አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 22፣ 2006 ( ኤፍ.ቢ.ሲ ) የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በተለያዩ ጨዋታዎች በዛሬው እለት ቀጥሏል። በአዲስ አበባ ስታዲየም በተደረጉ ጨዋታዎች ፥ የሊጉ መሪ ቅዱስ ጊዮርጊስ አስራ አንደኛ ደረጃ ላይ ከሚገኘው ከመብራት ሀይል በ9 ሰዓት ተገናኝቶ 3 ለ 2 በሆነ ውጤት ረቷል። በተመሳሳይ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከሲዳማ ቡና 11 ከ 30 ላይ ተገናኝተው ፥ ጨዋታው በሲዳማ ቡና 2 ለ 1 አሸናፊነት ተጠናቋል። ። በክልል ጨዋታዎች በደቡብ ደርቢ ሀዋሳ ከነማ አርባ ምንጭ ከነማን ፣ ቦዲቲ ላይ ወላይታ ዲቻ ኢትዮጵያ ቡናን በተመሳሳይ 1 ለ 0 በሆነ ውጤት መርታት ችለዋል። ደደቢት በበኩሉ በአበበ በቂላ ስታዲየም በወራጅ ቀጠና ላይ የሚገኘውን ሀረር ከተማን በ10 ሰዓት አስተናግዶ 1 ለ 1 ተለያይቷል።
It's about Sidaama!