Skip to main content

Posts

Showing posts from October, 2013

በወቅታዊ የሲዳማ ዞን የፖለቲካ ኣጀንዳ፧ ሲዳማ ዞን መንግስት የሚያካህዳቸውን የልማት ስራዎች ምርጫ ተኮር ከመሆን ኣልፈው ለህዝቡ እድገት እና ብልጽግና መሆን ኣለባቸው

New Photo from Internet በሲዳማ ዞን የየወረዳ ካቢኔዎች በየወረዳው የሚገኙትን ቀበሌዎች በመከፋፈል ወቅታዊ የዞኑ መንግስት ኣጀንዳ በሆነው የግብርና ስራ ላይ ከየቀበሌዎቹ ነዋሪዎች ጋር በመምክር ላይ መሆናቸው ታውቋል። በምክክሩ ላይ ኣርሶ ኣደሮቹ በ 2006 ዓም ለማምረት እና ለመስራት በሚፈልጉትን ስራ እና ምርት በማቀድ እያንዳንዳቸው በጽሁፍ እንዲያቀርቡ በመደረግ ላይ ነው ሲሆን፤ ከዚህም ባሻገር በሌሎች ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ላይ በኣርሶ ኣደሮቹ ለተነሱ ጥያቄዎች በካቢኔ ኣባላት ማብራርያ እየተሰጠባቸው ነው። ካቢኔዎቹ ከኣርሶ ኣደሮቹ ጋር ባደረጉት ውይይት በባለፈው ዓመት ማለትም በ 2005 ዓም የምርት ዘመን በታዩ ድክመቶችን እና ጥንካሬዎችን የመረመሩ ሲሆን፤ በዚህ ዓመት ድክመቶቹን በማረም ጥንካሬዎችን የበለጠ በማጠናከር በምቻልበት ሁኔታ ላይ ትኩረት ሰጥተዋል ተብሏል። በውይይቱ ላይ ካቢኔዎቹ እንዳሉት ከሆነ፤ የሲዳማ ኣርሶ ኣደሮች በእጃቸው ያለው ሃብት መሬት፤ የሰው ኃይል እና ውሃ በመሆኑ እነዚህን በማቀናጄት የበለጠ ምርታማነትን ማረጋገጥ ይቻላል። በምቀጥሉት የበጋ ወራት የግብርና ምርታማነትን ለማረጋገጥ በትንሽ ጊዜ ውስጥ ልደርሱ የምችሉ የግብርና ምርቶችን እንዲያመርቱ የምደረግ ሲሆን፤ ለዚህም ውሃ ከማሳቸው ኣጠገብ ያላቸው ኣርሶ ኣደሮች ከዚሁ የውሃ ሀብት እንዲጠቀሙ፧ ውሃ ከማሳቸው ኣጠገብ የሌላቸው ደግሞ የውሃ ጉርጓድ እንድቆፍሩ መክረዋል። ሪፖርተራችን ጥቻ ወራና በወቅታዊው የሲዳማ ፖለቲካ ላይ ያናገራቸው ስማቸውን እንዲገለጽ ያልፈለጉ የሲዳማ ፖለቲካ ተንታኝ የካቢኔዎቹ የልማት ዘማቻ ድብቅ ኣጀንዳ ያጋለጡ ሲሆን፤ የሲዳማን ኣርሶ ኣደሮች ምርታማነትን ለማሳደግ ካቢኔዎቹ በማድረግ ላይ ካሉት እንቅስ

ካላ ደሴ ዳልኬ በወላይታ ዞን በሁምቦ ወረዳ ኣባያ ቢሳሬ ቀበሌ ነዋሪ በሆኑ የሲዳማ ተወላጆች ላይ በኣከባቢው ነዋሪዎች የሚፈጸሙ ወንጀሎች እንዲቆሙ ትዕዛዝ ሰጡ

ካላ ደሴ ዳልኬ የደቡብ ክልል ፕሬዚዳንት ከኣንድ ወር በፊት በወላይታ ዞን በሁምቦ ወረዳ ኣባያ ቢሳሬ ቀበሌ ውስጥ ነዋሪ የሆኑ የሲዳማ ተወላጆች ላይ በኣከባቢው ነዋሪዎች የተለያዩ ወንጀሎች እንደተፈጸሙባቸው እና ቤት ንብረታቸውን በእነዚሁ ሰዎች መቃጠሉን ብሎም ኣከባቢውን በኣስቸኳይ እንዲለቁ በምል የማስፈራሪያ ዛቻ እንደደረሳቸው በቪድዮ የተደገፈ መረጃ በማቅረብ የሲዳማ ዞን መንግስት እና የቦርቻ ወረዳ ኣስተዳደር መፍትሄ እንዲፈልግላቸው ጥሪ ማቅረባችን ይታወሳል። በጉዳዩ ላይ ሪፖርተራችን ጥቻ ወራና ታማኝ ምንጭ ጠቅሶ ከሃዋሳ እንደዘገበው፤ እነዚሁ በቤትንብረታቸው ላይ ጉዳት የደረሰባቸው የሲዳማ ተወላጆች 18 ተወካዮችን መርጠው ወደ ሃዋሳ በመላክ ለደቡብ ክልል ፕሬዚዳንት ለካላ ደሴ ዳልኬ ኣቤቶታ ኣቅርበዋል። የተጎጂዎቹን ተወካዮች በቢሮቸው ተቀብለው ያነጋገሩት የክልሉ ፕሬዚዳንት ካላ ደሴ፤ በኣስቸኳይ ጉዳይ ኣጣሪ ቡድን በመሰዬም እና ቡድኑን ወደ ቀበሌው በመላክ የወንጀሉ መፈጸም ኣለመፈጸም እንድጣራ ማድረጋቸው ታውቋል። ኣጣሪ ቡድኑ ባቀረበው ሪፖርት በሲዳማ ተወላጆች ላይ ወንጀል መፈጽሙን በማረጋገጡ፤ ካላ ደሴ ዳልኬ በኣከባቢው ነዋሪዎች የወደሙ ቤቶች እንድገነቡ እና በኣከባቢው ተወላጆች በሲዳማዎች ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎች በኣስቸኳን እንዲቆሙ ትዕዛዝ መስጠታቸው ተገልጸዋል። ፕሬዚዳንቱ በሰጡት ትዕዛዝ መሰረት በኣከባቢው ያለውን ችግር የመፍታት ስራ በመሰራት ላይ ሲሆን፤ ህዝቡም በመረጋጋት ላይ ነው ተብሏል። ኣዲሱ የክልሉ ፕሬዚዳንት ካላ ደሴ ዳልኬ ተጎጂዎቹ ያቀረቡትን ኣቤቶታ በመስማት እና በኣስቸኳይ መፍትሄ በማፈላለግ ሀላፊነታቸውን በመወጣታቸው እና ለተጎጂ የሲዳማ ተወላጆች ኣጋሪነታቸውን በማሳየታቸው መደሰታቸውን

የቀድሞው የፌዴራል ቤቶች ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር የነበሩት አቶ ተፈሪ ፍቅሬ በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው ዛሬ ፍርድ ቤት ቀረቡ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 19 ፣ 2006 (ኤፍ ቢ ሲ)  የቀድሞው የፌዴራል ቤቶች ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር የነበሩት አቶ ተፈሪ ፍቅሬ በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው ዛሬ ፍርድ ቤት ቀረቡ። ተከሳሹ የፌዴራል ቤቶች ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር በመሆን ከ2002 እስከ 2005 ዓመተ ምህረት ያገለገሉት    አቶ ተፈሪ ፍቅሬ የፌደራል የስነ ምግባርና    ፀረ ሙስና    አቃቢ ህግ በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አንደኛ ወንጀል ችሎት ክስ መስርቶባቸዋል ። በግለሰቡ ላይ የተከፈተው    የክስ መዝገብ ተከሳሹ የተሰጣቸውን የመንግስት ሃላፊነት ያለአግባብ ተጠቅመው የማይገባ ጥቅም ለማግኘትና ለሌሎች ለማስገኘት በማሰብ ፤ በቀድሞው ወረዳ 23 ቀበሌ 12 በውጭ ምንዛሬ ተከራይቶ የነበረውን የቤት ቁጥር 106 የመንግስት ቤት ለኢትዮጵያውያን እንዲከራይ ግምት እንዲሰራ በታዘዘው መሰረት በባለሙያዎች 1 ሺህ 998 ብር ተመን ከወጣለት በኋላ ፤ የኤጀንሲውን የተለመደ አሰራር በመጣስና የባለሙያዎችን የኪራይ ግምት ውድቅ በማድረግ ለአንዲት ግለሰብ ተመኑን ቀንሰው አከራይተዋል። በዚህም ከ2002 እስከ 2005 ዓመተ ምህረት መንግስት ከቤቱ ማግኘት የነበረበትን 17 ሺህ 420 ብር በማሳጣትና በመንግስት ላይ ጉዳት አድርሰው ተከራይን ያለአግባብ ተጠቃሚ አድርገዋል ይላል ። በቀድሞው ወረዳ 21 ቀበሌ 01 የቤት ቁጥር 112/40 የሆነውን የመንግስት መኖሪያ ቤት ባሰፋ ትሬዲንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ድርጅት፥ ለመኖሪያነት አገልግሎት በጨረታ አሸንፎ 7 ሺህ 650 ብር እየከፈለ ይኖርበት የነበረውን ቤት፤ ተከሳሹ ከተከራይ ድርጅቱ ጋር በመመሳጠር ቤቱ ለመኖሪያ ቤትነት እንደተሰጠ እየታወቀ ለስራ አልተመቸኝም በማለት እንዲያመለክቱ አድርገው ፤ የኤጀንሲውን መመሪያ ወደጎን በመተው በዚ

የሲዳማ ዞን የካቢኔ ሽግሽግ የመተካካት ፖሊስን የተከተለ ነውን?

ጥቻ ወራና  (Xiichcha Woraana) ከሲዳማ እንደ ዘገበው፤ የቀድሞ የሲዳማ ዞን መንግስት ዋና ኣስተዳዳሪ የነበሩትን ካላ ሚሊዮን ማቲዎስ ከሲዳማ ዞን ለቀው ወደ ክልል ያመሩ ሲሆን የደቡብ ክልል ትምህርት ቢሮ ሃለፊ ሆነዋል። በካላ ሚሊዮን ማቲዎስ ቦታ ከሃርቤጎና እንደመጡ የምነገርላቸውን የቀድሞው የዞኑ የድርጅት ጉዳይ መምሪያ ሀላፊ ካላ ኣክልሉ ኣዴላ ተተክተዋል። በካላ ኣክልሉ ቦታ ደግሞ ካላ ደስታ ላታሞ የዞኑ ድርጅት ጉዳይ መምሪያ ሀላፊ ሆነው ተሹመዋል። በተመሳሳይም የዞኑ ፋይናንስ መምሪያ ሀላፊ ሆነው ስሰሩ የቆዩት ካላ በቀለ ታፎ ወደ ሲዳማ ዞን ስቪል ሰርቪስ መምሪያ ተዛውረዋል። በካላ በቀለ ቦታ የቀድሞ የሸቤድኖ ወረዳ ዋና ኣስተዳዳሪ ካላ ታረቀኝ ጋቤራ ተተክተዋል። የሲዳማ ዞን የካቢኔ ሽግሽግ በተመለከተ  ጥቻ ወራና  ያሰባሰብናቸው የህዝብ ኣስተያዬት እንደምያመለክተው፤ ሰሞኑን በሲዳማ ዞን ኣስተዳደር የተደረገው የካቢኔ ሽግሽግ የኣገሪቱ መንግስት በመከተል ላይ ያለውን የመተካካትን ፖሊስ ተግባራዊ ያላደረገ ነው። የካቢኔ ሽግሽጉ የዞኑን የመምሪያ ሃለፊዎች ከመምሪያ ወደ መምሪያ የቀያየር እንጂ የመተካካትን ፖሊስ ተግባራዊ በማድረግ ኣዳዲስ መሪዎችን ያመጣ ኣይደለም። እንደነዚሁ ኣስተያየት ሰጪዎች ከሆነ፤ ጉልቻ መቀያየር ወጥ ኣያጣፍጥም እንደምባለው ሀላፊዎችን ከመምሪያ ወደ መምሪያ መቀያየር ብዙም ለውጥ ኣያመጣም ብለዋል። በተመሳሳይም የካለ ሚሊዮን ማቲዎስ ወደ ክልል ትምህርት ቢሮ መዛወራቸውን በርካታ ኣስተያየት ሰጭዎች የተቃወሙ ሲሆን፤ የካላ ሚሊዮን ኣባት ካላ ማቲዎስ ለሲዳማ ህዝብ መብት መከበር ያደረጉትን መስዋዕትነት ከግንዛቤ ውስጥ በማስገባት እና ካላ ሚሊዮን የዞኑ ዋና ኣስተዳደሪ በመሆን በቆዩባቸው ኣመታት በሲዳማ

Ethiopia: After the Middlemen

EDITORIAL My early readings on global economics involve writings by the renowned economic historian Niall Ferguson and the Nobel Laureate Joseph Stiglitz. Reading the works of these intellectuals, especially the unconventional thoughts of Stiglitz on markets, have helped me realise the dynamics of the global market place. At the base of the historical records of Ferguson as well as the ground breaking revelations of Stiglitz lays the fundamental theories of market information. Unlike the claims by classical economic theories, market information exists and flows asymmetrically. It is this asymmetry of information that mediates the very act of transactions. Markets exist as mediums of hosting this transaction. There is no way that a buyer and a seller could have the same information - in both quality and quantity - about a given good or service they want to transact. Certainly, one of them knows more about the service and hence fixes the price. Often, it is the seller who kn

No Easy Way to Democratise Ethiopia

ANALYSIS Ethiopia must not indulge in democracy until it accomplishes good governance. There still are problems of competence, diligence, character, dedication and integrity of the civil service that need to be attended. Of course, the nation is exhibiting improvements in these tenets, even if some might erroneously claim they are deteriorating. Ethiopia's political journey must prioritise the job of creating a healthy business atmosphere the heart of good governance and electoral democracy. The business sphere and the powerhouse of the visionless Ethiopian oppositions must be corrected before it gets beyond repair. The political opposition, rather than working on developing its own capacity, is seen hunting opportunities that could quench its quest for power. This is happening whilst it is still visibly incompetent. The nation was reticent with a view to assist the private sector to flourish. But the businessmen were doing every wrong in order to collect as much wealth

Ethiopia: When an Economy Goes Wrong

ANALYSIS The change in the rate of economic growth from one year to the next is approximated by the aggregate values of goods and services adjusted in their current prices. These figures are often understood to be figures representing the annual economic growth of a country. But this expression of growth is a misnomer to many people who may be taking growth to mean the reduction in the cost of living. One can not blame such folks because they are not aware of what this economic growth concept really means when it translate into what or how much of goods and services they could buy with the money in their pockets. Official who give press conferences on this subject added that about one million jobless people were employed in the past year. This is a good news, even many world leaders, including president Barack Obama of United States, would envy even if the Ethiopian officials do not mention the number of the unemployed. Employing one million people annually, in an agricult

በኢትዮጵያ ፕሪሚዬር ሊግ ተሳታፊ የሆኑት የሲዳማ እግር ኳስ ክለቦች በመጀመሪያ ጫዋታዎቻቸው ሽንፈት ኣስተናግደዋል

New በኢትዮጵያ ፕሪሚዬር ሊግ ተሳታፊ የሆኑት የሲዳማ ቡና እና ሃዋሳ ከነማ የእግር ኳስ ክለቦች በመጀመሪያ ጫዋታዎቻቸው ሽንፈት ኣስተናግደዋል። በትናንትናው እለት መከላከያን የገጠመው የሲዳማ ቡና 3 ለ 1 የተሸነፈ ሲሆን ሃዋሳ ከነማ በበኩሉ መብራት ኃይልን ገጥሞ 2 ለ1 ተሸንፏል። ሁለቱም  የሲዳማ ክለቦች የዘንድሮውን ፕሪሚዬር ሊግ በሽንፈት መጀመራቸው ለኣመቱ ውድድር ያደረጉት ዝግጅት ጥንካሬን በተመለከተ በኣንዳንድ የክለቦቹ ደጋፊዎች ዘንድ ጥርጣሬ እንዲያድርባቸው ኣድርጓል። በምቀጥሉት ጫዋታዎች ኣቋማቸውን ኣስተካክለው ነጥብ እንደምሰበስቡ እና ወደ ቀድሞ ጥንካሬያቸው እንደምመለሱ ይጠበቃል። 

የባለፈው ኣመት የሲዳማ ብሎም የኣገሪቱ የቡና ኤክስፖርት ምን ይመስል ነበር

Price Discrepancy Stunts Coffee Exports For over four years now, the headquarters of the Ethiopian Commodity Exchange (ECX), located in the Chelelk-Alsam Tower on Chad Street, has shone with the price ticker board displaying the country is own commodity prices. The prices displayed on the ticker board which is wrapped around the waist of the building appear in green, yellow and red, respectively indicating increases, stability or plunges. The prices for different varieties of coffee, however, which take up most of the space on the board, are, drawing a lot of frustration from exporters these days. They say it does not reflect international market conditions. Whereas the board was initially intended to help the traders in price discovery, that, say traders, is no longer the case. One such exporter is Adem Kedir, for whom coffee trading is not just a business, but a family heritage in which his father and brothers are also employed. After starting out helping in his father’s

የፍቼ ጫምባላላ በዓል የሲዳማ ብቻ ሳይሆን የዓለም ቅርስ ሊሆን ይገባል፤

የሲዳማ ዞን ከምድር ወገብ በስተሰሜን አካባቢ ይገኛል። በሰሜናዊ ምስራቅና በደቡባዊ ምስራቅ የኦሮሚያ ክልል በደቡብ ጌዲኦ ዞንና የኦሮሚያ ክልል፣ በምእራብ በኩል ደግሞ የወላይታ ዞን ያዋስኑታል። ዞኑ በሶስት የአየር ንብረቶች የሚካተት ሲሆን  30 በመቶ ደጋ፣  60  በመቶ ወይና ደጋ፣ 10  በመቶ በቆላ ይሸፈናል። የዞኑ አጠቃላይ የቆዳ ስፋት  7 ሺ  200  ካሬ ኪሎ ሜትር ሲሆን በ 19  የገጠር ወረዳዎችና በሁለት የከተማ አስተዳደሮች የተዋቀረ ነው። በ 1999  ዓ . ም በተካሄደው የህዝብና የቤቶች ቆጠራ መሰረት በዞኑ የሚገኘው የሲዳማ ህዝብ ብዛት  3 ነጥብ 2 ሚሊዮን እንደሚሆን ተገምቷል። የሲዳማ ብሄር በሰሜናዊ ምስራቅ አፍሪካ ከሚገኙ የኩሽ ቋንቋ ተናጋሪዎች መካከል ተጠቃሽ ሲሆን በደቡብ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል ከሚገኙ ዞኖች አንዱ ነው። የሲዳማ ብሄር የራሱ የሆነ የጊዜ አቆጣጠር ቀመር ያለው ሲሆን ቀመሩን ተከትሎ የፍቼ የዘመን መለወጫ በዓል በድምቅት ይከበራል። የፍቼ በዓል የሚከበርበትን ቀን  « አያንቶ » ( የተመረጡ አዛውንቶች )  ክዋክብት በጨረቃ ዙሪያ የሚያደርጉትን ኡደት በመቃኘት ይወስናሉ። በጎሳ መሪው  ( ሞቴው )  ውሳኔ መሰረት የበዓሉ ቀን ከታወጀ በኋላ ሁሉም በየፊናው ዝግጅቱን ያጧጡፋል። በዓሉም እስከ ሁለት ሳምንታት ለሚደርስ ጊዜ በየአካባቢው በሚገኙ  « ጉዱማይሌዎች » ( አደባባዮች )  በድምቀት ይከበራል። ጉዱማይሌ በዞኑ በሚገኙ መንደራት ሁሉ የሚገኝ ሲሆን ትልቅ ክብር የሚሰጠው ቦታ ነው። አራስ የመታረሻ ጊዜዋ አብቅቶ ከመውጣቷ በፊት ከልጇ ጋር በቅድሚያ የምታየው ጉዱማይሌውን ነው። ሙሽሮች ከሰርጋቸው ማግስት ጀምሮ ጉዱማይሌን ሳያዩ ወደአዲሱ ኑሯቸው አይቀላቀሉም። የሲዳማ ብሄር ተወላጆች እንደየእድሜያቸውና በ