- ለኤክስፖርት የተዘጋጀ ቡና ላይ የኮንትሮባንድ ንግድ ደርቷል በቡና ንግድ ተሳታፊ ሳይሆኑ የቡና ፈቃድ አውጥተው ለዓመታት የተቀመጡና ምናልባትም አጭበርባሪዎች ሊሆኑ ይችላሉ የተባሉ 37 ግለሰቦችን ፈቃድ መሰረዙን የንግድ ሚኒስትሩ አስታወቁ፡፡ የንግድ ሚኒስትሩ አቶ ከበደ ጫኔ የአሥር ወራት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርታቸውን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባለፈው ሳምንት ሲያቀርቡ፣ የቡና ንግድ መቀዝቀዙንና ኮንትሮባንድ መስፋፋቱን፣ እንዲሁም ከቡና ጋር የተያያዙ ችግሮችን ለመፍታት የንግድ ሚኒስቴር ምን እያደረገ እንደሆነ ተጠይቀዋል፡፡ የቡና ጉዳይ ድሮ በሚኒስቴር ደረጃ ይመራ ከነበረበት ወርዶ በአንድ ተቋም ውስጥ መመሸቁ እንደሚያሳስባቸው የተናገሩት ሚኒስትሩ፣ ከኮንትሮባንድ መስፋፋት በተጨማሪ የቡና ንግድ ሳይኖራቸው የቡና ፈቃድ ያወጡ መኖራቸውን አስረድተዋል፡፡ በቡና ንግድ ካልተሰማሩ ፈቃዱን ለምን እንደሚፈልጉት መገመት እንደሚቻል የተናገሩት ሚኒስትሩ፣ ዋነኛው መንግሥት ለቡና ንግድ የሚሰጠውን ትኩረትና ጥቅማ ጥቅም ለመቀራመት ሊሆን እንደሚችል ገልጸዋል፡፡ በቡና ንግድ ዘርፍ ለሚሰማሩ መንግሥት ቅድሚያ የባንክ ብድርና የውጭ ምንዛሪ እንዲያገኙ ስለሚያደረግ፣ እነዚህ በቡና ንግድ ላይ ለመሰማራት ፈቃድ ያወጡ ነገር ግን ኤክስፖርት አድርገው የማያውቁ ነጋዴዎች ይህንን ጥቅም ለመመዝበር አቅደው ሊሆን ይችላል ብለዋል፡፡ ‹‹እንዲህ ዓይነት የማጭበርበር ሥራ የሚሠሩ የቡና ንግድ ፈቃድ ይዘው የተቀመጡ ነጋዴዎች ፈቃድ ተሰርዟል፤›› ብለዋል፡፡ እነዚህ ነጋዴዎች የሚያገኙትን ብድር ተጠቅመው አራጣ የማበደር ተግባር ውስጥ ተሰማርተው ሊሆኑ ይችላል የሚሉት አቶ ከበደ፣ የነጋዴዎቹን ማንነት ከመግለጽና ፈቃዳቸውን ከመሰረዝ ባለፈ የሚወሰድ ዕርምጃ ስለመኖሩ አልተናገሩ
It's about Sidaama!