አዲስ አበባ ጥቅምት 20/2007 ዛምቢያ ፕሬዝዳንቷን በሞት ካጣች በኋላ የአገሪቱ ካቢኔ አዲስ ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት መሾሟን ዘ ኒዮርክ ታይምስ ዘገበ። የአገሪቱ ካቢኔ ትናንት ባደረገው አስቸኳይ ስብሰባ የአገሪቱ ምክትል ፕሬዝዳንት የነበሩትን ጌይ ስኮትን በጊዜያዊነት ሰይሟል። የእንግሊዙ ዜና ማሰራጫ ቢቢሲ የዛምቢያን መከላከያ ሚኒስትር ኢድጋር ሉንጉን እንደዘገበው ደግሞ የዘር ሃረጋቸው ከስኮትላንድ የሚመዘዙት ሚስተር ስኮት ዛምቢያ ከቅኝ አገዛዝ ነጻ ከወጣች በኋላ የአገሪቱ የመጀመሪያው ነጭ የአገር መሪ ያደርጋቸዋል። ጌይ ስኮት የፕሬዝዳንትነት ምርጫው በ90 ቀን ውስጥ እስከሚካሄድ ድረስ በተጠባባቂነት አገሪታን ይመራሉ። የ70 ዓመቱ አዛውንት ጌይ ስኮት ከዚህ ቀደም አርሶ አደር፣የግብርና ባለሙያና የምጣኔ ሃብት ባለሙያ ሆነው መሰራታቸውን የቢቢሲ ዘገባ አመልክቷል። በተጨማሪም ሚስተር ስኮት በተለያዩ ሃላፊነቶች፣ የሚኒስቴር ቦታዎችና እንደ አውሮፓዊያን አቆጣጠር ከ2011 እስከ 2014 በምክትል ፕሬዝዳንትነት አገልግለዋል። የሚስተር ስኮት እንደ አውሮፓዊያን አቆጣጠር በ1994 የደቡብ አፍሪካ መሪ የነበሩት ኤፍ ዴ ክለርክ ከስልጣን ከወረዱ በኃላ ከሳሃራ በታች የመጀመሪያው ነጭ መሪ ሆነው መመረጥ በአለም አቀፍ ብዙሃን መገናኛ ተቋማት አዎንታዊና አሉታዊና አስተያዬቶችን እየሰጡ ነው። ዛምቢያን ለ3 አመታት የመሩት የ77 አመቱ ሚካኤል ሳታ ከትናት በስቲያ በሞት መለየታቸው ይታወሳል። ምንጭ፦ ኢዜኣ
የለበሰው ያደፈ ቁምጣና ሹራብ ከቅዝቃዜው አላዳነውም፡፡ ካፊያው ልብሱን አርሶታል፡፡ ሽው እያለ ከሐይቁ የሚነሳው ነፋስ የሚፈጥረው ቅዝቃዜ ያንቀጠቅጠዋል፡፡ የተጫማው ያረጀ ሲሊፐር እግሩን ከምንም አላዳነውም፡፡ በባዶ እግሩ የሚራመድ ያህል ጨቅይቷል፡፡ ተደባዳቢ ይመስል ፊቱ የተሞነጫጨረ ነው፡፡ ገና 12 ዓመቱ ቢሆንም፣ ቁመናው እንደ ትልቅ ሰው ግዙፍ ነው፡፡ የሚለብሰውን እንደ ልቡ ባያገኝም፣ የሚያስፈልገውን ነገር ለማሟላት ቤሳቢስቲን የሌላቸው ወላጆቹን አያስቸግርም፡፡ ከቤተሰቦቹ ጋር ከሚኖሩበት ታቦር ተራራ ጀርባ ወዳለው ሐዋሳ ሐይቅ ከወረደ እንኳንስ የራሱን የቤተሰቦቹንም የዕለት ጉርስ የሚሸፍንበት ገንዘብ አያጣም፡፡ የአስጎብኚነት ዕውቀት፣ ከሐይቁም ውስጥ ዓሳ የሚያጠምድበት መረብም ሆነ ፈቃድ የለውም፡፡ ሙሉቀን (ስሙ ተቀይሯል) እና ጓደኞቹ ሐይቁን ለመጎብኘት የሚሄዱ ጎብኚዎች በካሜራቸው ጥሩ ፎቶ እንዲያስቀሩ ድባቡን የማሳመር ሥራ ይሠራሉ፡፡ ካሜራውን ይዞ ቁጭ ብድግ እያለ ጥሩ ፎቶ ለማንሳት ጥረት የሚያደርግ ሲያዩ፣ ቆርጠው የያዙትን የዓሳ ሥጋ ይዘው ጠጋ ጠጋ ይላሉ፡፡ ቁርጥራጩን የዓሳ ሥጋ ምግብ ለሚቀሙት አባኮዳዎች ሻሞ ይላሉ፡፡ የተወረወረላቸውን ቀድመው ለመቅለብ አባኮዳዎቹ ክንፋቸውን እየመቱ ወደ ላይ ብድግ ይላሉ፡፡ የናሽናል ጆግሪፊ የፎቶግራፍ ባለሙያዎች ያነሱት ዓይነት ፎቶዎች ሳያስቡት ያነሳሉ፡፡ በሁኔታው ተደስተው ደጋግመው ድንቅ ፎቶዎችን ለመውሰድ ሲዘጋጁ እነ ሙሉቀንም አጀንዳቸውን ይፋ ማድረግ ይጀምራሉ፡፡ አቶ ዳዊት አብርሃም ‹‹አንዱን ዓሳ በአሥር ብር ገዝቼ ነው እንዲህ የማዘጋጀው፤›› በማለት በቅድሚያ መረጃ ይሰጣሉ፡፡ ለቀጣዩ ዜና በዚህ መልኩ እንዲዘጋጁ ካደረጉ በኋላ፣ ሌሎች ሰዎች መቶም ሁለት መቶም ብር እንደሚሰጧቸው ቀለል