ዛሬ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ሁለት የጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች ይካሄዳሉ።
በ8 ሰዓት ላይ ሙገር ሲሚንቶ ከ አርባ ምንጭ ከነማ ሲገናኙ፥ ሲዳማ ቡና ከወልዲያ ከነማ 10 ሰዓት ላይ ይጫወታሉ።
ኢትዮጵያ ቡና ከመብራት ሃይል ከነገ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም የፕሪሚየር ሊግ ቀሪ ጨዋታውን ሲያካሂድ ፥ ወላይታ ዲቻ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ፣ ሀዋሳ ከነማ ከደደቢት አንድዚሁ ቀሪ ጨዋታቸውን የሚያደርጉ ይሆናል።
በሌላ በኩል 23ተኛው ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ ይቀጥላል።
የሊጉ መሪ ቼልሲ ከተከታዩ ማንችስተር ሲቲ ዛሬ ምሽት 1 ሰዓት ከ30 ላይ የሚያደርጉት ጨዋታ ተጠባቂ ነው።
ሊቨርፑል ከዌስት ሃም፣ ማንችስተር ዩናይትድ ከሌችስተር ሲቲ በተመሳሳይ 12 ሰዓት ነገ ይገናኛሉ።
ከነገ አርሰናል በኤሜሬትስ አስቶን ቪላን 10 ሰዓት ከ30 ላይ ያስተናግዳል።
Comments
Post a Comment