በየ3 አመቱ የደሞዝ ጭማሪ ሊደረግ ይችላል ከመጪው ሐምሌ ወር ጀምሮ ለመንግስት ሠራተኞች እንደሚጨመር የተነገረው የደሞዝ መጠን እስካሁን በይፋ አልተገለፀም፡፡ በሌላ በኩል ከአሁን በኋላ በየሦስት አመቱ ለመንግስት ሠራተኞች የደሞዝ ጭማሪ ሊደረግ እንደሚችል ምንጮች ጠቁመዋል፡፡ በሲቪል ሠርቪስ ሚኒስቴር የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ጌታቸው አብዲሣ፤ በቅርቡ መንግስት ይጨመራል ብሎ ከሰጠው መረጃ ውጪ በምን ያህል ፐርሰንት እንደሚጨመር መረጃ አልደረሰንም ብለዋል፡፡ ለመንግስት ሠራተኞች ለመጨረሻ ጊዜ ደሞዝ የተጨመረው በታህሳስ ወር 2003 ዓ.ም ሲሆን በወቅቱ ከ38.75 በመቶ እስከ 44.71 በመቶ የሚደርስ ጭማሪ መደረጉ የሚታወስ ሲሆን አሁን ከዚያ በላይ የደሞዝ ጭማሪ እንደሚጠበቅ በግል ዩኒቨርሲቲ የኢኮኖሚክስ መምህር አቶ መስፍን ይልማ ግምታቸውን ሰንዝረዋል። የደሞዝ ጭማሪው በተለይ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው የመንግስት ደሞዝተኞችን ተጠቃሚ ማድረግ እንዳለበት ተናግረዋል - ምሁሩ፡፡ የደሞዝ ጭማሪ ስሌቱ አለመታወቁ ትንታኔዎችን ለመስጠት ያስቸግራል ያሉት መምህሩ፤ እስከዛሬ በመንግስት በኩል የሚደረጉ የደሞዝ ጭማሪዎች የሠራተኛውን ፍላጐት አርክተው አያውቁም፤ ይኸኛውም ጭማሪ የተለየ ነገር ይዞ አይመጣም ብለዋል፡፡ ባለፉት አምስት ዓመታት በፓርላማ ብቸኛ የተቃዋሚ ፓርቲ ተወካይ የሆኑት የተከበሩ አቶ ግርማ ሰይፉ በበኩላቸው፤ የደሞዝ ጭማሪው አስፈላጊና ወቅታዊ መሆኑን ጠቅሰው፤ ጭማሪው አንዲት ሣንቲም እንኳ ቢሆን በሠራተኛው ህይወት ላይ ለውጥ ባያመጣም ትርጉም አለው ይላሉ፡፡ መንግስት መቼውንም ቢሆን የሠራተኛውን ፍላጐት ሊያሟላ የሚችል ደሞዝ የመጨመር አቅም አይኖረውም ያሉት የፓርላማ አባሉ፤ አንድ የመንግስት ሰራተኛ የሚመራው ኑሮ ሊስትሮ ከሚሰራ ሰው
It's about Sidaama!