለፈው የጥር ወር ጀምሮ ከበንሳ  እና ቡርሳ ወረዳዎች በስተቀር ኣብዛኛዎቹ የሲዳማ ወረዳዎች በድርቅ ተመተዋል፤ Food Security Outlook Update March to May rains may not fully restore rangelands in pastoral areas In most parts of  Southern Nations, Nationalities, and Peoples’ Region (SNNPR) , three-to-five days of  Sapie  rains fell in January. However, this year, the rest of January has been remained dry except in Bensa and Bursa Woredas of Sidama Zone and Konta Special Woreda where there were light showers fell during the third week of January.  Belg  rains typically start in early February in parts of SNNPR, but they have not yet started. Sweet potatoes, other root crops, and to some extent maize were planted in November, and they have reached the vegetative stage. However, many of the crops are wilting. Read more at:   www.fews.net

Popular posts from this blog

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

የለበሰው ያደፈ ቁምጣና ሹራብ ከቅዝቃዜው አላዳነውም፡፡ ካፊያው ልብሱን አርሶታል፡፡ ሽው እያለ ከሐይቁ የሚነሳው ነፋስ የሚፈጥረው ቅዝቃዜ ያንቀጠቅጠዋል፡፡ የተጫማው ያረጀ ሲሊፐር እግሩን ከምንም አላዳነውም፡፡ በባዶ እግሩ የሚራመድ ያህል ጨቅይቷል፡፡ ተደባዳቢ ይመስል ፊቱ የተሞነጫጨረ ነው፡፡ ገና 12 ዓመቱ ቢሆንም፣ ቁመናው እንደ ትልቅ ሰው ግዙፍ ነው፡፡ የሚለብሰውን እንደ ልቡ ባያገኝም፣ የሚያስፈልገውን ነገር ለማሟላት ቤሳቢስቲን የሌላቸው ወላጆቹን አያስቸግርም፡፡ ከቤተሰቦቹ ጋር ከሚኖሩበት ታቦር ተራራ ጀርባ ወዳለው ሐዋሳ ሐይቅ ከወረደ እንኳንስ የራሱን የቤተሰቦቹንም የዕለት ጉርስ የሚሸፍንበት ገንዘብ አያጣም፡፡ የአስጎብኚነት ዕውቀት፣ ከሐይቁም ውስጥ ዓሳ የሚያጠምድበት መረብም ሆነ ፈቃድ የለውም፡፡ ሙሉቀን (ስሙ ተቀይሯል) እና ጓደኞቹ ሐይቁን ለመጎብኘት የሚሄዱ ጎብኚዎች በካሜራቸው ጥሩ ፎቶ እንዲያስቀሩ ድባቡን የማሳመር ሥራ ይሠራሉ፡፡ ካሜራውን ይዞ ቁጭ ብድግ እያለ ጥሩ ፎቶ ለማንሳት ጥረት የሚያደርግ ሲያዩ፣ ቆርጠው የያዙትን የዓሳ ሥጋ ይዘው ጠጋ ጠጋ ይላሉ፡፡ ቁርጥራጩን የዓሳ ሥጋ ምግብ ለሚቀሙት አባኮዳዎች ሻሞ ይላሉ፡፡ የተወረወረላቸውን ቀድመው ለመቅለብ አባኮዳዎቹ ክንፋቸውን እየመቱ ወደ ላይ ብድግ ይላሉ፡፡ የናሽናል ጆግሪፊ የፎቶግራፍ ባለሙያዎች ያነሱት ዓይነት ፎቶዎች ሳያስቡት ያነሳሉ፡፡ በሁኔታው ተደስተው ደጋግመው ድንቅ ፎቶዎችን ለመውሰድ ሲዘጋጁ እነ ሙሉቀንም አጀንዳቸውን ይፋ ማድረግ ይጀምራሉ፡፡ አቶ ዳዊት አብርሃም ‹‹አንዱን ዓሳ በአሥር ብር ገዝቼ ነው እንዲህ የማዘጋጀው፤›› በማለት በቅድሚያ  መረጃ ይሰጣሉ፡፡ ለቀጣዩ ዜና በዚህ መልኩ እንዲዘጋጁ ካደረጉ በኋላ፣ ሌሎች ሰዎች መቶም ሁለት መቶም ብር እንደሚሰጧቸው ቀለል

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የመንግሥት ስልጠና የምርጫ ቅስቀሳ አካል ነው ብሏል  የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ለምን ወጣ መባሉ ተገቢ አይደለም - ምርጫ ቦርድ ምርጫ ቦርድ ከኢህአዴግ ተፅዕኖ ሙሉ ለሙሉ ነፃ መሆኑ ሳይረጋገጥና የምርጫ አፈፃፀም ችግሮች ሳይወገዱ የምርጫ የጊዜ ሰሌዳ ለማወጅ መዘጋጀቱ ተገቢ አይደለም ሲል ፕ/ር በየነ ጴጥሮስ የሚመሩት ኢማዴ-ደህአፓ ተቃወመ፡፡ መንግስት፤ የዩኒቨርሲቲ መምህራንና ተማሪዎችን ጨምሮ ለተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች እየሰጠ ያለው ስልጠና የምርጫ ቅስቀሳ አካል ነው ሲልም ፓርቲው ኮንኗል፡፡  የኢትዮጵያ ማህበረ ዴሞክራሲ ደቡብ ህዝቦች አንድነት ፓርቲ ሰሞኑን ለብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ባስገባው ግልፅ ደብዳቤ፤ ያለፉት አገር አቀፍና የአካባቢ ምርጫዎች ከመካሄዳቸው በፊት በምርጫ ችግሮችና መፍትሄዎቻቸው ዙሪያ ኢህአዴግ ከተቃዋሚዎች ጋር የሚወያይበት መድረክ እንዲዘጋጅ በተደጋጋሚ ብንጠይቅም እስካሁን ከቦርዱ የተሰጠ ተግባራዊ ምላሽ የለም ብሏል፡፡  ሃገሪቱ “በአንድ አውራ ፓርቲ” ብቸኛ ቁጥጥር ስር መውደቋ አደገኛና አሳሳቢ ነው ያለው ፓርቲው፤ የመድብለ ፓርቲ ስርአት የመገንባት ተስፋችን ጨርሶ እንዳይከስም ቦርዱ ሃላፊነቱን መወጣት እንዳለበት አሳስቧል፡፡ ነፃና ፍትሃዊ ምርጫ የሚካሄድበትን ሁኔታ ለመፍጠር ገዥው ፓርቲና ሃቀኛ ተቃዋሚ ፓርቲዎች የሚወያዩበት መድረክ እንዲያመቻች በህግ ስልጣን የተሰጠው ምርጫ ቦርድ የገባውን ቃል በማጠፍ መድረኩን ሳያመቻች የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማዘጋጀቱ ፋይዳ የለውም ብሏል - ፓርቲው፡፡  ገዥው ፓርቲ ኢህአዴግ በተሻሻለው የምርጫ ህግ፣ ለቦርዱ የተሰጠውን የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ መድረክ የማስተባበር ስልጣን ለመቀማት ታማኝ ፓርቲዎችን በተቃዋሚ ስም አሰባስቦ “የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ መድረክ” በመፍጠር የምርጫ ውድድር አሯሯጭ አሰልፏል ሲ

የ10ኛ እና የ12ኛ ክፍል ማለፊያ ነጥብ ውጤት ነገ ይፋ ይሆናል

አዲስ አበባ ፣ ነሃሴ 23 ፣ 2005 (ኤፍ ቢ ሲ) የ10ኛ ክፍል ማጠቃለያና የ12ኛ ክፍል መሰናዶ ማለፊያ ነጥብ ውጤትን ነገ ይፋ እንደሚያደርግ የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ። የዩኒቨርስቲ መግቢያና ወደ መሰናዶ ማለፊያ ነጥብን ለመወሰን  ፥ የዩኒቨርስቲዎችን ቀጣይ የመቀበል አቅም ከግምት ውስጥ በማስገባት መወሰኑንም ነው ሚኒስቴሩ የገለጸው። በአጠቃላይ 548 ሺህ 138 ተማሪዎች የ10 ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተናውን ወስደው 70 በመቶዎቹ 2 ነጥብ እና ካዛ በላይ ውጤት ሲያስመዘግቡ ፥ በተመሳሳይም የ12ኛ ክፍልን የዩኒቨርስቲ መግቢያ ፈተናን ከወሰዱት መካከል 70 በመቶ የሚሆኑት ተፈታኞች ከ350 ነጥብ በላይ ውጤት ማስመዝገባቸውን ቀደም ሲል  የሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና የፈተናዎች ኤጀንሲ አስታውሷል ። በነገው እለትም የሁለቱም ፈተናዎች የመቁረጫ ውጤት ይፋ ይደረጋል ተብሏል።