በሲዳማ ዞን ዘንድሮ ከ72 ሺህ የሚበልጡ ወጣቶች የስራ እድል ተጠቃሚ ለማድረግ ታቅዷል ሐዋሳ ህዳር 20/2006 በሲዳማ ዞን በተያዘው ዓመት ከ72 ሺህ የሚበልጡ ስራ አጥ ወጣቶች በገጠር ስራ እድል ፈጠራ እና ልማት ፕሮግራም ተጠቃሚ እንደሚሆኑ የዞኑ ዋና አስተዳደሪ ገለጹ፡፡ የዞኑ የገጠር ስራ እድል ፈጠራና ልማት ጽህፈት ቤት ከባለድርሻ አካላት ጋር የምክክር መድረክ አካሂደዋል፡፡ የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አክሊሉ አዱላ በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች፣ የቴክኒክና ሙያ ተቋማት፣ ከግል ኮሌጆችና አስርኛ ክፍል ላጠናቀቁ ዜጎች ሰፊ የስራ እድል ተዘጋጅቷል፡፡ ሃገራዊም ሆነ ክልላዊ የምጣኔ ሃብታችን እድገት ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር የገጠር ስራ እድል ፈጠራና ልማት እንቅስቃሴ ለማሳካት የሚያስችሉ ጠንካራ ስልቶች ተግባራዊ ማድረግ ወሳኝ በመሆኑ በየደረጃው የሚገኙ የባለድርሻ አካላት ጠንክረው መስራት እንዳለባቸው ጠቁመዋል፡፡ ሀገሪቱን መካከለኛ ገቢ ካላቸው ሃገሮች ተርታ ለማሰለፍ በመንግስት በኩል ልዩ ትኩረት ከተሰጣቸው ልማታዊ እንቅስቃሴዎች አንዱ ለዜጎች ሰፊ የስራ እድል በመፍጠር ዘርፉ ውጤታማ እንዲሆኑ ማስቻል ቁልፍ ጉዳይ በመሆኑ ትኩረት ተሰጥቶ ሊሰራ ይገባዋል ብለዋል፡፡ ለዘርፉ ወቅታዊ ድጋፍና ክትትል ማድረግ በግብርና የሚመራው ክፍለ ኢኮኖሚ ወደ ኢንዱስትሪ ለማሸጋገርና ልማታዊ ባለሃብቶችን ለመፍጠር ከሚያበረክተው አስተዋጽኦ ባሻገር ስራ አጥነትንና ድህነትን ለመቅረፍና ስራ ፈጣሪ ዜጎችን ለማፍራት ያለው ጠቀሜታ ከፍተኛ በመሆኑ ሁሉም መረባረብ እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡ በዘርፉ የሚታዩ ችግሮችን ከመሰረቱ ለመቅረፍ የአመራርንና የባለሙያውን አመለካከት ከመቀየር አኳያ ከ100 ሺህ ለመበልጡ የዞን፣ የወረዳና ለቀበሌ አመራሮች የአቅም ግንባታ ስልጠና
It's about Sidaama!