ሀዋሳ የካቲት 20/2006 ትምህርት ቤቶች የነገዎቹን ተመራማሪዎች፣ ሳይንቲስቶችና የልማት አርበኞች ማፍሪያ ስፍራዎች መሆናቸውን በተግባር እያሳዩ እንደሚገኙ የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ገለጹ፡፡ ሁለተኛ ዙር የሃዋሰ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቤቶች የሳይንስና ፈጠራ ስራዎች አውደ ረኢ " ትምህርት ቤቶች የፈጠራ ማዕከላት ይሆናሉ " በሚል መሪ ቃል ትናንት በሃዋሳ ከተማ ተከፍቷል፡፡ መንግስት ለሳይንስና ሂሳብ ትምህርቶች የሰጠው ትኩረት የፈጠራ ስራን ለማሳደግ ከፍተኛ እገዛ እያደረገ መሆኑን የአውደ ረኢው ተሳታፊና የፈጠራ ባለቤት የሆኑ ተማሪዎች ገልፀዋል፡፡ የከተማው አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ቴዎድሮስ ገቢባ በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት አስተዳደሩ ለትምህርት ልማት በሰጠው ልዩ ትኩረት አገልግሎቱን ለሁሉም ዜጎች በፍትሃዊነት ከማዳረስ አኳያ ከፍተኛ ውጤት ተመዝግቧል፡፡ በዚህም በከተማው የሚገኙ ትምህርት ቤቶች ከልማዳዊ አሰራር ተላቀው በተደራጀ መንገድ ሁሉንም ባለድርሻ አካላት በተልዕኮ ዙሪያ በማሰለፍ የተማሪ ውጤትን ለመቀየር በሚያስችል የውድድር ሂደት ውስጥ ተገብቷል፡፡ በአሁኑ ጊዜ በከተማው ትምህርት ቤቶች የሚታዩት ሰፋፊ የፈጠራ ስራዎች የትምህርት ፖሊሲውና ፓኬጅ ትግበራ ውጤቶች መሆናቸውን ጠቁመው እነዚህ አበረታች ውጤቶች አጠናክሮ ለማስቀጠል የሁሉም ባለድርሻ አካላት ጥረት ይጠይቃል ብለዋል፡፡ በተማሪዎች እየተሰሩና ለህብረተሰቡ በአነስተኛ ዋጋ በጥራት የሚቀርቡ የፈጠራ ስራ ውጤቶች ሀገራችን በሳይንስና ቴክኖሎጂ ለመድረስ ያስቀመጠችውን ግብ ማሳካት እንደሚትችል በተግባር እያሳየ በመሆኑ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል፡፡ የከተማው አስተዳደር ትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ታዬ ቢሊሶ በበኩላቸው በከተማ
It's about Sidaama!