በምርት ዘመኑ የተገኘው አዲስ ቡና ወደ ውጭ እየተላከ እንዳልሆነ ቡና ላኪዎች ገለጹ፡፡ ስማቸውን መግለጽ ያልፈለጉ ሁለት የቡና ላኪዎች ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ ባለፉ ስድስት ወራት የተሸጠው ቡና ከአገር የወጣው በክረምት ወራት ነው፡፡ የሽያጭ ስምምነቱ ባለፈው ዓመት ቢደረግም በዚያው ዓመት መውጣት ባለመቻሉ፣ በዚህ ጊዜ መውጣት ያለበት አዲስ ቡና ግን መውጣት አልቻለም፡፡ ወቅቱ የታጠበ ቡና ወጥቶ አልቆ የደረቀ ቡና የሚላክበት ቢሆንም፣ በተለያዩ ምክንያቶች አፈጻጸሙ ዝቅተኛ መሆኑን ነጋዴዎች አመልክተዋል፡፡ ሽያጩ ሳይፈጸም የቀረው የተቀመጠው የቡና ዋጋ ሊወርድ ይችላል በሚል የቡና ገዥዎች ግብይት ለመፈጸም ባለመፈለጋቸው መሆኑን ሪፖርተር ያነጋገራቸው ነጋዴዎች ገልጸዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም አገር ውስጥ የሚገኙ ቡና አምራቾች የብራዚል ቡና በድርቅ በመመታቱ የዓለም የቡና ዋጋ ከፍ ሊል ስለሚችል፣ የሚያመርቱትን ቡና ለገበያ እያቀረቡ አይደለም በማለት አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡ ስማቸውን መግለጽ ያልፈለጉ አንድ የንግድ ሚኒስቴር የሥራ ኃላፊ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ አዲሱ ቡና በሚፈለገው ደረጃ መውጣት ያልቻለው ቡና ላኪዎቹ በገለጿቸው ሁለት ምክንያቶች እንደሆነ አረጋግጠዋል፡፡ የመጀመርያ የዓለም ገበያ ከፍተኛ የዋጋ መዋዠቅ ውስጥ በመሆኑ ነው፡፡ በዚህ ምክንያት ትላልቅ ገዥዎች ግዥ ከመፈጸም ተቆጥበዋል፡፡ በሁለተኛ ደረጃ የብራዚል ቡና በድርቅ በመመታቱና ብራዚል ምን ያህል ቡና ለገበያ እንደምታቀርብ በውል ባለመታወቁ፣ ገዥውም አቅራቢውም ወደ ቡና ግብይት ለመግባት ቁጥብ በመሆናቸው ነው ሲሉ አስረድተዋል፡፡ በሌላ በኩል ንግድ ሚኒስቴር ባለፉት ስድስት ወራት ከቡና ወጪ ንግድ ከዕቅዱ በላይ ማግኘቱን አስታውቋል፡፡ ሚኒስቴሩ ውጤቱ የተገኘው የከረመ ቡ
It's about Sidaama!