Skip to main content

Posts

Showing posts from January, 2014

ካላ ጆን (ዮሐንስ) እና ባለቤታቸው ኣሬኔ ሃመር በሲዳማ ላይ ከጻፏቸው ምርምሮች መካከል ኣንዱ የሆነውን በሲዳማ ባህላዊ ኣምልኮ እና እምነት ላይ የተሰራ ስራ

በሲዳማ ብሄር ላይ የተለያየ ጥናት ካደረጉት የውጭ ተመራማሪዎች መካከል የሆኑት እና '' የሲዳማ ህዝብ እና ባህሉ ''በምል ርዕስ ካላ ቤታና ሆጤሳ  ባሳተሙት መጽሃፍ ውስጥ ስማቸው በተደጋጋሚ በመጠቀሱ የተነሳ መላው የመጽሃፉ ኣንባቢያ  የምታውቃቸው ካላ ጆን (ዮሐንስ) እና ባለቤታቸው ኣሬኔ ሃመር በሲዳማ ላይ ከጻፏቸው ምርምሮች መካከል ኣንዱ የሆነውን በሲዳማ ባህላዊ ኣምልኮ እና እምነት ላይ የተሰራ ስራ ከታች ያንቡ፦ ለተጨማር ንባብ ፦   http://www.jstor.org/discover/10.2307/3772719?uid=2&uid=4&sid=21103366544957   

ካለእድሜ ጋብቻ ጋር በተያያዘ ለኦብቴትሪክ ፊስቱላ ህመም የተጋለጡትን በርካታ የሲዳማ ታዳጊ እናቶች በማከም ብሎም የፊስቱላ ህክምና ኣገልግሎት በይርጋዓለም ሆስቲፓል እንዲጀመር በማድረግ ለሲዳማ ሴቶች ትልቅ ውለታ ስለዋሉት ዶር ካትሄሪን ሃምሊን ምን ያውቃሉ

Australian surgeon Catherine Hamlin has just celebrated her 90th birthday, and for most people, this would be a good enough reason to slow down.   ካለእድሜ ጋብቻ ጋር በተያያዘ ለኦብቴትሪክ ፊስቱላ ህመም የተጋለጡትን በርካታ የሲዳማ ታዳጊ እናቶች በማከም ብሎም የፊስቱላ ህክምና ኣገልግሎት በይርጋዓለም ሆስቲፓል እንዲጀመር በማድረግ ለሲዳማ ሴቶች ትልቅ ውለታ የዋሉት ዶር ካትሄሪን ሃምሊን እንኳን ለ90 ኛ ኣመት የልደት በዓሏ ኣደረሷት፤ ወራንቻ ኢንፎርሜሽን ኔትዎርክ   90 year old surgeon keeps a steady hand in Ethiopia By   Naomi Selveratnam   Source   World News Australia Radio  U PDATED YESTERDAY 8:08 PM Australian surgeon Catherine Hamlin has just celebrated her 90th birthday, and for most people, this would be a good enough reason to slow down. (Transcript from World News Australia Radio) But Dr Hamlin says she will continue her work with women in Ethiopia with the potentially life-threatening medical condition, obstetric fistula. (Click on audio tab above to hear full item) When Catherine Hamlin celebrated her 90th birthday, she didn't want gifts or a party.

ለሞጆ - ሀዋሳ ፈጣን መንገድ ግንባታ የጨረታ ሂደት ተጀመረ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 21 ፣2006 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሰልጣን  ከሞጆ -መቂ እና ከአርበር ረከቴ -ገለምሶ ያለውን የ113 ኪሎ ሜትር የአስፋልት መንገድ ግንባታ ለመጀመር የሚያስችለውን የጨረታ ሂደት ጀመረ። የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ከሞጆ- ሀዋሳ ያለውን የፈጣን መንገድ ግንባታን በአራት ተቋራጮች ከፋፍሎ ለማሰራት አቅዷል። ከሞጆ  እስከ መቂ፣ ከመቂ እስከ ዝዋይ ፣ ከዝዋይ እስከ አርሲነገሌ እና ከአርሲነገሌ   እስከ ሃዋሳ  ተብሎም መንገዱ ተከፋፍሏል። ለነዚህ የመንገድ ፕሮጀክቶች የኢትዮጵያ መንግስት አራት ከሚሆኑ አለም አቀፍ አበዳሪ  ድርጅቶች በብድር ያገኘውን ከ173 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር በላይ በጀት ትናንት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አጽድቆታል። በኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን የኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሳምሶን ወንድሙ እንደሚሉት፥ ከነዚህ አራት የመንገድ ፕሮጀክቶች በቀዳሚነት ወደ ግንባታ ሂደት የሚገባው ከሞጆ- መቂ ያለው ነው። 56 ኪሎ ሜትር ርዝመት ላለው ለዚህ መንገድ የኢትዮጵያ መንግስት ከአፍሪካ ልማት ፈንድ ያገኘው ከ126 ሚሊየን የአሜርካን ዶላር በላይ የገንዘብ ብድር ትናንት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተቀብሎ አጽድቆታል። የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን የገንዘብ ብድሩ ከአበዳሪው መገኘቱን እንዳረጋገጠ፥ እስከሚጸድቅ ሳይጠብቅ ወደ ጨረታ ሂደት መገባቱን ነው አቶ ሳምሶን የተናገሩት። ከመቂ - ሃዋሳ ያለውን መንገድ ለመገንባት የአለም ባንክ፣ የኮርያ መንግስትና የቻይና  ኤግዚም ባንክን  የመሳሰሉ  አበዳሪዎች ለፕሮጀክቱ ማስፈጸሚያ የሚሆን ገንዘብ ለመስጠት ይሁንታቸውን አሳይተዋል ብለዋል። የሞጆ ­- ሃዋሳ የመንገድ ግንባታ ከነባሩ ሙሉ በሙሉ ሳይገናኝ ራሱን ችሎ የሚሰራ መሆኑንም ተናግረዋ

በሃዋሳ ከተማ ሰሞኑን የትራንስፖርት ኣገልግሎት እጥረት ተከሰቷል፤ ችግሩ የተፈጠረው በቤንዚን ኣቅርቦት እጥረት ነው ተብሏል

በከተማዋ እና በኣከባቢያዋ የትራንስፖርት ኣገልግሎት የምሰጡት በሺዎች የምቆጠሩት ባለሶስት ጎማ ተሽከርካሪዎች ሰሞኑን እንደተለመደው የትራንስፖርት ኣገልግሎት በመስጠት ላይ ኣይደሉም። የሃዋሳ ከተማዋ ነዋሪዎች ለወራንቻ ኢንፎርሜሽን ኔትዎርክ እንደተናገሩት፤   ኣገልግሎት በመስጠት ላይ ያሉትም የባዳጂ ታክሲዎች ቁጥር ጥቂት በመሆኑ የከተማዋ ነዋሪዎች የእለትተእለት ስራቸውን ተንቀሳቅሰው ለማከናዎን መቸገራቸውን ኣመልክተዋል። በጉዳዩ ዙሪያ ወራንቻ ኢንፎርሜሽን ኔትዎርክ ያናገራቸው የባዳጂ ኣሽከርካሪዎች እንዳስረዱት፤ ለሃዋሳ ከተማ እና ለኣካባቢዋ ነዳጅ የማከፋፈል ኣገልግሎት በመስጠት ላይ ከምገኙት ከኣስር በላይ የነዳጅ ማዴያዎች መካከል ኣብዛኛዎቹ ቤንዚን ኣይሸጡም። በኣጠቃላይ ከተማዋ ከሁለት የማይበልጡ ብቻ ቤንዚን በማደል ላይ ሲሆኑ፤ በእነዚህም ነዳጅ ማደያዎች የቤንዚህ ኣገልግሎት ፈላጊው እና ኣቅርቦቱ የተመጣጠነ ባለመሆኑ በርካታ ኣሽከርካሪዎች በረዥም ሰልፈ ጊዜያቸውን በማቃጠል ላይ በመሆናቸውን ተናግረዋል። የነዳጅ ማደያዎቹ ሰራተኞች በበኩላቸው እንደምሉት ከሆነ፤ ቤንዚን የማደል ኣገልግሎት የማይሰጡት የቤንዚን እጥረት በመፈጠሩ ነው። ነገር ግን ኣንዳንድ የከተማዋ ነዋሪዎች በሰጡት ኣስተያየት በኣገሪቱ ውስጥ የነዳጅ እጥረት እንደሌለ እየታወቀ ሳለ በሃዋሳ ከተማ ብቻ የነዳጅ እጥረት መከሰቱ ጉዳዩን በጥርጣሬ እንድመለከቱ እንዳደረጋቸው ጠቁመው፤ የምመለከተው የመንግስት ኣካል መፍትሄ እንድፈልግ ጥሪ ኣቅርበዋል። 

Ethiopia's renewable energy revolution shouldn't fail to empower its poor

Large-scale clean energy projects shouldn't eclipse the urgent need to provide electricity to low-income and rural communities Will Ethiopia's renewable energy project light up poor communities? Photograph: Rebecca Blackwell/AP The 84 wind turbines erected just south of Addis Ababa,  Ethiopia 's capital, tower above an arid landscape of grassland and unpaved roads, inhabited mostly by small-scale farmers, who – along with 77% of population –  lack access to electricity . The Ashegoda wind farm, launched in November, will produce an estimated 400 GWh of electricity per year, and forms just one piece of the Ethiopian government's strategy to harness indigenous  energy resources for development. When – and to what extent – the country's rural population will benefit depends on striking a balance between investing in new grid-connected generation and effective strategies for expanding access. Ethiopia today stands at a crossroads. In 2012, it had the world&#

Ethiopia - Land for Sale

As the economy thrives, we examine the plight of Ethiopians forced from their land to make way for foreign investors. Just a few decades ago, Ethiopia was a country defined by its famines, particularly between 1983-1985 when in excess of half a million people starved to death as a consequence of drought, crop failure and a brutal civil war. Against this backdrop, it is impressive that in recent years, Ethiopia has been experiencing stellar economic growth. The headline statistics are certainly remarkable: the country is creating millionaires faster than any other in Africa; output from farming, Ethiopia’s dominant industry, has tripled in a decade; the capital Addis Ababa is experiencing a massive construction boom; and the last six years have seen the nation’s GDP grow by a staggering 108 percent. But it is not all positive news, because for all the good figures there are still plenty of bad ones. Around 90 percent of the population of 87 million still suffers from nume

የኢኮኖሚ ዕድገቱ ባለ አንድ አሃዝ ሆኖ እንደሚቀጥል የተመድ ሪፖርት ይፋ አደረገ

ሪፖርተር ያቀናበረው ይህ የሥዕል መግለጫ፣ የላይኛው መስመር በያመቱ የተመዘገበውን የኢኮኖሚ ዕድገት የሚወክል ሲሆን የታችኛው መስመር ደግሞ ዓመቱን እ.ኤ.አ. ይጠቁማል) - የዋጋ ግሽበት እያንሰራራ ወደ ሁለት አሃዝ ማምራቱ ይጠበቃል የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ከጥቂት ቀናት በፊት ይፋ ያደረገው፣ የዓለም ኢኮኖሚ ሁኔታና መጪውን ጊዜ የተነበየበት የዘንደሮው ሪፖርት፣ (World Economic Growth Situation and Prospects) የዓለምን ኢኮኖሚ ዕድገት በየቀጣናው ተንትኗል፡፡  በዚህ ሪፖርት መሠረት ኢትዮጵያ ምንም እንኳ የኢኮኖሚዋ ዕድገት ትልልቅ ከሚባለው ጎራ ቢሰለፍም፣ በመንግሥት የታቀደውን መጠን ሆኖ አልተገኘም፡፡ የኢኮኖሚ ዕድገቱ በአንድ አሃዝ ተወስኖ፣ ከስድስት ዓመት በፊት ከነበረበት የ12 ከመቶ ዕድገት በግማሽ ያህል እየወረደ መምጠቱንና በዚሁ መጠን እንደሚቀጥልም ትንበያው ይጠቁማል፡፡ በመጪዎቹ ሁለት ዓመታት ውስጥ ከ6.4 ከመቶ ያልበለጠ ዕድገት እንደሚኖርም ይጠበቃል፡፡ በአንጻሩ የዋጋ ግሽበትም (ምርትና አገልግሎቶች በአጠቃላይ የሚያሳዩት የዋጋ ጭማሪ) እያንሠራራ እንደሚቀጥልና ወደ ሁለት አሃዝ እንደሚጠጋ ተመድ ይፋ አድርጓል፡፡  መንግሥት በዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅዱ መሠረት የሚጠብቀው የአገሪቱ ዓመታዊ የኢኮኖሚ ዕድገት (ከጠቅላላ የአገር ውስጥ ምርት አኳያ- ጂዲፒ) በዝቅተኛው ዕርከን 11 ከመቶ፣ በከፍተኛው የዕድገት ጣሪያ ደግሞ 14 ከመቶን እየረገጠ እንደሚጓዝ ነበር፡፡ ሆኖም ከመንግሥት በወጣው መረጃ እንኳ ከታየ፣ የአገሪቱ ኢኮኖሚ ከታሰበው በታች በስምንት ከመቶ ክልል ውስጥ እያደገ ይገኛል፡፡  ካስቀመጠው ውጥን በታች ዕድገቱ መጓዙ ያሳሰበው መንግሥት፣ በተለያዩ ጊዜያት ባስተላለፋቸው መግለጫዎቹም ካሰበ

የሕፃናት ሽያጭና ወሲብ ቀስቃሽ ፊልሞችን ለመከላከል የወጣው ኮንቬንሽን ፀደቀ

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሕፃናት ሽያጭን፣ የሕፃናት የወሲብ ንግድና የሕፃናትን የወሲብ ቀስቃሽ ፊልሞችን ለመከላከል የወጣው ኮንቬንሽንን ማክሰኞ ዕለት አፀደቀ፡፡  የሕፃናት ሽያጭን፣ የሕፃናት የወሲብ ንግድና ወሲብ ቀስቃሽ ፊልሞች በማሳተፍ የሚፈጸሙ ወንጀሎች በዓለም አቀፍም ሆነ አገር አቀፍ ደረጃ አሳሳቢ እየሆኑ በመምጣታቸው፣ ኮንቬንሽኑን በማፅደቅ የሕፃናትና መብት ማስከበር ተገቢ ነው ተብሏል፡፡ አዋጁ እንዲፀድቅ የፓርላማው የሴቶች፣ የሕፃናትና የወጣቶች ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ያቀረበውን የውሳኔ ሐሳብ ፓርላማው ተቀብሎታል፡፡ የተጠቀሰውን ወንጀል ለመከላከልና የሕፃናትን መብት ለማስከበር ኢትዮጵያ ብቻዋን መንቀሳቀሷ ውጤታማ እንደማያደርጋት፣ ነገር ግን ኮንቬንሽኑን በማፅደቅ ከሌሎች አገሮች ጋር ተባብሮ በአጋርነት ወንጀሉን መከላከል እንደሚያስችላት ተገልጿል፡፡ በተመሳሳይም ሕፃናትን በጦርነት ማሳተፍን በሚመለከት የወጣውን የሕፃናት መብቶች ኮንቬንሽን ተጨማሪ ፕሮቶኮል ፓርላማው በማክሰኞ ውሎው አፅድቆታል፡፡  ም ንጭ፦ http://www.ethiopianreporter.com

በሲዳማ ዞን ባለፉት ስድስት ወራት ከ196 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ተሰበሰበ

አዋሳጥር 21/2006 በሲዳማ ዞን ባለፉት ስድስት ወራት  ከተለያዩ ምንጮች ከ196 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን የዞኑ  ገቢዎች ባለስልጣን ዋና ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡  የተሰበሰበው ገቢ ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር ከ15 በመቶ በላይ እድገት ማሳየቱም ተገልጿል፡፡  የጽህፈት ቤቱ  የዕቅድ ክትትልና ግብረ መልስ የስራ ሂደት ኦፊሰር አቶ አክሊሉ እንጀቶ ዛሬ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት ገቢው የተሰበሰበው  ከመደበኛና የማዘጋጃ ቤቶች አገልግሎትን ጨምሮ ቀጥታና ቀጥታ ካልሆነ የታክስ ግብር እንዲሁም ታክስ ካልሆኑ ገቢዎች ነው፡፡  የተሰበሰበው ገቢ ከአምና ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር ከ15 በመቶ በላይ እድገት ማሳየቱን አስረድተዋል፡፡  በዞኑ ኢኮኖሚው የሚያመነጨውን የገቢ ግብር አሟጦ በመጠቀም በበጀት ዓመቱ የተያዘውን እቅድ ለማሳካት  ሌሎች ዝግጅቶችን ጨምሮ የቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቱን የማስፈጸም አቅም ለማጠናከር እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡  ዞኑ ባለፈው የበጀት ዓመትም ከተለያዩ የገቢ ርዕሶች ከ296 ሚሊዮን  ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡ ጠቁመው የዞኑን አጠቃላይ ወጪ በሚገኘው ገቢ ለመሸፈን የተቀናጀ ጥረት በመደረግ ላይ መሆኑን አመልክተዋል፡፡  በዞኑ 15ሺህ 146 ግብር ከፋዮችና 1 ሺህ 535 የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢዎች  እንዳሉም ገልፀዋል፡፡  በተያዘው የበጀት ዓመትም 290 ተጨማሪ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢዎችን ለመመዝገብ ታቅዶ እስከአሁን 71 መመዝገቡን ገልፀዋል፡፡ ምንጭ፦ ኢቲቪ እኣኣ 1/29/2014

Ethiopian Lawmakers Enact Anti-Tobacco Law

The Ethiopian House of Representatives has reportedly ratified the World Health Authority’s Framework Convention on Tobacco Control (FCTC), which places limitations on the sale and use of cigarettes. Besides a ban on smoking in public, the proclamation also includes plans of increasing taxes on cigarette and initiating public campaigns against the hazards of smoking. Campaigns against smoking cigarettes have been gaining ground in sub-Saharan African countries in the past few years. According to experts, given that the market for cigarettes in the western world is well defined, the search for more consumers is quickly spreading to Africa and Asia, where lack of education, poverty and weak legislation makes it relatively easy for tobacco companies to make huge profits. In December 2013, when the draft bill was initially brought before the house, Ethiopian lawmakers expressed disappointment that the country had stalled in ratifying the convention. Like many other African na

Foot Power: York County runners share marathon experience in Ethiopia

By M.C. Besecker To say Clay Shaw is a living legend in the York County racing scene is not a stretch of the imagination at all. Just take a quick look at the facts. Shaw was an inaugural member of the York Road Runners' Club. He directed various races in the area for years, often drawing elite athletes from all along the East Coast. He has run 182 marathons in 22 different countries. Shaw is also a local trendsetter. He has run a marathon in all 50 states, and now several local runners are attempting to duplicate that feat. Not to be outdone, Shaw decided to do it again, embarking on a second tour of our country. He has only two states left to wrap up that second tour: Kansas, which he plans to do in March, and Alaska, later this summer. Shaw might have started this adventure alone, but he has had a partner in crime to keep him company on his many excursions for many years. Wife Karen Mitchell has run 105 marathons, and typically follows Shaw wherever he goes. The mo

የጉቦ ነገር በኢትዮጵያ

መንግሥት በሚፈጽማቸው ግዢዎች የውጭ ኢንቨስተሮች ጉቦ እንጠየቃለን አሉ በኢትዮጵያ ኢንቨስት በማድረግ ላይ የሚገኙ የውጭ ኩባንያዎች በሙስና ላይ ስላላቸው አመለካከት ለማወቅ በተደረገ ረቂቅ ጥናት፣ የኢትዮጵያ መንግሥት በሚፈጽማቸው ግዥዎች እስከ 80 በመቶ ጉቦ እንደሚጠየቁ ተመለከተ፡፡  ይህ አስደንጋጭ ነው ሲሉ ረቂቅ ጥናቱን ያካሄደው ሰላም ዴቨሎፕመንት አማካሪ ድርጅት ሥራ አስኪያጅ አቶ አመነ ዲያነ ገልጸዋል፡፡ አቶ አመነ እንደሚሉት፣ ለጥናቱ ከተጠየቁት 350 ኢንቨስተሮች መካከል አንድ መቶ ብር ለሚያወጣ ግዥ 80 በመቶውን ጉቦ የሚጠይቁ አሉ፡፡ እንደዚህ ዓይነት ምላሽ የሰጡት ግን ውስን ቁጥር ያላቸው ቢሆንም ሁኔታው አስደንጋጭ ነው ብለዋል፡፡  ባለፈው ሐሙስ በፀረ ሙስና ኮሚሽን ባለቤትነት ሰላም ዴቨሎፕመንት አማካሪ ድርጅት ባካሄደው ጥናት ላይ ውይይት ተካሂዷል፡፡ በሒልተን ሆቴል በተካሄደው በዚህ ውይይት ለተካሄደው ጥናት ሐሳባቸውን እንዲገልጹ የተጠየቁት ኢንቨስተሮች ከ42 አገሮች የተወከሉ ናቸው፡፡ እነዚህ ኢቨስተሮች እንደሚሉት ጉዳያቸውን ለማስፈጸም ወደ መንግሥት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት በሚሄዱበት ወቅት ጉቦ ይጠየቃሉ፡፡  ከዚህ በተጨማሪም የመረጃ ማረጋገጫ ለማግኘትና ፈቃድ ለማውጣት የሚወስደው ጊዜ መሻሻል ቢታይበትም፣ አሁንም መስተካከል እንደሚቀረው አመልክተዋል፡፡  በተካሄደው ውይይት ላይ በጥናቱ ጐልተው ከታዩት ውስጥ አነስተኛ ሙስና ገዝፎ ታይቷል፡፡ ነገር ግን ትላልቅ የሙስና ድርጊቶች በሰፊው የሚነገርላቸው በመሆናቸው ሊጤን እንደሚገባው ተመልክቷል፡፡  በጥናቱ ሕግና መመርያ፣ የቢሮክራሲ ማነቆዎችና ቢዝነስ ለመሥራት ያለው ቅለትና የሙስና ችግሮች አጽንኦት ተሰጥቷቸው ቀርበዋል፡፡  በሦስቱም መስኮች ችግር መኖሩ በረቂቅ ጥ

የጥራት ደረጃ ያጭበረበሩ ሁለት ቡና ላኪዎች በሕግ ሊጠየቁ ነው

- ሌሎች ስድስት ላኪዎች በማስጠንቀቂያ ታልፈዋል -ራሱን የቻለ የመጋዘን አገልግሎት ኢንተርፕራይዝ ሊቋቋም ነው ለውጭ ገበያ የሚቀርብ የቡና ምርት የጥራት ደረጃ በማጭበርበር የወደቀ የጥራት ደረጃ ያለው የቡና ምርት ከአገር ለማስወጣት የሞከሩ ሁለት ቡና ላኪዎች በሕግ እንዲጠቁ መወሰኑን የንግድ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ የሚኒስቴሩ የውጭ ንግድ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ያዕቆብ ያላ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለመንግሥት የወጪ አስተዳደር ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ነው በቡና ላኪዎቹ ላይ ስለተወሰነው ዕርምጃ ያሳወቁት፡፡ በንግድ ሚኒስቴር ቀጥተኛ ክትትል የሚደረግባቸው የግብርና ምርቶች የውጭ ንግድ ማስፋፊያ ሥርዓት አፈጻጸምና ውጤታማነት ላይ በ2004 ዓ.ም. በኦዲት የታየ ችግር በመኖሩ፣ ቋሚ ኮሚቴው ችግሩ በምን ዓይነት መንገድ እየተቀረፈ መሆኑን ለማወቅ ነው ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱን የጠራው፡፡ በ2004 ዓ.ም. ታዩ ከተባሉት ችግሮች መካከል ለውጭ ገበያ የሚቀርቡ የግብርና ምርቶች የጥራት ደረጃ ጉድለት አገሪቱን በእጅጉ እየጐዳ መሆኑን፣ ወደ ውጭ ገበያ ለማቅረብ ከኢትዮጵያ ምርት ገበያ የሚገዙ የግብርና ምርቶች የኪሎ ጉድለት እንደሚታይባቸው፣ ግዥውን የፈጸሙ ላኪዎች የገዙትን የግብርና ምርት በጥራት ደረጃው እንደማያገኙት፣ ወደ ውጭ እንዲላክ የተዘጋጀ ቡና ዋጋ ውጭ አገር ተሽጦ ከሚገኘው ገቢ የሚንር መሆኑ በ2004 ዓ.ም. በዋና ኦዲተር ጄኔራል የተደረገው የክዋኔ ኦዲት ያስረዳል፡፡ ችግሩን በምን ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ባለፈው ረቡዕ በፓርላማው ቋሚ ኮሚቴ የተጠየቁት ሚኒስትር ዴኤታው አቶ ያዕቆብ፣ አብዛኞቹ ችግሮች መለየት መቻላቸውንና መቀረፋቸውን ገልጸዋል፡፡ ይሁን እንጂ አሁንም ጥቂት የሚባሉ ነገር ግን ተፅዕኖ ፈጣሪ የሆኑ ቡና ላኪዎች የቡና

በሲዳማ ዞን ለባለሃብቶች የኢንቨስትመንት ፈቃድ ተሰጠ

ሐዋሳ ጥር 20/2006 በሲዳማ ዞን ባለፉት ሶስት ወራት ከ24 ሚሊዮን ብር የሚበልጥ የኢንቨስትመንት ካፒታል ላስመዘገቡ 12 ባለሃብቶች ፈቃድ መሰጠቱን የዞኑ ንግድና ኢንዱስትሪ መምሪያ ገለጸ፡፡  በመምሪያው የኢንቨስትመንት ማስፋፋፊያ የስራ ሂደት አስተባባሪ አቶ ብርሃኑ ወልደሚካኤል ትናንት ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት ባለሃብቶቹ ከተሰማሩባቸው የስራ መስኮች መካከል አገልግሎት መስጫ ተቋማት፣ግብርናና ኢንዱስትሪ ይገኙበታል፡፡  ባለሃብቶቹ ለ279 ቋሚና 788 ዜጎች ጊዜያዊ የስራ እድል ማግኘታቸውን ገልፀው ባለፈው ዓመት በተጀመረ የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴም ከሁለት ሺህ ለሚበልጡ ዜጎች የስራ እድል መፈጠሩን ተናግረዋል፡፡  መምሪያው ለ41 ባለሃብቶች የፍቃድ እድሳትና ተጨማሪ የማስፋፊያ ፈቃድ መሰጠቱን ጠቁመው ቦታ ወስደው ወደ ስራ ያልገቡ ባለሃብቶችን ድጋፍ  በመስጠት ወደ ስራ የሚገቡበትን ሂደት ለማመቻቸት ባደረገው ጥረት 320 ፕሮጀክቶች የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ሆነዋል፡፡  አዲስ ፈቃድ ወስደው ወደ ስራ ከገቡ ባለሃብቶች መካከል አንዳንዶቹ ልማታዊው መንግስት እያደረገላቸው ድጋፍ በርካታ ባለሃብቶች በሃገር ውስጥ እንዲፈጠሩ ከማድረግ ሌላ በድህነት ላይ በሚደረገው ዘመቻ ላይ የራሳቸውን አሻራ እንዲያሳርፉ ከፍተኛ እገዛ እያደረገ ይገኛል ብለዋል፡፡  በሲዳማ ዞን ባለፉት 15 ዓመታት ከሁለት ቢሊዮን ብር በላይ ካፒታል ያስመዘገቡ ከ770 በላይ ባለሃብቶች በኢንቨሰትመንት መሰክ በመሰማራት ከ56 ሺህ ለሚበልጡ ዜጎች ቋሚና ጊዜያዊ የስራ እድል መፍጠራቸውን አቶ ብርሃኑ አስታውቀዋል፡፡ ምንጭ፦ ኢዜኣ 1/28/2014

የኮፒ ፔስት ጉዳይ ወዴት እየወሰደን ይሆን?..............እንዳለ ደበላ ሀዋሳ ኢዜአ

ዘወትር ከሚቀመጡባት የዛፍ ጥላ ስር ዛሬም እንደወትሯቸው ተቀምጠዋል። በተለመደው ሁኔታ ከፊት ለፊታቸው ካለች ሰባራ የእንጨት ባለመደገፊያ ወንበር ላይ የተቀመጡ ደምበኛቸው የመጡበትን ሁኔታ እየገለጹላቸው ነው።  እርጅናና ኑሮ ያጎሳቆለው እጃቸው ቢንቀጠቀጥም እንደወትሮ አስኪሪፕቶ ጨብጦ ከባለጉዳያቸው የሚነገራቸውን ዋና ዋና ሀሳብ በያዟት እንደርሳቸው እድሜ የተጎሳቆለች የምትመስል ማስታወሻ ቢጤ ደብተር ላይ ጫር ጫር ያደርጋሉ።  እንግዳቸው የመጡበትን ጉዳይ አስረድተው እንደጨረሱ ሻምበል ቢተው በተለመደ ሁኔታ በመካከሉ ካርቦን የገባበት የታጠፈ ወረቀት አውጥተው መጻፍ ጀመሩ።  የመጀመሪያውን ጨርሰው ሌላ ሁለተኛ ካርቦን በመካከሉ የገባበት ወረቅት አውጥተው ያለ ምንም የሀሳብ መቆራረጥ በሚንቀጠቀጥ እጃቸው በማስታወሻ ላይ የጫሩትን ሀሳብ መልከት እያደረጉ የቃላት ዝናብ በወረቀቱ ላይ ያዘንቡ ጀመር።  እንደጨረሱ የጻፏቸውን ሁለት ገጽ ወረቀቶች በየተራ አንብበው እንደጨረሱ ለደንበኛቸው አስፈረሙበትና ቴምብር ለጥፈው በክላሰር በማድረግ ሰጧቸው።  ለዚህ አገልግሎታቸው ከደንበኛቸው የክላሰሩንና የቴምብሩን ዋጋ ሳይጨምር የተቀበሉት 20 ብር ብቻ ነው።  ዛሬ ዘመናዊው አለም በፈጠራቸው የጽሁፍ ማሽኖች ሳቢያ የምንጽፋቸው ጽሁፎች ለራሳችንም የማይገቡና ግራ የሚያጋቡ እየሆኑና በኮፒ ፔስት የተሞሉ ጽሁፎች ተበራከተው በመጡበት ወቅት ራፖር ጸሀፊው ሻምበል ያለምንም መመሳሰልና ኮፒ ፔስት የባለጉዳዮቻቸውን ሀሳብ አዳምጠው ያለምንም የሀሳብ መቆራረጥ ለሁሉም በሚገባ መልኩ ያለማቋረጥ ይጽፋሉ።  የደረስንበት የቴክኖሎጂ አለም ስራችንን ቀልጣፋና በአጭር ጊዜ እንድናከናውን የረዳን ቢሆኑም ኢንተርኔትና ፌስ ቡክ አድራጊና ፈጣሪ በመሆን ከአዕምሯችን አፍልቀን እንዳንጽፍ እን