Skip to main content

Posts

Showing posts from September, 2013

ኣብዛኛው ተማሪ ኣንደኛ ምርጫ የሆነውን ትምህርት ኣይነት እና ዩኒቨርሲቲ በማያገኝበት ሁኔታ፤ ዩኒቨርሲቲን እና የትምህርት ክፍል መቀያየርን መከልከል ምን ይሉታ?

ዩኒቨርሲቲ እና የትምህርት ክፍል መቀያየር አይቻልም - ትምህርት ሚኒስቴር አዲስ አበባ ፣ መስከረም 20 ፣ 2006 (ኤፍ ቢ ሲ) ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚገቡ ተማሪዎች አድራሻቸውን ጭምር በመጠቀም የዩኒቨርሲቲ እንቀያየር ማስታወቂያ ሲለጥፉ ይስተዋላል። ይህ ጉዳይ በተለይም በአዲስ አበባ አራት ኪሎ አካባቢ በስፋት ይስተዋላል ፤ አዲስ ገቢ ተማሪዎችም ይህን አካባቢ በብዛት ያዘወትሩታል። ተማሪዎቹ እንደሚሉት ከተለያዩ ሰዎች በሚያገኙት መረጃ መሰረት ዝውውሩን ለመጠየቅ ይነሳሳሉ። የተመደቡበት ቦታ ምቹ አይደለም በሚል ፣ ከቤተሰብ መራቅ ባለመፈለግ ፣ የተመደቡበት የትህርት ክፍል ከምርጫቸው ጋር አይጣጣምም የሚሉት ለዝውውሩ ዋነኛ ምክንያቶች ናቸው ። ተማሪዎቹ ከሚለጥፏቸው ማስታወቂያዎች በተጨማሪ ዩኒቨርሲቲ የሚቀያየሩ ተማሪዎችን እናገናኛለን የሚሉ እና በአጋጣሚው ለመጠቀም የሚሞክሩ ግለሰቦችም ይስተዋላሉ። የትምህርት ሚኒስቴር በበኩሉ የዩኒቨርሲቲም ሆነ የትምህርት ክፍል ዝውውር አይፈቀድም ይላል። በሚኒስቴሩ የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ደሳለኝ ሳሙኤል ፥ ተማሪዎቹ ባስመዘገቡት ውጤት እና በሞሉት ምርጫ መሰረት የተመደቡ በመሆኑ ጉዳዩ አይታሰብም ባይ ናቸው። አያይዘውም አዲሶቹም ሆኑ ነባሮቹ ተቋማት በሚገባ እና በሚሰጡት ትምህርት አግባብ የተደራጁ በመሆናቸው የትም ቢመደቡ ተማሪዎቹ ስጋት እንዳይገባቸውም ነው የተናገሩት። ከዚህ ባለፈ ግን የሚቀያየሩ ተማሪዎችን እናገናኛለን ከሚሉ ህገ ወጦችም ራሳቸውን ይጠብቁ ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። http://www.fanabc.com/index.php?option=com_content&view=article&id=5579:2013-09-30-07-42-38&a

ባህልን የመጠበቅ የመንግሥት ግዴታ

አገራችን ኢትዮጵያ የብዙ ባህሎች ባለቤት ናት፡፡ የብሔርና የሃይማኖት ብዙኅነት ያበዛቸው የተለያዩ ባህሎች የኢትዮጵያውያን መታወቂያ ናቸው፡፡ ኅብረተሰብን ኅብረተሰብ ከሚያስብሉት ምክንያቶች አንዱ ባህል ሲሆን፣ ባህሉ የማይታወቅለት ኅብረተሰብ በሌሎች አገሮችም የመታወቁ ነገር አነስተኛ ነው፡፡ አንዲት አገር ለምትከተለው ሁለንተናዊ የዕድገት አቅጣጫ ባህል የራሱ የሆነ አዎንታዊም ሆነ አሉታዊ ተፅዕኖ ይኖረዋል፡፡ በዚህ ጽሑፍ የምንመለከተው አወንታዊ ተፅዕኖ ያላቸውን ባህሎች የሕግ መሠረት ነው፡፡ እነዚህ ባህሎች ለኅብረተሰቡ ቀጣይ ሕልውና መሠረት የሆኑ፣ የአገሪቱን ልማት የሚያግዙና በዓለም አቀፍ ተቀባይነት ባላቸው መስፈርቶች ለግለሰቦች ጠቃሚ የሆኑ ናቸው፡፡ በዚህ ሳምንት እየተከበረ ያለውን የመስቀል በዓል መነሻ በማድረግ በዓላትን ተከትለው የሚታዩ ባህሎችን የሕግ መሠረት መመልከት የዚህ ጽሑፍ ዓላማ ነው፡፡ በዓላት ብዙ ብዙ ክፍል ቢኖራቸውም በአገራችን ባህል ላይ ሰፊ ተፅዕኖ ያደረጉት ሃይማኖታዊ በዓላት ስለመሆናቸው በድፍረት መናገር ይቻላል፡፡ ቁሳዊ የባህል ክፍሎችን ብንመለከት አለባበስ፣ አመጋገብ፣ ለጌጥ የምንጠቀምባቸው ዕቃዎች፣ በዓላቱ የሚከበሩባቸው ቦታዎች ወዘተ. ሃይማኖታዊ መሠረት አላቸው፡፡ የመስቀልን በዓል መነሻ አድርጎ ከሚታዩት ባህሎች ውስጥ በአልባሳት ላይ የሚታዩ ጥልፎች፣ በሰውነት ላይ የሚቀረፁ ጌጦች፣ በደረትና በጆሮ የሚንጠለጠሉ የመስቀል ጌጦች ይገኙበታል፡፡ በደቡብ ብሔሮችና ብሔረሰቦች የተለመዱት የመስቀል በዓል አከባበሮችን ተከትሎ የሚታዩት የአመጋገብ ባህል ተጨማሪ አስረጅ ነው፡፡ ግዙፋዊ ያልሆኑም ባህሎች ከሃይማኖት በመነጩ ባህሎች ይስተዋላል፡፡ ሕዝቡ በኅብረት በመሆን በየሰፈሩ ትናንሽ ደመራ መደመሩ፣ ለንግድ ወጥተው የነበሩ የኅብረ

Ethiopians demonstrate against anti-terrorism law

Ethiopians have taken to the streets of the capital Addis Ababa. They’ve protested what they termed as an intentional move by the government to criminalize them through the anti-terrorism law. The protesters claim that only citizens who have expressed opinions against the government have been subject to the law since it was adopted in 2009. The New York-based independent Committee to Protect Journalists says more than 10 journalists have been charged under Ethiopia’s anti-terrorism law, and that the country has the highest number of exiled journalists in the world.   Human Rights Watch has also expressed concerns over the law for what it calls the overly broad definition of “terrorist acts.”   The law’s provisions on support for terrorism contain a vague prohibition on “moral support” under which journalists have been convicted. Since 2011, eleven journalists have reportedly been convicted. The protesters demand that the government redefines who a terrorist is.   The ri

INFANT MORTALITY IN THE RURAL SIDAMA ZONE, SOUTHERN ETHIOPIA: EXAMINING THE CONTRIBUTION OF KEY PREGNANCY AND POSTNATAL HEALTH CARE SERVICES

http://www.google.com/url?sa=i&rct=j&q=&esrc=s&source=images&cd=&cad=rja&docid=Qll9yHLE2i6WeM&tbnid=WZR7Jjs1w1Lb1M:&ved=0CAQQjB0&url=http%3A%2F%2Fwww.msf.org.uk%2Fcountry-region%2Fethiopia&ei=EmJIUsTIB5DK9QTVo4HoBA&bvm=bv.53217764,d.eWU&psig=AFQjCNEu-ZFaU-fIpp51n14qm0ynB7DyDg&ust=1380561760755591 Summary Objectives: This study is aimed at examining the contribution of selected pregnancy and postnatal health care services to Infant Mortality (IM) in Southern Ethiopia. Method: Data were collected from 10 rural villages of the Sidama Zone, Southern Ethiopia, using a structured interview schedule. The 1,094 eligible women respondents were selected using a combination of simple random and multi-stage sampling techniques. The main outcome variable of the study (IM) was measured by reported infant deaths during the twelve months preceding the survey, and was estimated at 9.6% or 96 infant deaths per 1,000 births. Pregnancy and

በሲዳማ ዞን የገጠር ቀበሌ ተደራሽ መንገድ ግንባታ እንቅስቃሴ ጥሩ ሆኖ በጥራት ላይ ትኩረት ብሰጠው

በሲዳማ  ዞን ውስጥ ከኣንድ ቢሊዮን ብር በሚበልጥ ገንዘብ መንገድ መስራቱ እየተነገረ ያለ ሲሆን ፤ የመንገዶቹ ጥራት ግን ትኩረት የተሰጠበት ኣይመስልም። ሰሞኑን የዞኑ መንገድና ትራንስፖርት መምሪያ ይፋ ያደረገውን መረጃ ከታች ያንብቡ፦ አዋሳ መስከረም 19/2006 በሲዳማ ዞን በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት ከአንድ ቢሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ በአንድ ሺህ ኪሎ ሜትር በላይ የገጠር ቀበሌ ተደራሽ መንገድ ግንባታ መካሄዱን የዞኑ መንገድና ትራንስፖርት መምሪያ ገለጸ፡፡ በፕሮግራሙ ከ30 ሺህ ለሚበልጡ ስራ አጥ ወጣቶች የስራ ዕድል መፈጠሩ ተገልጿል፡፡ የመምሪያ ኃላፊ አቶ ማቴዎስ ዳንኤል ሰሞኑን ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት ሀገራዊና ክልላዊ የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅዱን ተከትሎ በዞኑ ሁሉም የገጠር ቀበሌ ደረጃቸውን በጠበቁና ክረምት ከበጋ በሚያገለግሉ መንገዶች ለማገናኘት በትኩረት እየተሰራ ይገኛል፡፡ ፕሮግራሙ በዞኑ ገጠርና ከተማ ፣በአምራችና አገልግሎት ሰጪ እንዲሁም በግብርናና ኢንዱስትሪ ዘርፎች መካከል የሚኖረውን ትስስር በማጠናከር አርሶ አደሩ ምርቱን ለገበያ በማቅረብ ከምርቱ ተጠቃሚ እንዲሆን ጠቀሜታው የጎላ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በዞኑ እስካሁን 927 ኪሎ ሜትር የገጠር ቀበሌዎችን ክረምት ከበጋ የሚያገለግል መንገድ መኖሩን ጠቁመው ሽፋኑን ከፍ ለማድረግ በበጀት ዓመት ከአንድ ሺህ ኪሎ ሜትር ባላይ መንገድ ግንባታ መከናወኑን ተናግረዋል፡፡ የቀበሌ ተደራሽ መንገድ ግንባታ 25 በመቶ በህብረተሰብ ተሳትፎ የሚሸፈን በመሆኑ ከ154 ሺህ በላይ ህዝብ በስራው በመሳተፍ 850 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን የጠረጋና ምንጣሮ ስራ ማከናወናቸውን ገልጸው ከ13 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ገንዘብ ከወጪ ማዳኑን አስረድተዋል፡፡ በዚሁ ስራ ከተሳተፉት የህብረተሰብ ክፍ

ወጣቱን በማብቃት ላይ መሠራት አለበት

የኢትዮጵያ የሕዝብ ብዛት ከ85 ሚሊዮን በላይ መሆኑን መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡ አገሪቱ ካላት የሕዝብ ብዛት ውስጥ ከሁለት ሦስተኛ በላዩ ወጣቶች ናቸው፡፡ ይህ በሚገባ የሚሠራበት ከሆነ እጅግ መልካም አጋጣሚ መሆኑ አያጠራጥርም፡፡ ምክንያቱም ወጣቶች የማኅበረሰቡ የጀርባ አጥንት መሆናቸውን በማስመስከራቸው ነው፡፡  ኢትዮጵያ እንደ አገር ይህንን የወጣት ኅብረተሰብ ፍሬያማ በማድረግ ልታተርፍበት ትችላለች፡፡ መንግሥት ይህንን በመገንዘብ የወጣቶች ፖሊሲ ቀርፆ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል፡፡ ሆኖም ግን መንግሥት የአገሪቱን ወጣቶች አቅም በሚገባ አደራጅቶ እየተጠቀመበት ነው ለማለት ያስቸግራል፡፡ ስለዚህ መንግሥት ይህን ግዙፍና ጠንካራ የሆነ የኅብረተሰብ አካል እንዴት ሊጠቀምበት እንደሚችል ማሰብ ይገባዋል፡፡  እንደ አሜሪካ ባሉ የዓለማችን ኃያላን አገሮች ወጣቶች ያላቸው ተፅዕኖ ምን ያህል ከፍተኛ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ለአብነት እንኳን በዓለማችን በሰፊው የሚታወቀው የፌስቡክ ማኅበረሰብ ድረ ገጽ መሥራችና ባለቤት ወጣት አሜሪካዊ ነው፡፡ የ29 ዓመቱ ማርክ ዘከርበርግ በፌስቡክ ድረ ገጽ በኩል ከአንድ ቢሊዮን በላይ ተጠቃሚዎችን ማፍራት ችሏል፡፡ በዚህም ከአሜሪካ አልፎ በዓለማችን ላይ ተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰብ አድርጐታል፡፡ እዚህ ላይ ልብ ሊባል የሚገባው ነገር ለዚህ ወጣት ጉዞ መሳካት በርካቶች እጃቸው አለበት፡፡ ለአብነት የፌስቡክን ባለቤት አነሳን እንጂ በአሜሪካ ለአገርም ሆነ ለሕዝባቸው ኩራት የሆኑ በርካታ ወጣቶች ይገኛሉ፡፡ እነዚህ ወጣቶች ከአገራቸው አልፈው በዓለማችን ላይ እንደዚህ ተፅዕኖ ፈጣሪ እንዲሆኑ ያስቻላቸው ዓቢይ ጉዳይ ደግሞ፣ ለወጣቶች ምቹ የሆነ ፖለሲ በአገራቸው በመኖሩ ነው፡፡ ታዲያ እኛም እንደ አገር ከዚህ ልንማር የምንች

Hawassa University won Grants from NORHED

Hawassa University has won grants for four grand projects proposed by its different academic units some in partnership with foreign and local universities. Two projects from the Main Campus and two others from the College of Agriculture have secured funding from NORHED/NORAD for staff capacity building (Masters and PhD), collaborative research and training. The two projects at the Main Campus are one from College of Social Science & Humanities- School of Language & Communication Study and the other is from College of Law & Governance from Governance & Development Studies. The two projects are entitled “ Linguistic Capacity Building – Tools for the inclusive development of Ethiopia ” and   ‘ Institutional Cooperation for Capacity Building of Universities and Local Authorities for Democratic and Economic Governance in South Sudan and Ethiopia (ICBULGOV)’   respectively. The project entitled “ Linguistic Capacity Building – Tools for the inclusive development of Et

በወላይታ ዞን ውስጥ ነዋሪ የሆኑ የሲዳማ ተወላጆች በኣከባቢው ነዋሪዎች የምደርስባቸውን ግፍ እና ስቆቃ መቋቋም ስላቃታቸው የሲዳማ ዞን እና የቦርቻ ወረዳ ኣስተዳደር ጠልቃ እንድገባ እየተማጸኑ ነው

በወላይታ ዞን ውስጥ ነዋሪ የሆኑ የሲዳማ ተወላጆች በኣከባቢው ነዋሪዎች የምደርስባቸውን ግፍ እና ስቆቃ መቋቋም ስላቃታቸው የሲዳማ ዞን እና የቦርቻ ወረዳ ኣስተዳደር ጠልቃ እንድገባ እየተማጸኑ ነው። በወላይታ ዞን ውስጥ ነዋሪ የሆኑ የሲዳማ ተወላጆች በኣከባቢው ነዋሪዎች የምደርስባቸውን ግፍ እና ስቆቃ መቋቋም ስላቃታቸው የሲዳማ ዞን እና የቦርቻ ወረዳ ኣስተዳደር ጠልቃ እንድገባ እየተማጸኑ ነው። በካላ ማቲዎስ የቴ በተባሉ የተጎጂዎች ተወካይ በኩል በቪድዮ  ተደግፎ  በተላለፈው መልዕክት ላይ እንደተገለጸው፤ የኣካባቢው ነዋሪዎች በሲዳማ ተወላጆች ንብረት ላይ ጉዳት ከማድረስ ኣልፈው ኣከባቢውን በኣስቸኳይ ለቀው ካልወጡ በንብረታቸው እና በእነርሱም ላይ ጥቃት እንደምፈጽሙ በማስፈራራት ላይ መሆናቸው ተገልጿል።  በኣገሪቱ ብሎም በክልሉ ዜጎች እንደልባቸው በየትኛውም ኣካባቢ የመዘዋወር እና የመኖር ብሎም ንብረት የማፍራት መብት በህገ መንግስት ተደንግጎ  እያለ ይህን መሰል የሰብኣዊ መብት ጥቃት በሲዳማ ተወላጆች ላይ መድረሱ የኣገሪቱን ህገ መንግስት ጭምር የጣስ ኣካሄድ ነው ። በቪድዮ  ተደግፎ  የቀረበውን ይህንን  መልዕክት ከላይ ይመልከቱ

Queen Furra

Queen Furra I got an e-mail last night from one of my regular readers, Yaya, telling me my last post on Queen Furra got her curisoity going and asked me if I knew any material written about her and could direct her to it.I looked up in Encyclopadia Aethiopica (Harrasssowitz Verlag, 2005) and I found a half page entry written by a certain Anbessa Teferra.Here it is. The orgin of Furra, the legendary queen of the Sidama, is not clear.According to Gasparini, she was the wife of Ahmad b.Ibrahaim al-Gazi (Gragn, known as Diingamo Koyya among the Sidama).Others claim that Furra’s father was an honourable clan leader during the 14th or 15th cent. and when he passed away, she was made queen because she was the eldest daughter. According to some legends, Furra was a brutal ruler who, in particular, harshly repressed the men.Thus males were required to do all the household jobs which were customarily done by women.These included preparing food, scraping the   Enset , fetching water, cl

London: Conference on the Human Rights Situation in the Worst Hit Regions in Ethiopia – September 28, 2013

To all Oromos and Friends of Oromo! A human rights advocacy group, composed of oppressed peoples, have organized a conference on the current state of human rights situation in the worst hit regions in Ethiopia (Oromia, Ogaden, Somali, Sidama Shakacho, Anyuak and Benishangul States). Coordinated and sustainable effort is needed to make an end to repression and bring perpetrators to justice Please come & take a part in this important work. Date:   28 September 2013 Time:   14:00 – 21:30pm Venue:   West Training Unit 16 Merrick Road, Southall, UB2 4 AU, London http://gadaa.com/oduu/21865/2013/09/22/london-conference-on-the-human-rights-situation-in-the-worst-hit-regions-in-ethiopia-september-28-2013/

በሀዋሳና በሌሎች የኣገሪቱ ከተሞች የኢንዱስትሪ ዞኖችን ለመጀመር የሚያስችለው ጥናት እየተጠናቀቀ ነው

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 18 ፣ 2006 ( ኤፍ.ቢ.ሲ ) ለኢንዱስትሪ ዞንነት በተመረጡት አራት ከተሞች ላይ የኢንዱስትሪ መንደር ለማቋቋም የሚያስችለው ጥናት እየተገባደደ ነው ተባለ። የኢንዱስትሪ ሚንስትር አቶ አህመድ አብተው እንዳሉት ፥   በአዲስ አበባ ድሬድዋ ፣ ሀዋሳና ኮምቦልቻ ሊገነቡ የታቀዱትን የኢንዱስትሪ ዞኖች  ለመጀመር የሚያስችለው ጥናት እየተጠናቀቀ ነው። ከጥናቱ በተጓዳኝ መንደሩን ለመገንባት የሚያስችለውን ገንዘብ የማፈላለግ ሰራም እየተካሄደ ነው። በዚህ መሰረት ከአንድ የእስራኤል ድርጅት ጋር በኮምቦልቻ የሚገነባው የኢንዱስትሪ መንደር በትብብር ለመስራት የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ መፈረሙን ነው ሚነስትሩ የተናገሩት። በተመሳሳይ በአዲስ አባባ ለሚ ሳይት ከተገነባው በተጨማሪ ሌላ የኢንዱስትሪ መንደር ለመገንባትም ከአለም ባንክ ጋር ንግግር ተጀምሯል። በድሬድዋና በሃዋሳ ለሚገነቡት የኢንዱሰትሪ መንደሮችን ከመንግስት ጋር በመተባባር የመገንባት ፍላጎት  ያላቸው ድርጅቶችም የአዋጭነት ጥናት እያደረጉ ነው ተብሏል። http://www.fanabc.com/index.php?option=com_content&view=article&id=5555:2013-09-28-06-15-48&catid=102:slide

“ኢህአዴግ፤ የምትቃወሙትንም እኔ ነኝ የምሰጣችሁ እንዳይለን” - ተቃዋሚዎች

 “የኢህአዴግን የሥልጣን ዘመን አጭበርብረሃል” የሚል ወቀሳ ደርሶብኛል “ሥልጣን ለኢህአዴግ የምርጫ ሳይሆን የህልውና ጉዳይ ነው!” ውዲቷን ኢትዮጵያ ላለፉት 12 ዓመታት በርዕሰብሔርነት የመሯት (ወይስ መራቻቸው?) የ90 ዓመቱ አዛውንት ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ፤ ከጥቂት ቀናት በኋላ ሥልጣናቸውን በአደራ ለሰጣቸው ኢህአዴግ አስረክበው ከቤተመንግስት በመውጣት ኢህአዴግ ወዳዘጋጀላቸው መኖርያ ቤት ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል። “ሰላማዊ የሥልጣን ሽግግር ይደረጋል” ሲባል ሰማሁ ልበል? ወይስ ጆሮዬ ነው? (ጆሮዬ በሆነ!) ለምን መሰላችሁ? መቼም እሳቸው ከሥልጣን አልወርድም ብለው ከኢህአዴግ ጋር ሙግት ሊገጥሙ አይችሉም። ይሄማ ውለታ ቢስ መሆን ነው። እናላችሁ ---- “ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር” ከሚለው ይልቅ “ሰላማዊ የሥልጣን እርክክብ” ቢባል የተሻለ ሳይሆን አይቀርም የሚሉ ወገኖች አሉ። በነገራችሁ ላይ ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ በሥልጣን ዘመናቸው ከህመማቸው በቀር በሌላ በሌላው እድለኛ ናቸው ማለት ይቻላል። እንዴት ብትሉ---- ስንቱ ቱባ ቱባ የኢህአዴግ ሹማምንት በጋዜጠኞች ሲሞለጩና ሲተቹ፣ በፓርቲያቸው ሲገመገሙና “ሂሳችሁን ዋጡ” ሲባሉ፤ እሳቸው ግን ለ12 ዓመት እንደተከበሩ ኖረዋል። (ከተሳሳትኩ እታረማለሁ!) የፕሬዚዳንቱ አማካሪ አቶ አሰፋ ከሲቶ፤ “ውጤታማና እድለኛ ናቸው” ያሉት ለዚህ ይሆን እንዴ? በእርግጥ አልተሳሳቱም፤ሰውየው እድለኛ ናቸው። ባለቀ ሰዓት ግን ተቃዋሚ ፓርቲዎች ባልሾመ አንጀታቸው የትችት መዓት አወሩዱባቸው እንጂ። ባለፈው ሳምንት በዚሁ ጋዜጣ ላይ ስለፕሬዚዳንቱ የ12 ዓመት የሥልጣን ዘመን አስተያየት የሰጡ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎችና ምሁራን በአንድ ድምፅ “ውጤታማ አልነበሩም” ብለዋቸዋል። እኔ ፕሬዚዳንቱን ብሆን (ምኞት እኮ ነው!)

ጸረ _ረሃብ ተክል፦ የሲዳማ ዌሴ

Africa faces over the next decade an ever-increasing need to achieve sustainability in agricultural production. In the Horn of Africa one of the primary obstacles to sustainability has been the threat of famine. Yet, as this important booklet shows, there are parts of Ethiopia that survived famine during the 1980s because of the utilization of enset as part of the subsistence system. Also known as the false banana, enset is very likely the most unstudied domesticated crop in Africa. It helps to feed approximately ten million people in Ethiopia and Eritrea (in restricted pockets). Given that it figures so importantly in the diet of contemporary Ethiopians and that it has acted as a famine buffer, why has it been so neglected? The answers are complex. They are partly related to cultural perceptions, politics, and history. This short monograph unwraps much  of the mystery surrounding enset. It explores its history, noting that enset was once much more widespread in Ethiopia. It also

በጤና ተቋማት የሚወልዱ የሲዳማ እናቶች ቁጥር መጨመሩ እየተነገረ ነው

Recién nacido en Aroressa (©F. Schwieker-Miyandazi). አዋሳ መስከረም 16/2006 በሲዳማ ዞን በአንድ ለአምስት አደረጃጀትና በጤና ልማት ሰራዊት የተቀናጀ ጥረት በተከናወኑ ስራዎች በጤና ተቋም የሚወልዱ እናቶች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን የዞኑ ጤና መምሪያ ገለጸ፡፡ በመምሪያው የጤና ልማት እቅድ የስራ ሂደት ባለሙያ አቶ አበበ በካዬ ትናንት ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት እናቶች በጤና ተቋም እንዲወልዱ በማድረግ የእናቶችና ህፃናትን ሞት ለመቀነስ የሚደረገው ጥረት አበረታታች ነው፡፡ በዞኑ ሁሉም ወረዳ በአንድ አምስት አደረጃጀት፣ በጤና ልማት ሰራዊትና በጤና ኤክስቴንሽን አማካኝነት ህብረተሰቡን በማስተባበር የተከናወኑ ስራዎች በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ40 ሺህ በላይ እናቶች በጤና ተቋማት የወሊድ አገልግሎት ተጠቀሚ መሆን በመቻላቸው ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር በ10 ሺህ ብልጫ አለው ብለዋል፡፡ መምሪያው የወሊድ አገልግሎቱን በሁሉም ጤና ተቋማት በነፃ እንዲሰጥ በማድረጉ ወደ ጤና ተቋም ሄደው የቅድመ ወሊድ፣ የወሊድና የድህረ ወሊድ እንዲያገኙ ድጋፍ መደረጉ ለቁጥሩ መጨመር አስተዋጽኦ ማበርከቱን ተናግረዋል፡፡ የወሊድ አገልግሎት ካገኙት እናቶች መካከል 11 ሺህ በአዋላጅነት በሰለጠኑ የጤና ባለሙያዎች ሲሆን ቀሪዎቹ በጤና ኤክስቴንሽን አማካኝነት መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ በየቀበሌው የተመደቡ የጤና ኤክስቴንሽን ሰራተኞች ከአከባቢው ህብረተሰብ ጋር በመተባበር ሁሉም እናቶች ከጤና ተቋም ውጭ እንዳይወሊዱ የሚያደርጉት ሁሉ አቀፍ ጥረት ከፍተኛ ነው ብለዋል፡፡ በዞኑ በጤና ተቋም የሚወልዱ እናቶች ቁጥር ባለፉት ሶስት ዓመታት በከፍተኛ ፍጥነት እያደገ መጥቷል፡፡ የቅድመ ወሊድና ድህረ ወሊድ አገልግሎቱን በማጠናከር ከወሊድ ጋር በ

"On this mission I will be teaching, counseling and spreading the Gospel of Jesus the Christ to the people who live in Hawassa," Ingraham explained. "

  Dunnigan pastor hopes to weld ties with Ethopia A Dunnigan pastor is raising money - and prayers - to establish a church in Ethiopia. Pastor Lashanna Ingraham, 27, of Dunnigan's Body of Jesus the Christ Church has been invited on a two-year mission trip to Hawassa, Ethiopia by Pastor Bereket Asnake of Hawassa's Siloam Reformation Messenger's Church. "On this mission I will be teaching, counseling and spreading the Gospel of Jesus the Christ to the people who live in Hawassa," Ingraham explained. "(I will be) visiting their local churches and college, where approximately 3,000 locals and students gather on the college grounds every Friday for the opportunity to hear the word of God." Ingraham needs to raise $10,000 for the overseas trip, which is not the first exotic location to which Dunnigan's Body of Jesus the Christ's church has spread. Dunnigan's leader and founder, Pastor Herman Brown, works to train mini